Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 4:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ውስ​ጠ​ኛው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ደጅና ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ መግ​ቢያ የሚ​ወ​ስ​ደው የው​ስ​ጠ​ኛ​ውም የቤተ መቅ​ደሱ ደጆች የወ​ርቅ ነበሩ። እን​ዲ​ሁም ሰሎ​ሞን ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራው ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ የመብራት መኰስተሪያዎች፣ ለመርጨት የሚያገለግሉ ጐድጓዳ ሳሕኖች፣ ጭልፋዎችና ጥናዎች፣ እንደዚሁም የቤተ መቅደሱ የወርቅ መዝጊያዎች፣ ይኸውም የቅድስተ ቅዱሳኑ የውስጠኛው መዝጊያዎችና የቤተ መቅደሱ አዳራሽ መዝጊያዎች ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ጉጠቶቹንም ድስቶቹንም ሙዳዮቹንም ጀሞዎቹንም ከንጹሕ ወርቅ ሠራ። የውስጠኛውም ቤት የቅድስተ ቅዱሳን ደጆች የቤተ መቅደሱም ደጆች የወርቅ ነበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የመብራት ማብሪያና ማጥፊያዎች፥ ማንቈርቈሪያዎች፥ ጥናዎችና የእሳት መጫሪያዎች፤ እነዚህ ዕቃዎች ሁሉ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ናቸው፤ የቤተ መቅደሱ የውጪ በሮችና የቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችም በወርቅ የተለበጡ ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ጕጠቶቹንም ድስቶቹንም ጭልፋዎቹንም ማንደጃዎቹንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ። የውስጠኛውም ቤት የቅድስተ ቅዱሳን ደጆች የቤተ መቅደሱም ደጆች የወርቅ ነበሩ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 4:22
12 交叉引用  

የኪ​ሩ​ቤ​ል​ንና የዘ​ን​ባባ ዛፍ፥ የፈ​ነ​ዳም አበባ ሥዕል ቀረ​ጸ​ባ​ቸው፤ በተ​ቀ​ረ​ጸ​ውም ሥራ ላይ በወ​ርቅ ለበ​ጣ​ቸው፤ እስከ መድ​ረ​ካ​ቸ​ውም የተ​ያ​ያዙ ነበሩ።


ከጥሩ ወር​ቅም የተ​ሠ​ሩ​ትን ጽዋ​ዎ​ችና ጕጠ​ቶች፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽን​ሐ​ሖ​ችን፥ ለው​ስ​ጠ​ኛ​ውም ቤት ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ደጆች፥ ለቤተ መቅ​ደ​ሱም ደጆች የሚ​ሆ​ኑ​ትን የወ​ርቅ ማጠ​ፊ​ያ​ዎች አሠራ።


ነገር ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ከሚ​መ​ጣው ገን​ዘብ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ሆኑ የብር መዝ​ጊ​ያ​ዎች፥ ጽዋ​ዎ​ችና ጕጠ​ቶች፥ ድስ​ቶ​ችም፥ መለ​ከ​ቶ​ችም፥ የወ​ር​ቅና የብር ዕቃ​ዎ​ችም አል​ተ​ሠ​ሩም ነበር።


ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንና ማን​ካ​ዎ​ቹ​ንም፥ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹ​ንም የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ት​ንም የናስ ዕቃ ሁሉ ወሰዱ።


የመ​ብ​ራ​ቶች መቅ​ረ​ዞ​ች​ንና በላ​ያ​ቸው ያሉ መብ​ራ​ቶ​ችን፥ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ ማን​ኪ​ያ​ዎ​ቹን፥ ሥራ የሚ​ሠ​ሩ​ባ​ቸው ጻሕ​ሎ​ች​ንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ።


ሰሎ​ሞ​ንም አባቱ ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ የመ​ገ​ል​ገያ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ አም​ጥቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በነ​በ​ረው ግምጃ ቤት አገባ።


መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋን፥ የኵ​ስ​ታሪ ማድ​ረ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም ከጥሩ ወርቅ አድ​ርግ።


ለመ​ሠ​ዊ​ያው ክዳን ሥራ​ለት፤ መሸ​ፈ​ኛ​ውን፥ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ የሥጋ ሜን​ጦ​ዎ​ቹን፥ የእ​ሳት መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አድ​ርግ። ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ከናስ አድ​ርግ።


ሰባ​ቱ​ንም መብ​ራ​ቶ​ች​ዋን መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ የኵ​ስ​ታሪ ማድ​ረ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ።


ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንና መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንና ድስ​ቶ​ችን፥ ጭል​ፋ​ዎ​ች​ንም፥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ት​ንም የናስ ዕቃ ሁሉ ወሰዱ።


ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ መዝ​ጊ​ያም ሁለት ተዘ​ዋ​ዋሪ ሳን​ቃ​ዎች ነበ​ሩት፤ ለአ​ንዱ መዝ​ጊያ ሁለት፥ ለሌ​ላ​ውም መዝ​ጊያ ሁለት ሳን​ቃ​ዎች ነበ​ሩት።


跟着我们:

广告


广告