Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 4:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የእ​ግር መታ​ጠ​ቢ​ያ​ዎ​ችን፥ የእጅ መታ​ጠ​ቢ​ያ​ዎ​ችን፥ ጋኖ​ችን፥ የሥጋ ማውጫ ሜን​ጦ​ዎ​ች​ንና ኪራም የሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ ከን​ጹሕ ናስ ሠርቶ ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አቀ​ረ​በ​ለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ሜንጦዎችንና ከእነዚሁም ጋራ የተያያዙ ዕቃዎች። ኪራምአቢ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ እንዲሆኑ ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራለት ከሚብረቀረቅ ናስ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ምንቸቶቹንም መጫሪያዎቹንም ሜንጦዎቹንም ዕቃቸውንም ሁሉ ኪራም-አቢ ለንጉሡ ለሰሎሞን ለጌታ ቤት ከተሰነገለ ናስ ሠራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ምንቸቶቹንም መጫሪያዎቹንም ሜንጦዎቹንም ዕቃቸውንም ሁሉ ኪራም ለንጉሡ ለሰሎሞን ስለ እግዚአብሔር ቤት ከለስላሳ ናስ ሠራ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 4:16
13 交叉引用  

ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንም፥ መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንም፥ ዕቃ​ዎ​ቹ​ንም ሁሉ ኪራም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሠራ። በን​ጉሡ ቤትና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትም አርባ ስም​ንት አዕ​ማድ ነበሩ። ኪራ​ምም ለን​ጉሡ የሠ​ራ​ቸው ዕቃ​ዎች ሁሉ ከጥሩ ናስ ነበር።


ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንና ማን​ካ​ዎ​ቹ​ንም፥ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹ​ንም የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ት​ንም የናስ ዕቃ ሁሉ ወሰዱ።


ከሚ​ጢ​ብ​ሐ​ትና ከተ​መ​ረ​ጡት ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ከተ​ሞች ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፤ ከዚ​ህም ሰሎ​ሞን የና​ሱን ኩሬና ዓም​ዶች የና​ሱ​ንም ዕቃ ሠራ።


ለሥጋ ሜን​ጦ​ዎ​ቹና ለድ​ስ​ቶቹ፥ ለመ​ጠጥ ቍር​ባን መቅ​ጃ​ዎ​ቹም ጥሩ​ውን ወርቅ፥ ለወ​ር​ቁም ጽዋ​ዎች ወር​ቁን በየ​ጽ​ዋው ሁሉ በሚ​ዛን ሰጠው፤ ለብ​ሩም ጽዋ​ዎች ብሩን በየ​ጽ​ዋው በሚ​ዛን ሰጠው።


አሁ​ንም ብል​ሃ​ተ​ኛና አስ​ተ​ዋይ ሰው አቢ​ኪ​ራ​ምን ልኬ​ል​ሃ​ለሁ።


ኪራ​ምም ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንና መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ቤት ያሉ ማን​ኪ​ያ​ዎ​ች​ንና የመ​ገ​ል​ገ​ያ​ውን ዕቃ ሁሉ ሠራ። ኪራ​ምም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ።


አን​ድ​ዋ​ንም ኵሬ፥ በበ​ታ​ች​ዋም ያሉ​ትን ዐሥራ ሁለት በሬ​ዎች ሠራ።


ንጉ​ሡም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ሜዳ በሱ​ኮ​ትና በሴ​ድራ መካ​ከል ባለው በወ​ፍ​ራሙ መሬት ውስጥ አቀ​ለ​ጣ​ቸው።


ለመ​ሠ​ዊ​ያው ክዳን ሥራ​ለት፤ መሸ​ፈ​ኛ​ውን፥ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ የሥጋ ሜን​ጦ​ዎ​ቹን፥ የእ​ሳት መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አድ​ርግ። ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ከናስ አድ​ርግ።


የመ​ሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ዕቃ ሁሉ፥ ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንም፥ መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንም፥ ሜን​ጦ​ዎ​ቹ​ንም፥ የእ​ሳት ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ፤ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ከናስ አደ​ረገ።


跟着我们:

广告


广告