Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 36:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ስለ​ዚ​ህም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ንጉሥ አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ እር​ሱም ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን በቤተ መቅ​ደሱ ውስጥ በሰ​ይፍ ገደ​ላ​ቸው፤ለን​ጉ​ሣ​ቸው ለሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስም አል​ራ​ራ​ለ​ትም፤ ደና​ግ​ሉ​ንም አል​ማ​ረም፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወሰ​ዳ​ቸው፤ ሁሉ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ አሳ​ልፎ ሰጠው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ስለዚህ የባቢሎናውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ወጣቶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ፈጀ፤ ወጣቱንም ሆነ ወጣቲቱን፣ ሽማግሌውንም ሆነ በዕድሜ የገፋውን አላስቀረም፤ እግዚአብሔር ሁሉንም ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጉልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጎልማሳውንና ድንግሊቱን ሽማግሌውንና አዛውንቱን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለዚህ የባቢሎን ንጉሥ በእነርሱ ላይ አደጋ እንዲጥል እግዚአብሔር ፈቀደ፤ ንጉሡም በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩትን እንኳ ሳይቀር፥ በይሁዳ የሚገኙትን ወጣቶች ወንዶችን ሁሉ በሰይፍ ፈጀ፤ እግዚአብሔር ለናቡከደነፆር አሳልፎ ስለ ሰጣቸውም ወጣት ወይም ሽማግሌ፥ ወንድ ወይም ሴት ማንንም ሳይለይ፥ ሁሉንም ያለ ምሕረት አጠፋቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጕልማሶቻቸውን በቤተመቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጕልማሳውንና ቈንጆይቱን ሽማግሌውንና አሮጌውን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 36:17
39 交叉引用  

ወደ እር​ሱም ሮጡ በን​ጉ​ሡም ትእ​ዛዝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ ውስጥ በድ​ን​ጋይ ደበ​ደ​ቡት።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ሠራ​ዊት አለ​ቆች አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ ምና​ሴ​ንም በዛ​ን​ጅር ያዙት፤ በሰ​ን​ሰ​ለ​ትም አስ​ረው ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ዱት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ በይ​ሁዳ ንጉሥ ፊት በተ​ነ​በ​በው መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን ቃላት ሁሉ፥ ማለት ክፉ ነገ​ርን አመ​ጣ​ለሁ፥


አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም የሰ​ማ​ይን አም​ላክ ከአ​ስ​ቈጡ በኋላ በከ​ለ​ዳ​ዊው በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ እር​ሱም ይህን ቤት አፈ​ረሰ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ባቢ​ሎን አፈ​ለሰ።


ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ዘመን ጀም​ረን እስከ ዛሬ ድረስ እጅግ በድ​ለ​ናል፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን እኛና ልጆ​ቻ​ችን ንጉ​ሦ​ቻ​ችን፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም ለሰ​ይ​ፍና ለም​ርኮ፥ ለብ​ዝ​በ​ዛና ለዕ​ፍ​ረት በአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት እጅ ተጣ​ልን፤ እስከ ዛሬም ድረስ በፊ​ታ​ችን እፍ​ረት እን​ኖ​ራ​ለን።


ዮሴ​ፍን እንደ መንጋ የም​ት​መራ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድ​ምጥ፤ በኪ​ሩ​ቤል ላይ የም​ት​ቀ​መጥ፥ ተገ​ለጥ።


ፍላ​ጾ​ቻ​ቸ​ውም ጐበ​ዞ​ችን ይጨ​ፈ​ጭ​ፋሉ፤ ሕፃ​ኖ​ቻ​ች​ሁ​ንም አይ​ም​ሩም፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ለል​ጆ​ቻ​ችሁ አይ​ራ​ሩም።


አለ​ቆች መቅ​ደ​ሴን አረ​ከሱ፤ ስለ​ዚ​ህም ያዕ​ቆ​ብን ለጥ​ፋት፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ለው​ር​ደት ሰጠሁ።


በሕ​ዝቤ ላይ ተቈ​ጥቼ ነበር፤ ርስ​ቴ​ንም አረ​ከ​ስሽ፤ በእ​ጅ​ሽም አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸው አል​ራ​ራ​ሽም፤ ቀን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም እጅግ አክ​ብ​ደ​ሻል።


ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በመ​ዓት እጐ​በ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቶ​ቻ​ቸው በሰ​ይፍ ይሞ​ታሉ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በራብ ይሞ​ታሉ፤


ታላ​ላ​ቆ​ችና ታና​ና​ሾች በዚች ምድር ይሞ​ታሉ ፥ አይ​ቀ​በ​ሩም ሰዎ​ችም አያ​ለ​ቅ​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ ስለ እነ​ር​ሱም ፊት አይ​ነ​ጩ​ላ​ቸ​ውም፤ ራስ​ንም አይ​ላ​ጩ​ላ​ቸ​ውም፤


ስለ​ዚህ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለራብ ስጥ፤ ለሰ​ይ​ፍም እጅ አሳ​ል​ፈህ ስጣ​ቸው፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የወ​ላድ መካ​ንና መበ​ለ​ቶች ይሁኑ፤ ወን​ዶ​ቻ​ቸ​ውም በሞት ይጥፉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም በጦ​ር​ነት ጊዜ በሰ​ይፍ ይመቱ።


የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ የመ​ል​ክ​ያን ልጅ ጳስ​ኮ​ር​ንና የካ​ህ​ኑን የመ​ዕ​ሴ​ይን ልጅ ሶፎ​ን​ያ​ስን ወደ ኤር​ም​ያስ በላከ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ እን​ዲ​ህም አለ፦


ከዚህ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ ከቸ​ነ​ፈ​ርና ከሰ​ይፍ፥ ከራ​ብም በዚ​ህች ከተማ የቀ​ሩ​ትን ሕዝ​ቡ​ንም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም በሚ​ሹት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም በሰ​ይፍ ስለት ይመ​ታ​ቸ​ዋል፤ አያ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ም​ራ​ቸ​ውም።”


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ይችን ከተማ ለከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅና ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እር​ሱም ይይ​ዛ​ታል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ሕዝብ ላይ እን​ዳ​መ​ጣሁ፥ እን​ዲሁ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ላ​ቸ​ውን በጎ​ነት ሁሉ አመ​ጣ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው አደ​ረገ፤ እር​ሱን በድ​ላ​ች​ኋ​ልና፥ ቃሉ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምና ይህ ነገር ሆነ​ባ​ችሁ።


በአ​ን​ቺም ወን​ድና ሴትን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንና ብላ​ቴ​ና​ውን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም ጐል​ማ​ሳ​ው​ንና ቆን​ጆ​ዪ​ቱን እበ​ት​ና​ለሁ፤


ሕፃ​ና​ቱ​ንም በመ​ን​ገድ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቹ​ንም በአ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ቻ​ችን ያጠፋ ዘንድ ሞት በመ​ስ​ኮ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ሀገ​ራ​ችን ገብ​ቶ​አ​ልና።


ብዙ ሕዝ​ብን ይሰ​በ​ሰ​ቡ​ብ​ሻል፤ በድ​ን​ጋ​ይም ይወ​ግ​ሩ​ሻል፤ በሰ​ይ​ፋ​ቸ​ውም ይወ​ጉ​ሻል።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሞን ልጆ​ችና ስለ ስድ​ባ​ቸው እን​ዲህ ይላል ብለህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ሰይፍ ሰይፍ ለመ​ግ​ደል ተመ​ዝ​ዞ​አል፤ ጨር​ሶም ያርድ ዘንድ ተሰ​ን​ግ​ሎ​አል በል።


ለባሪያዎቼስ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? እነርሱም ተመልሰው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ያደርግብን ዘንድ እንዳሰበ እንዲሁ አድርጎብናል አሉ።


ፈጽ​መህ እን​ደ​ም​ት​ጠፋ እኔ ዛሬ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ረህ ትወ​ር​ሳት ዘንድ በም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር ዘመ​ንህ አይ​ረ​ዝ​ምም።


跟着我们:

广告


广告