Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 35:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ኢዮ​ስ​ያስ ግን ይዋ​ጋው ዘንድ ተጽ​ናና እንጂ ፊቱን ከእ​ርሱ አል​መ​ለ​ሰም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አፍ የተ​ነ​ገ​ረ​ውን የኒ​ካ​ዑን ቃል አል​ሰ​ማም፤ በመ​ጊ​ዶ​ንም ሸለቆ ይዋጋ ዘንድ መጣ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ኢዮስያስ ግን ሌላ ሰው መስሎ በጦርነት ሊገጥመው ወጣ እንጂ ወደ ኋላ አልተመለሰም፤ በመጊዶ ሜዳ ላይ ሊዋጋው ሄደ እንጂ፣ ኒካዑ ከእግዚአብሔር ታዝዞ የነገረውን ሊሰማ አልፈለገም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ኢዮስያስ ግን ማንነቱን ሸሽጎ ለመዋጋት ወጣ እንጂ ፊቱን ከእርሱ አልመለሰም፤ በጌታም አፍ የተነገረውን የኒካዑን ቃል አልሰማም፥ በመጊዶም ሸለቆ ለመዋጋት መጣ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ኢዮስያስ ግን ጦርነት ለመግጠም ቊርጥ ውሳኔ አደረገ፤ እግዚአብሔር በንጉሥ ኒካዑ አማካይነት የተናገረውንም ሊሰማ አልፈለገም፤ ልብሰ መንግሥቱን ለውጦ ሌላ ሰው በመምሰል በመጊዶ ወደሚገኘው ሜዳ ሊዋጋ ሄደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ኢዮስያስ ግን ይዋጋው ዘንድ ተጸናና እንጂ ፊቱን ከእርሱ አልመለሰም፤ በእግዚአብሔርም አፍ የተነገረውን የኒካዑን ቃል አልሰማም፥ በመጊዶም ሸለቆ ይዋጋ ዘንድ መጣ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 35:22
16 交叉引用  

ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስቱ ሐኖ​ንን፥ “ተነሺ፥ ራስ​ሽን ለውጪ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስት እንደ ሆንሽ ማንም አይ​ወቅ፤ ወደ ሴሎም ሂጂ፤ ስለ​ዚ​ህም ሕፃን ከደ​ዌው ይድን እን​ደ​ሆነ ጠይቂ፤ እነሆ፥ በዚህ ሕዝብ ላይ እን​ደ​ም​ነ​ግሥ የነ​ገ​ረኝ ነቢዩ አኪያ በዚያ አለ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ልብ​ሴን ለውጬ ወደ ሰልፍ እገ​ባ​ለሁ፤ አንተ ግን የእ​ኔን ልብስ ልበስ” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ልብ​ሱን ለውጦ ወደ ሰልፍ ገባ።


አንድ ሰውም ቀስ​ቱን ድን​ገት ገትሮ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ በሳ​ን​ባ​ውና በደ​ረቱ መካ​ከል ወጋው፤ ሰረ​ገ​ለ​ኛ​ው​ንም፥ “መል​ሰህ ንዳ፤ ተወ​ግ​ቻ​ለ​ሁና ከሰ​ልፍ ውስጥ አው​ጣኝ” አለው።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም በድ​ኑን በሰ​ረ​ገ​ላው አድ​ር​ገው ከመ​ጊዶ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጡት፤ በመ​ቃ​ብ​ሩም ቀበ​ሩት። የሀ​ገ​ሩም ሰዎች የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ዮአ​ክ​ስን ወሰ​ዱት። ቀብ​ተ​ውም በአ​ባቱ ፋንታ አነ​ገ​ሡት።


የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ያን ባየ ጊዜ በአ​ት​ክ​ልት ቤት መን​ገድ ሸሸ። ኢዩም፥ “እር​ሱ​ንም ደግሞ አል​ተ​ወ​ውም” ብሎ ተከ​ተ​ለው። በይ​ብ​ላ​ሄ​ምም አቅ​ራ​ቢያ ባለ​ችው በጋይ አቀ​በት በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ወጋው። ወደ መጊ​ዶም ሸሸ፥ በዚ​ያም ሞተ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ልብ​ሴን ለውጬ ወደ ጦር​ነት እገ​ባ​ለሁ፤ አንተ ግን የእ​ኔን ልብስ ልበስ” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ልብ​ሱን ለወጠ፤ ወደ ሰል​ፍም ገባ።


እር​ሱም፥ “የይ​ሁዳ ንጉሥ ሆይ፥ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? በም​ዋ​ጋ​በት በሌላ ቤት ላይ ነው እንጂ በአ​ንተ ላይ ዛሬ አል​መ​ጣ​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ድ​ቸ​ኩል አዝ​ዞ​ኛል፤ ከእኔ ጋር ያለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋህ ተጠ​ን​ቀቅ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ​በት።


ቀስ​ተ​ኞ​ቹም ንጉ​ሡን ኢዮ​ስ​ያ​ስን ወጉት፤ ንጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “እጅግ ቈስ​ያ​ለ​ሁና ከሰ​ልፉ ውስጥ አው​ጡኝ” አላ​ቸው።


በአ​ባ​ትህ ዝግባ አዳ​ራሽ ስለ ሠራህ በውኑ ትነ​ግ​ሣ​ለ​ህን? በውኑ አባ​ትህ አይ​በ​ላና አይ​ጠ​ጣም ነበ​ርን? ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅ​ንስ አያ​ደ​ር​ግም ነበ​ርን? በዚ​ያም ጊዜ መል​ካም ሆኖ​ለት ነበር።


በዚያ ቀን በመጊዶን ሜዳ እንደ ነበረው እንደ ሐዳድሪሞን ልቅሶ ታላቅ ልቅሶ በኢየሩሳሌም ይሆናል።


በይ​ሳ​ኮ​ርና በአ​ሴር መካ​ከል ቤት​ሳ​ንና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ዶርና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ መጌ​ዶና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ የመ​ፌታ ሦስ​ተኛ እጅና መን​ደ​ሮ​ችዋ ለም​ናሴ ነበሩ።


አለ​ቆ​ችም ከስ​ን​ቃ​ቸው ወሰዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ጠ​የ​ቁም።


በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው።


ነገ​ሥ​ታት መጡ፤ ተዋ​ጉም፤ በዚያ ጊዜ በመ​ጌዶ ውኆች አጠ​ገብ በቶ​ናሕ የከ​ነ​ዓን ነገ​ሥ​ታት ተዋጉ፤ በቅ​ሚ​ያም ብርን አል​ወ​ሰ​ዱም።


ሳኦ​ልም መል​ኩን ለውጦ፥ ሌላ ልብ​ስም ለብሶ ሄደ፤ ሁለ​ትም ሰዎች ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ፤ በሌ​ሊ​ትም ወደ ሴቲቱ መጡ። ሳኦ​ልም፥ “እባ​ክሽ በመ​ና​ፍ​ስት አም​ዋ​ር​ቺ​ልኝ፤ የም​ል​ሽ​ንም አስ​ነ​ሽ​ልኝ” አላት።


跟着我们:

广告


广告