2 ዜና መዋዕል 35:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 እርሱም፥ “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? በምዋጋበት በሌላ ቤት ላይ ነው እንጂ በአንተ ላይ ዛሬ አልመጣሁም፤ እግዚአብሔርም እንድቸኩል አዝዞኛል፤ ከእኔ ጋር ያለው እግዚአብሔር እንዳያጠፋህ ተጠንቀቅ” ብሎ መልእክተኞችን ላከበት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም21 ኒካዑ ግን መልእክተኛውን ልኮ፣ “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፤ አንተንና እኔን የሚያጣላን ምንድን ነው? ጦርነት ከገጠምሁት ቤት ጋራ እንጂ በአሁኑ ጊዜ አንተን የምወጋህ አይደለሁም፤ እግዚአብሔር እንድፈጥን አዝዞኛል፤ ስለዚህ ከእኔ ጋራ ያለውን እግዚአብሔርን መቃወምህን ተው፤ አለዚያ ያጠፋሃል” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ኒካዑም እንዲህ ብሎ መልእክተኞችን ላከበት፦ “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ! እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? ውግያ የማደርገው በሌላ ቤት ላይ ነው እንጂ በአንተ ላይ ዛሬ አልመጣሁም፤ ጌታም እንድቸኩል አዝዞኛል፤ ከእኔ ጋር ያለው ጌታ እንዳያጠፋህ ይህን በእርሱ ላይ ከማድረግ ተመለስ።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ኒካዑ ግን ለኢዮስያስ “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፥ እኔንና አንተን የሚያጣላን ምንም ነገር የለም፤ እኔ የመጣሁት ጠላቶቼን ለመውጋት እንጂ፥ አንተን ለመውጋት አይደለም፤ ጠላቶቼንም በፍጥነት እንድወጋ እግዚአብሔር አዞኛል፤ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ስለ ሆነ፥ ባትቃወመኝ ይሻልሃል፤ እምቢ ብትል ግን እግዚአብሔር ያጠፋሃል” የሚል መልእክት ላከበት፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 እርሱም “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለኝ? በምዋጋበት በሌላ ቤት ላይ ነው እንጂ በአንተ ላይ ዛሬ አልመጣሁም፤ እግዚአብሔርም እንድቸኵል አዝዞኛል፤ ከእኔ ጋር ያለው እግዚአብሔር እንዳያጠፋህ ይህን በእርሱ ላይ ከማድረግ ተመለስ” ብሎ መልእክተኞችን ላከበት። 参见章节 |