Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 35:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ከነ​ቢ​ዩም ከሳ​ሙ​ኤል ዘመን ጀምሮ እን​ደ​ዚህ ያለ ፋሲካ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ከቶ አል​ተ​ደ​ረ​ገም፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ኢዮ​ስ​ያ​ስና ካህ​ናቱ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በዚ​ያም የተ​ገኙ የይ​ሁ​ዳና የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖ​ሩት እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት ያለ ፋሲካ ያደ​ረገ የለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከነቢዩ ሳሙኤል ዘመን ጀምሮ እንዲህ ያለ ፋሲካ በእስራኤል ዘንድ ተከብሮ አያውቅም፤ ኢዮስያስ ከካህናቱ፣ ከሌዋውያኑ፣ ከመላው ይሁዳና ከእስራኤል፣ በዚያ ከነበሩትም ከኢየሩሳሌም ሰዎች ጋራ እንዳከበረው አድርጎ ያከበረ አንድም የእስራኤል ንጉሥ የለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከነቢዩ ከሳሙኤል ዘመን ጀምሮ እንደዚህ ያለ ፋሲካ በእስራኤል ዘንድ ከቶ ተከብሮ አያውቅም፤ ከእስራኤልም ነገሥታት ሁሉ ኢዮስያስና ካህናቱ፥ ሌዋውያኑም፥ በዚያም የተገኙ የይሁዳና የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩት እንዳከበሩት ያለ ፋሲካ ያከበረ የለም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከነቢዩ ሳሙኤል ዘመን ጀምሮ የፋሲካ በዓል ይህን በመሰለ ሁኔታ ከቶ ተከብሮ አያውቅም፤ ንጉሥ ኢዮስያስ፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የይሁዳ፥ የእስራኤልና የኢየሩሳሌም ሕዝብ የፋሲካን በዓል አሁን ባከበሩት ዐይነት ከዚህ በፊት ከነበሩት ነገሥታት መካከል፥ አንዱ እንኳ አክብሮ አያውቅም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ከነቢዩ ከሳሙኤል ዘመን ጀምሮ እንደዚህ ያለ ፋሲካ በእስራኤል ዘንድ ከቶ አልተደረገም፤ ከእስራኤልም ነገሥታት ሁሉ ኢዮስያስና ካህናቱ፥ ሌዋውያኑም፥ በዚያም የተገኙ የይሁዳና የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩት እንዳደረጉት ያለ ፋሲካ ያደረገ የለም።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 35:18
4 交叉引用  

እንደ ተጻ​ፈም ብዙ​ዎቹ አላ​ደ​ረ​ጉ​ትም ነበ​ርና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፋሲካ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያደ​ርጉ ዘንድ እን​ዲ​መጡ ከቤ​ር​ሳ​ቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ አዋጅ እን​ዲ​ነ​ገር ወሰኑ።


ይህም ፋሲካ ኢዮ​ስ​ያስ በነ​ገሠ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት ተደ​ረገ። 19 ‘ሀ’ ንጉሡ ኢዮ​ስ​ያስ ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ባገ​ኘው መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን ቃላት ሁሉ ለመ​ጠ​በቅ አስ​ማ​ተ​ኞ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን፥ ሟር​ተ​ኞ​ች​ንና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምድ​ርና በይ​ሁዳ የሚ​ገ​ኙ​ትን ምስ​ሎ​ችና ቃሪ​ያ​ሲም የተ​ባሉ ጣዖ​ታ​ትን በእ​ሳት አቃ​ጠለ። 19 ‘ለ’ እንደ ሙሴ ሕግ ሁሉ በፍ​ጹም ልቡ፥ በፍ​ጹም ነፍሱ፥ በፍ​ጹም ኀይሉ ከእ​ርሱ በፊት ከነ​በ​ሩት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ለሰ የሚ​መ​ስ​ለው ሰው አል​ነ​በ​ረም። ከእ​ር​ሱም በኋላ የሚ​መ​ስ​ለው አል​ተ​ነ​ሣም። 19 ‘ሐ’ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉሥ ምናሴ በይ​ሁዳ ላይ በአ​ደ​ረ​ገ​ውና በአ​ነ​ሣ​ሣው ጥፋት ሁሉ ከአ​ስ​ከ​ተ​ለው ታላቅ ቍጣ አል​ተ​መ​ለ​ሰም። 19 ‘መ’ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን እን​ዳ​ራ​ቅሁ ይሁ​ዳን ከፊቴ አር​ቃ​ለሁ። የመ​ረ​ጥ​ኋ​ት​ንም ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና ስሜ በዚያ ይጠ​ራ​በ​ታል ያል​ሁ​ትን ቤት እጥ​ላ​ለሁ።”


跟着我们:

广告


广告