2 ዜና መዋዕል 35:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 የአሳፍም ልጆች መዘምራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሳፍም፥ እንደ ኤማንም የንጉሡም ባለ ራእይ እንደ ነበረው እንደ ኤዶትም ትእዛዝ በየስፍራቸው ነበሩ፤ በረኞቹም በሮቹን ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ያዘጋጁላቸው ነበርና ከአገልግሎታቸው ይርቁ ዘንድ አያስፈልጋቸውም ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 መዘምራኑ የአሳፍ ዘሮች በዳዊት፣ በአሳፍ፣ በኤማንና በንጉሡ ባለራእይ በኤዶታም በተሰጠው መመሪያ መሠረት በቦታቸው ነበሩ። በእያንዳንዱ በር ላይ የነበሩት በር ጠባቂዎችም ሌዋውያን ወገኖቻቸው ስላዘጋጁላቸው፣ ከጥበቃ ቦታቸው መለየት አያስፈልጋቸውም ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 የአሳፍም ልጆች መዘምራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሣፍም እንደ ኤማንም የንጉሡም ባለ ራእይ እንደነበረው እንደ ኤዶታም ትእዛዝ በየስፍራቸው ነበሩ፤ የደጁም ጠባቂዎች በሮቹን ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ያዘጋጁላቸው ነበርና ከአገልግሎታቸው እንዲርቁ አያስፈልጋቸውም ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ከዚህ በታች ስማቸው የተመለከተው የሌዋዊው የአሳፍ ጐሣ የሆኑ መዘምራንም ንጉሥ ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት፥ በተመደበላቸው ስፍራ ነበሩ፤ እነርሱም አሳፍ፥ ሄማንና የንጉሡ ነቢይ ይዱታን ናቸው፤ ሌሎች ሌዋውያን የፋሲካውን መሥዋዕት ያዘጋጁላቸው ስለ ነበር፥ የቤተ መቅደሱ ዘብ ጠባቂዎች ስፍራቸውን አይተዉም ነበር፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 የአሳፍም ልጆች መዘምራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሣፍ፥ እንደ ኤማን፥ የንጉሡም ባለ ራእይ እንደ ነበረው እንደ ኤዶታም ትእዛዝ በየስፍራቸው ነበሩ፤ በረኞቹም በሮቹን ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ያዘጋጁላቸው ነበርና ከአገልግሎታቸው ይርቁ ዘንድ አያስፈልጋቸውም ነበር። 参见章节 |