2 ዜና መዋዕል 34:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 በኢየሩሳሌምና በብንያምም ሀገር የተገኙትን ሁሉ በዚህ ነገር አማለ። በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ እንደ አባቶቻቸው አምላክ እንደ እግዚአብሔር ቤት ቃል ኪዳን አደረጉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም32 ከዚህ በኋላ በኢየሩሳሌምና በብንያም የሚኖረው ሁሉ በዚህ ነገር ቃል እንዲገባ አደረገ፤ የኢየሩሳሌምም ሕዝብ የአባቶቹ አምላክ ባዘዘው የአምላክ ቃል ኪዳን መሠረት ፈጸሙ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 በኢየሩሳሌምና በብንያምም የተገኙትን ሁሉ በዚህ ነገር አማለ፤ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩት የአባቶቻቸው አምላክ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን እንደሚያዝዘው አደረጉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 ከዚህ በኋላ መላው የብንያም ሕዝብና በኢየሩሳሌም የተገኙ ሌሎች ሰዎች ሁሉ ቃል ኪዳኑን ይጠብቁ ዘንድ ቃል እንዲገቡ አደረገ፤ በዚህም መሠረት የኢየሩሳሌም ሕዝብ ከቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር የገቡት ቃል ኪዳን የሚጠይቀውን ግዴታ ሁሉ ፈጸሙ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 በኢየሩሳሌምና በብንያምም የተገኙትን ሁሉ በዚህ ነገር አማለ፤ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩት የአባቶቻቸው አምላክ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን እንዳዘዘ አደረጉ። 参见章节 |