Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 34:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ኢዮ​ስ​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የስ​ም​ንት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ኢዮስያስ በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሠላሳ አንድ ዓመት ገዛ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ኢዮስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የስምንት ዓመት ልጅ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ኢዮስያስ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ስምንት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሠላሳ አንድ ዓመት ገዛ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ኢዮስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የስምንት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 34:1
18 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ፥ “መሠ​ዊያ ሆይ፥ መሠ​ዊያ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ኢዮ​ስ​ያስ የሚ​ባል ልጅ ለዳ​ዊት ቤት ይወ​ለ​ዳል፤ ዕጣ​ንም የሚ​ያ​ጥ​ኑ​ብ​ህን የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹን ካህ​ናት ይሠ​ዋ​ብ​ሃል፤ የሰ​ዎ​ቹ​ንም አጥ​ንት ያቃ​ጥ​ል​ብ​ሃል” ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ጠራ።


ንጉ​ሡም ላከ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ወደ እርሱ ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።


ኢዮ​አ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሰ​ባት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አርባ ዓመት ነገሠ፤ እናቱ ሳብያ የተ​ባ​ለች የቤ​ር​ሳ​ቤህ ሴት ነበ​ረች።


የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ሁሉ የዐ​ሥራ ስድ​ስት ዓመት ጐል​ማሳ የነ​በ​ረ​ውን ዖዝ​ያ​ንን ወስ​ደው በአ​ባቱ በአ​ሜ​ስ​ያስ ፋንታ አነ​ገ​ሡት።


ምና​ሴም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የዐ​ሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አምሳ አም​ስት ዓመት ነገሠ።


ለዘ​ለ​ዓ​ለም ክፋ​ቴን አት​መ​ል​ከ​ት​ብኝ፤ በም​ድር ጥል​ቀ​ትም አት​በ​ቀ​ለኝ፤ አቤቱ፥ በን​ስሓ ለሚ​መ​ለሱ ሰዎች፥ አም​ላ​ካ​ቸው አንተ ነህና፥ ቸር​ነ​ትህ በእኔ ላይ ይገ​ለጥ፤ መዳን የማ​ይ​ገ​ባኝ ሲሆን በይ​ቅ​ር​ታህ ብዛት አዳ​ን​ኸኝ።


ድሃና ጠቢብ ብላ​ቴና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ተግ​ሣ​ጽን መቀ​በል ከማ​ያ​ውቅ ከሰ​ነፍ ሽማ​ግሌ ንጉሥ ይሻ​ላል።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በአ​ሞጽ ልጅ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመን በመ​ን​ግ​ሥቱ በዐ​ሥራ ሦስ​ተ​ኛው ዓመት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል መጣ​ለት።


“ከይ​ሁዳ ንጉሥ ከአ​ሞጽ ልጅ ከኢ​ዮ​ስ​ያስ ከዐ​ሥራ ሦስ​ተ​ኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእ​ነ​ዚህ በሃያ ሦስቱ ዓመ​ታት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እኔም ማልጄ ተነ​ሥቼ ተና​ገ​ር​ኋ​ችሁ፤ ነገር ግን አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በን​ጉሡ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመን እን​ዲህ አለኝ፥ “ከዳ​ተ​ኛ​ዪቱ እስ​ራ​ኤል ያደ​ረ​ገ​ች​ውን አየ​ህን? ወደ ረዘ​መው ተራራ ሁሉ፥ ወደ ለመ​ለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች፤ በዚ​ያም አመ​ነ​ዘ​ረች።


በይሁዳ ንጉሥ በአሞጽ ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ ወደ አማርያ ልጅ ወደ ጎዶልያስ ልጅ ወደ ኵሲ ልጅ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።


አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት፤ ሌላም አምስት አተረፈ፤


ሳሙ​ኤል ግን ገና ብላ​ቴና ሳለ የበ​ፍታ ኤፉድ ታጥቆ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያገ​ለ​ግል ነበር።


ብላ​ቴ​ናው ሳሙ​ኤ​ልም አደገ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ውም ፊት ሞገስ እያ​ገኘ ሄደ።


跟着我们:

广告


广告