Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 33:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ው​ንም ሁሉ፥ በሙሴ የተ​ሰ​ጠ​ውን ሕግና ሥር​ዐት ፍር​ድ​ንም ሁሉ ቢያ​ደ​ርጉ ቢጠ​ብ​ቁም፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ከሰ​ጠ​ኋት ምድር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን እግር እንደ ገና አላ​ር​ቅም” ባለ​በት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ የሠ​ራ​ውን ጣዖ​ትና የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል አቆመ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በሙሴ አማካይነት ያዘዝኋቸውን ሕጎቼን፣ ደንቦቼንና ሥርዐቶቼን ሁሉ በጥንቃቄ ይፈጽሙ እንጂ፣ ከእንግዲህ የእስራኤላውያን እግር ለአባቶቻችሁ ከሰጠኋቸው ምድር ለቅቆ እንዲወጣ አላደርግም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እንዲሁም ጌታ ለዳዊትና ለልጁ ለሰለሞን፦ “እኔ ያዘዝኋቸውን ሁሉ፥ በሙሴም በኩል የተሰጠውን ሕግና ሥርዓት ፍርድንም ሁሉ ቢያደርጉ ቢጠብቁም፥ ለአባቶቻችሁ ከሰጠኋት ምድር እስራኤል እንደገና እንዲሰደዱ አላደርግም” ብሎ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እስራኤላውያን በሙሴ አማካይነት ያዘዝኳቸውን ሕጌን፥ ሥርዓቴንና ድንጋጌዬን ሁሉ በጥንቃቄ ቢጠብቁ ለቀድሞ አባቶቻቸው ከሰጠኋቸው ምድር እንደገና እንዲፈናቀሉ አላደርግም።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 33:8
18 交叉引用  

ለሕ​ዝ​ቤም ለእ​ስ​ራ​ኤል ስፍራ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እተ​ክ​ላ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ብቻ​ቸ​ውን ይቀ​መ​ጣሉ፤ ከዚ​ያም በኋላ የሚ​ጠ​ራ​ጠ​ሩት የለም፤ እንደ ቀድ​ሞው ዘመን የኀ​ጢ​አት ልጅ መከራ አያ​ጸ​ና​ባ​ቸ​ውም።


ለሕ​ዝ​ቤም ለእ​ስ​ራ​ኤል ስፍራ አደ​ር​ግ​ለ​ታ​ለሁ፥ በዚ​ያም እተ​ክ​ለ​ዋ​ለሁ፥ በስ​ፍ​ራ​ውም ይቀ​መ​ጣል፤ ከዚ​ያም በኋላ አይ​ና​ወ​ጥም፤ የኀ​ጢ​አ​ትም ልጆች እንደ ቀድ​ሞው አያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ትም፤


ምና​ሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ካጠ​ፋ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ ይልቅ ክፉ ይሠሩ ዘንድ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን አሳተ።


ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ በሰ​ጠ​ኋ​ቸው ምድር በዚህ ስፍራ አሳ​ድ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ እጅ የነ​ገ​ራ​ቸ​ውን ሥር​ዐት ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ታስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።”


አሮ​ንና ልጆ​ቹም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ።


ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድ​ቃን ነበሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐ​ትና በት​እ​ዛ​ዙም ሁሉ ያለ ነውር የሚ​ሄዱ ነበሩ።


“የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ያደ​ርግ ዘንድ የማ​ያ​ጸና ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።


ለእ​ና​ንተ፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ መል​ካም ይሆን ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ዕድ​ሜ​አ​ችሁ ይረ​ዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን ጠብቁ።”


ሙሴም እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ጠርቶ አላ​ቸው፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ እን​ድ​ት​ማ​ሩ​አ​ትም፥ በማ​ድ​ረ​ግም እን​ድ​ት​ጠ​ብ​ቁ​አት ዛሬ በጆ​ሮ​አ​ችሁ የም​ና​ገ​ራ​ትን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ስሙ።


አንተ ግን በዚህ በእኔ ዘንድ ቁም፤ ርስት አድ​ርጌ በም​ሰ​ጣ​ቸው ምድር ላይ ያደ​ር​ጉ​አት ዘንድ የም​ታ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ውን ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን፥ ፍር​ዴ​ንም ሁሉ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።


“በሕ​ይ​ወት እን​ድ​ት​ኖሩ፥ እን​ድ​ት​በ​ዙም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ገብ​ታ​ችሁ እን​ድ​ት​ወ​ር​ሱ​አት፥ ዛሬ ለአ​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ።


跟着我们:

广告


广告