Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 32:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከሚ​ኖሩ ሰዎች ጋር ስለ ልቡ ኵራት ሰው​ነ​ቱን አዋ​ረደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ዘመን ቍጣ​ውን አላ​መ​ጣ​ባ​ቸ​ውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ይሁን እንጂ ሕዝቅያስና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ስለ ልባቸው ትዕቢት ራሳቸውን አዋረዱ፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በዘመነ መንግሥቱ አልመጣባቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሕዝቅያስም ከኢየሩሳሌም ሰዎች ጋር ስለ ልቡ ኩራት ራሱን አዋረደ፥ የጌታም ቁጣ በሕዝቅያስ ዘመን አልመጣባቸውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ይሁን እንጂ በመጨረሻ ሕዝቅያስና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በትሕትና ራሳቸውን ስላዋረዱ ሕዝቅያስ ከዚህ ዓለም በሞት እስከ ተለየበት ጊዜ ድረስ እግዚአብሔር ሕዝቡን አልቀጣም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ሕዝቅያስም ከኢየሩሳሌም ሰዎች ጋር ስለ ልቡ ኵራት ሰውነቱን አዋረደ፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ በሕዝቅያስ ዘመን አልመጣባቸውም።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 32:26
14 交叉引用  

እነ​ዚ​ህም የአ​ው​ራ​ጃ​ዎች አለ​ቆች ጐል​ማ​ሶች ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጡ፤ ሠራ​ዊ​ትም ተከ​ተ​ላ​ቸው።


እነ​ዚ​ህም በእ​ነ​ዚያ ትይዩ ሰባት ቀን ያህል ሰፈሩ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ተጋ​ጠሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከሶ​ር​ያ​ው​ያን በአ​ንድ ቀን መቶ ሺህ እግ​ረኛ ገደሉ።


ልብ​ህን አላ​ደ​ነ​ደ​ን​ህ​ምና፥ እነ​ር​ሱም ለጥ​ፋ​ትና ለመ​ር​ገም እን​ዲ​ሆኑ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሰም​ተህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ ልብ​ስ​ህን ቀድ​ደ​ሃ​ልና፥ በፊ​ቴም አል​ቅ​ሰ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተመ​ለ​ሱና እንደ ተፀ​ፀቱ ባየ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ “ከተ​መ​ለሱ አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ከጥ​ቂት ቀንም በኋላ አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አይ​ፈ​ስ​ስም” ሲል ወደ ሰማያ መጣ።


ለሕ​ዝ​ቅ​ያ​ስም እጅግ ብዙ ሀብ​ትና ክብር ነበ​ረው፤ ለብ​ርና ለወ​ር​ቅም፥ ለከ​በ​ረው ዕን​ቍና ለሽ​ቱው፥ ለጋ​ሻ​ውና ውድ ለሆ​ነው ዕቃ ሁሉ ግምጃ ቤቶ​ችን ሠራ።


በተ​ጨ​ነ​ቀም ጊዜ አም​ላ​ኩን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለገ፤ በአ​ባ​ቶ​ቹም አም​ላክ ፊት ሰው​ነ​ቱን እጅግ አዋ​ረደ።


አሁ​ንም አቤቱ፥ የጻ​ድ​ቃን አም​ላ​ካ​ቸው አንተ ነህ። ንስ​ሓን የፈ​ጠ​ርህ ለጻ​ድቅ ሰው አይ​ደ​ለ​ምና፥ አን​ተን ላል​በ​ደሉ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አይ​ደ​ለ​ምና፤ ነገር ግን የእ​ኔን የኃ​ጥ​ኡን ንስሓ ወደ ማየት ተመ​ለስ።


አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ፈጽሜ በደ​ልሁ፤ ኀጢ​አ​ቴ​ንም አም​ና​ለሁ።


በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ፤ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።


跟着我们:

广告


广告