Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 32:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ብዙ​ዎ​ቹም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ ይዘው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይመጡ ነበር፤ ለይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እጅ መንሻ ይሰጡ ነበር፤ እር​ሱም ከዚህ ነገር በኋላ በሕ​ዝብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ብዙዎችም ለእግዚአብሔር መባ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ለይሁዳ ንጉሥ ለሕዝቅያስም ውድ የሆኑ ገጸ በረከቶችን አመጡለት፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮም በአሕዛብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ብዙዎቹም ለጌታ መባ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም ይመጡ ነበር፥ ለይሁዳም ንጉሥ ለሕዝቅያስ እጅ መንሻ ይሰጡ ነበር፤ እርሱም ከዚህ ነገር በኋላ በአሕዛብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ብዙ ሰዎች ለእግዚአብሔር መባን፥ ለንጉሥ ሕዝቅያስ ደግሞ ገጸ በረከትን ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ሕዝቦች ሁሉ ሕዝቅያስን ከፍ ባለ አክብሮት ተመለከቱት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ብዙዎቹም ለእግዚአብሔር መባ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም ይመጡ ነበር፤ ለይሁዳም ንጉሥ ለሕዝቅያስ እጅ መንሻ ይሰጡ ነበር፤ እርሱም ከዚህ ነገር በኋላ በአሕዛብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 32:23
18 交叉引用  

ለን​ጉ​ሡም መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ እጅ​ግም ብዙ ሽቶ፥ የከ​በ​ረም ዕንቍ ሰጠ​ችው፤ የሳባ ንግ​ሥት ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን እንደ ሰጠ​ችው ያለ የሽቶ ብዛት ከዚያ ወዲያ አል​መ​ጣም ነበር።


እነ​ር​ሱም ሁሉ በዓ​መት በዓ​መቱ ገጸ በረ​ከ​ቱን፥ የብ​ርና የወ​ርቅ ዕቃ፥ ልብ​ስና የጦር መሣ​ሪያ፥ ሽቱም፥ ፈረ​ሶ​ችና በቅ​ሎ​ዎች እየ​ያዙ ይመጡ ነበር።


ሰሎ​ሞ​ንም ከወ​ንዙ ጀምሮ እስከ ግብፅ ምድር ዳርቻ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ድረስ በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር፤ ግብ​ርም ያመ​ጡ​ለት ነበር፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ሙሉ ለሰ​ሎ​ሞን ይገዙ ነበር።


የዳ​ነው የይ​ሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰ​ድ​ዳል፤ ወደ ላይም ያፈ​ራል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት እጅግ አገ​ነ​ነው፤ ከእ​ርሱ በፊ​ትም ለነ​በ​ሩት ነገ​ሥ​ታት ያል​ሆ​ነ​ውን የመ​ን​ግ​ሥት ክብር ሰጠው።


የዳ​ዊት ልጅ ሰሎ​ሞ​ንም በመ​ን​ግ​ሥቱ በረታ፤ አም​ላ​ኩም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ እጅ​ግም አከ​በ​ረው፤ አገ​ነ​ነ​ውም።


ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ለኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ እጅ መን​ሻና የብር ግብር ያመጡ ነበር፤ ዐረ​ባ​ው​ያ​ንም ደግሞ ከመ​ን​ጎ​ቻ​ቸው ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በጎ​ች​ንና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየ​ሎ​ችን ያመ​ጡ​ለት ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥ​ቱን በእጁ አጸና፤ ይሁ​ዳም ሁሉ እጅ መንሻ ለኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ አመጣ፤ እጅ​ግም ብዙ ብል​ጥ​ግ​ናና ክብር ሆነ​ለት።


ከእ​ነ​ር​ሱም እያ​ን​ዳ​ንዱ ገጸ በረ​ከ​ቱን፥ የወ​ር​ቅ​ንና የብ​ርን ዕቃ፥ ልብ​ስ​ንና የጦር መሣ​ሪ​ያን፥ ሽቱ​ው​ንም፥ ፈረ​ሶ​ች​ንና በቅ​ሎ​ዎ​ችን እየ​ያዘ በየ​ዓ​መቱ ያመጣ ነበር።


ያባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ያከ​ብር ዘንድ ይህን ነገር በን​ጉሡ ልብ ያኖረ፥


እኔ ድሃና ቍስ​ለኛ ነኝ፤ የፊቴ፥ መድ​ኀ​ኒት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቀ​በ​ለኝ።


ስለ​ዚህ ሕዝቤ ወደ​ዚህ ይመ​ለ​ሳሉ፤ ፍጹም ጊዜም በላ​ያ​ቸው ይገ​ኛል፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ አስ​ታ​ወ​ስሁ፤ የቀ​ደ​መ​ውን ተአ​ም​ራ​ት​ህን አስ​ታ​ው​ሳ​ለ​ሁና፤


ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።


跟着我们:

广告


广告