Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 31:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሕዝ​ቅ​ያ​ስና አለ​ቆ​ቹም መጥ​ተው ክም​ሩን ባዩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ። ሕዝ​ቡን እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ባረኩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሕዝቅያስና ሹማምቱም መጥተው ክምሩን ባዩ ጊዜ፣ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ሕዝቡን እስራኤልንም ባረኩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሕዝቅያስና ሹማምንቱም መጥተው ክምሩን ባዩ ጊዜ ጌታንና ሕዝቡን እስራኤልን ባረኩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ንጉሥ ሕዝቅያስና ባለሟሎቹ የሆኑት ባለሥልጣኖች መጥተው፥ እጅግ የበዛውን የስጦታ ክምር ባዩ ጊዜ፥ እግዚአብሔርንና የእርሱ ወገኖች የሆኑትን የእስራኤልን ሕዝብ አመሰገኑ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሕዝቅያስና አለቆቹም መጥተው ክምሩን ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን ባረኩ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 31:8
20 交叉引用  

ዳዊ​ትም የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕት ማሳ​ረ​ግን ከፈ​ጸመ በኋላ ሕዝ​ቡን በሰ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም መረቀ።


ቆሞም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጉባኤ ሁሉ በታ​ላቅ ድምፅ ሲመ​ርቅ እን​ዲህ አለ፦


ሕዝ​ቡም ፈቅ​ደው ሰጥ​ተ​ዋ​ልና፥ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አቅ​ር​በ​ዋ​ልና ደስ አላ​ቸው፤ ንጉ​ሡም ዳዊት ደግሞ ታላቅ ደስታ ደስ አለው።


በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ወር መከ​መር ጀመሩ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ጨረሱ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ካህ​ና​ቱ​ንና ሌዋ​ው​ያ​ኑን ስለ ክምሩ ጠየቀ።


ንጉሡ ሰሎ​ሞ​ንም ፊቱን መልሶ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጉባኤ ሁሉ መረቀ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጉባኤ ሁሉ ቆመው ነበር።


ያባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ያከ​ብር ዘንድ ይህን ነገር በን​ጉሡ ልብ ያኖረ፥


የሰው ሁሉ ዐይን አን​ተን ተስፋ ያደ​ር​ጋል፤ አን​ተም ምግ​ባ​ቸ​ውን በየ​ጊ​ዜው ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።


ሕይ​ወ​ትን የሚ​ፈ​ቅድ ሰው ማን ነው? በጎ ዘመ​ን​ንም ለማ​የት የሚ​ወ​ድድ ማን ነው?


በቲቶ ልብ ስለ እና​ንተ ያን መት​ጋት የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ነው።


በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ በሰ​ማ​ያዊ ስፍራ በመ​ን​ፈ​ሳዊ በረ​ከት ሁሉ የባ​ረ​ከን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


እስ​ራ​ኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን​ነው? እርሱ ያጸ​ን​ሃል፤ ይረ​ዳ​ሃ​ልም፤ ትም​ክ​ሕ​ትህ በሰ​ይ​ፍህ ነው፤ ጠላ​ቶ​ችህ ውሸ​ታ​ሞች ናቸው፤ አን​ተም በአ​ን​ገ​ታ​ቸው ላይ ትጫ​ና​ለህ።”


በጌ​ታ​ችን እጅግ ደስ አለኝ፤ ቢሳ​ና​ችሁ እንኳ አሁ​ንም እን​ደ​ም​ታ​ስ​ቡ​ልኝ፥ ከዱሮ ጀምሮ ለእኔ ችግር ታስቡ፥ ትተ​ጉም ነበ​ርና።


ፈጣ​ሪዬ እንደ ባለ​ጸ​ግ​ነቱ መጠን፥ በክ​ብር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የም​ት​ሹ​ትን ሁሉ ይፈ​ጽ​ም​ላ​ች​ኋል።


ፊታችሁን ልናይ በእምነታችሁም የጎደለውን ልንሞላበት ሌሊትና ቀን ከመጠን ይልቅ እየጸለይን በአምላካችን ፊት ከእናንተ የተነሣ ስለምንደሰተው ደስታ ሁሉ ለእግዚአብሔር በእናንተ ምክንያት ምን ያህል ምስጋና እናስረክብ ዘንድ እንችላለን?


ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኀይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።


ልቤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ወደ ታዘ​ዘው ትእ​ዛዝ ነው፤ እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ኀያ​ላን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት።


跟着我们:

广告


广告