Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 31:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የሌ​ዋ​ዊ​ውም የይ​ም​ላእ ልጅ የም​ሥ​ራቁ ደጅ በረኛ ቆሬ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መባና የተ​ቀ​ደ​ሱ​ትን ነገ​ሮች እን​ዲ​ያ​ካ​ፍል ሕዝቡ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ቀ​ረ​ቡት ላይ ተሾመ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የምሥራቁ በር ጠባቂ የሆነው የሌዋዊው የዪምና ልጅ ቆሬ ደግሞ ለእግዚአብሔር በቀረበው የበጎ ፈቃድ ስጦታ ላይ የእግዚአብሔርን መባና የተቀደሱትንም ነገሮች ለማከፋፈል፣ ኀላፊ ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የሌዋዊውም የይምና ልጅ የምሥራቁ ደጅ ጠባቂ ቆሬ የጌታን መባና የተቀደሱትን ነገሮች እንዲያከፋፍል ሕዝቡ ለጌታ በፈቃድ ባቀረቡት መባ ላይ ተሾመ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የቤተ መቅደሱ የምሥራቃዊ በር ዘብ ጠባቂዎች አለቃ ለነበረው ለሌዋዊው ዩምና ልጅ ለቆሬ ደግሞ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን የበጎ ፈቃድ ስጦታዎች ሁሉ የመቀበልና የማከፋፈል ኀላፊነት ተሰጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የሌዋዊውም የይምና ልጅ የምሥራቁ ደጅ በረኛ ቆሬ የእግዚአብሔርን መባና የተቀደሱትን ነገሮች እንዲያካፍል ሕዝቡ ለእግዚአብሔር በፈቃድ ባቀረቡት ላይ ተሾመ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 31:14
22 交叉引用  

የአ​ሴ​ርም ልጆች፤ ኢያ​ምን፥ ኢያሱ፥ኢዩል፥ በሪዓ፥ እኅ​ታ​ቸው ሳራ፤ የበ​ሪዓ ልጆ​ችም፤ ኮቦር፥ መል​ኪ​ኤል።


እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሆነው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ የበ​ረ​ኞች አለ​ቆች በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው የሚ​ጠ​ብቁ እነ​ዚህ ነበሩ።


የም​ሥ​ራ​ቁም በር ዕጣ ለሰ​ሌ​ም​ያና ለዘ​ካ​ርያ ወደቀ። የዮ​አ​ስም ልጆች ለም​ል​ክያ ዕጣ ጣሉ፤ ዕጣ​ውም በሰ​ሜን በኩል ወጣ።


በም​ሥ​ራቅ በኩል ለየ​ዕ​ለቱ ስድ​ስት፥ በሰ​ሜን በኩል ለየ​ዕ​ለቱ አራት፥ በደ​ቡብ በኩል ለየ​ዕ​ለቱ አራት፥ ለዕቃ ቤትም ሁለት ሁለት ነበሩ።


ንጉ​ሡም ሕዝ​ቅ​ያ​ስና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አለቃ ዓዛ​ር​ያስ እንደ አዘዙ ኢዮ​ኤል፥ ዓዛ​ዝያ፥ አና​ኤት፥ ኡሳ​ሄል፥ ኢያ​ሪ​ሞት፥ ኢዮ​ዛ​ብድ፥ ኤል​ሄል፥ ሰማ​ኪያ፥ መሐት፥ በና​ያ​ስና ልጆቹ፥ ከኮ​ክ​ን​ያ​ስና ከወ​ን​ድሙ ከሰ​ሜኢ እጅ በታች ተቈ​ጣ​ጣ​ሪ​ዎች ነበሩ።


በካ​ህ​ና​ቱም ከተ​ሞች ለታ​ላ​ላ​ቆ​ችና ለታ​ና​ና​ሾች ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ክፍ​ላ​ቸ​ውን በእ​ም​ነት ይሰጡ ዘንድ ኤዶም፥ ብን​ያስ፥ ኢያሱ፥ ሴሚ፥ አማ​ርያ፥ ኮክ​ን​ያስ ከእጁ በታች ነበሩ።


በስ​ደት በሚ​ኖ​ር​ባ​ቸው ከተ​ሞች ሁሉ ለቀ​ረው ሰው ሁሉ የሀ​ገሩ ሰዎች በብ​ርና በወ​ርቅ፥ በዕ​ቃም፥ በእ​ን​ስ​ሳም ይር​ዱት፤ ይህም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላለው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ሌላ ይሁን።”


ከዚ​ያም በኋላ ዘወ​ትር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የመ​ባ​ቻ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የተ​ቀ​ደ​ሱ​ት​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት ሁሉ መሥ​ዋ​ዕት፥ ሰውም ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃድ የሰ​ጠ​ውን ቍር​ባን አቀ​ረቡ።


በባ​ቢ​ሎ​ንም አው​ራጃ ሁሉ የም​ታ​ገ​ኘ​ውን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ ሕዝ​ቡና ካህ​ና​ቱም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላለው ለአ​ም​ላ​ካ​ቸው ቤት በፈ​ቃ​ዳ​ቸው የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​ትን ትወ​ስድ ዘንድ አዝ​ዘ​ዋል፤


በዕቃ ቤቶ​ችም ላይ ካህ​ኑን ሰሌ​ም​ያን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳዶ​ቅን፥ ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም ፈዳ​ያን ሾምሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የመ​ታ​ንያ ልጅ የዘ​ኩር ልጅ ሐናን ነበረ፤ እነ​ር​ሱም የታ​መኑ ሆነው ተገኙ፤ ሥራ​ቸ​ውም ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ማከ​ፋ​ፈል ነበረ።


ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም የተ​ረ​ፈው ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ይሆ​ናል፤ ይህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የተ​ረፈ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


“ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ወይም ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ከሚ​ቀ​መ​ጡት እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው ስእ​ለ​ቱን ሁሉ፥ በፈ​ቃ​ዱም የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን ሁሉ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን ቍር​ባን ቢያ​ቀ​ርብ፥


እነ​ዚ​ህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በ​ታት ሌላ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ት​ሰ​ጡት ከስ​ጦ​ታ​ችሁ ሌላ፥ ከስ​እ​ለ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ ሌላ፥ በፈ​ቃ​ዳ​ች​ሁም ከም​ታ​ቀ​ር​ቡ​አ​ቸው ሁሉ ሌላ ናቸው።


“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ለየ እርም የሆነ ነገር ሁሉ፥ ሰው ቢሆን ወይም እን​ስሳ ወይም የር​ስቱ እርሻ ቢሆን፥ አይ​ሸ​ጥም፤ አይ​ቤ​ዥም፤ እርም የሆነ ነገር ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


“እነ​ዚ​ህ​ንም፥ ከስ​እ​ለ​ታ​ች​ሁና በፈ​ቃ​ዳ​ችሁ ከም​ታ​መ​ጡት ሌላ፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ለእ​ህ​ልም፥ ለመ​ጠ​ጥም ቍር​ባን፥ ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ በበ​ዓ​ላ​ችሁ ጊዜ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርቡ።”


የእ​ህ​ል​ህን፥ የወ​ይን ጠጅ​ህን፥ የዘ​ይ​ት​ህ​ንም ዐሥ​ራት፥ የላ​ም​ህ​ንና የበ​ግ​ህ​ንም በኵ​ራት፥ የተ​ሳ​ል​ኸ​ው​ንም ስእ​ለት ሁሉ፥ በፈ​ቃ​ድህ ያቀ​ረ​ብ​ኸ​ውን፥ የእ​ጅ​ህ​ንም ቀዳ​ም​ያት በከ​ተ​ሞ​ችህ ሁሉ ውስጥ መብ​ላት አት​ች​ልም።


ወደ​ዚ​ያም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ቀዳ​ም​ያ​ታ​ች​ሁን፥ ስዕ​ለ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ በፈ​ቃ​ዳ​ችሁ የም​ታ​ቀ​ር​ቡ​ትን፥ የላ​ማ​ች​ሁ​ንና የበ​ጋ​ች​ሁ​ንም በኵ​ራት ውሰዱ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የባ​ረ​ከ​ህን ያህል እጅህ መስ​ጠት በም​ት​ች​ለው መጠን ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ባ​ቱን ሱባዔ በዓል ታደ​ር​ጋ​ለህ።


跟着我们:

广告


广告