Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 30:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተገ​ኝ​ተው የነ​በሩ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በየ​ቀኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገኑ የቂ​ጣ​ውን በዓል በታ​ላቅ ደስታ ሰባት ቀን አደ​ረጉ፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑና ካህ​ና​ቱም በዜማ ዕቃ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሌዋውያኑና ካህናቱ በእግዚአብሔር የዜማ ዕቃ ታጅበው፣ በየዕለቱ ለእግዚአብሔር እየዘመሩ፣ በኢየሩሳሌም የነበሩት እስራኤላውያን የቂጣን በዓል በታላቅ ደስታ ለሰባት ቀን አከበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በኢየሩሳሌምም ተገኝተው የነበሩ የእስራኤል ልጆች የቂጣውን በዓል በታላቅ ደስታ ሰባት ቀን አከበሩ፤ ሌዋውያኑና ካህናቱም በዜማ ዕቃ ለጌታ እየዘመሩ ዕለት ዕለት ጌታን ያመሰግኑ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በኢየሩሳሌም የተሰበሰበውም ሕዝብ ሰባት ቀን ሙሉ የቂጣን በዓል በታላቅ ደስታ አከበረ፤ ሌዋውያኑና ካህናቱም በየቀኑ በዜማ መሣሪያዎቻቸው በመታጀብ እየዘመሩ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በኢየሩሳሌምም ተገኝተው የነበሩ የእስራኤል ልጆች የቂጣውን በዓል በታላቅ ደስታ ሰባት ቀን አደረጉ፤ ሌዋውያኑና ካህናቱም በዜማ ዕቃ ለእግዚአብሔር እየዘመሩ ዕለት ዕለት እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 30:21
22 交叉引用  

ከሕ​ዝ​ቡም ጋር ተማ​ክሮ በሠ​ራ​ዊቱ ፊት የሚ​ሄ​ዱ​ትን፥ “ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” የሚ​ሉ​ት​ንም፥ በቅ​ድ​ስና የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑ​ትን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ዘ​ም​ሩ​ትን መዘ​ም​ራን አቆመ።


ንጉሡ ሕዝ​ቅ​ያ​ስና አለ​ቆ​ቹም በዳ​ዊ​ትና በነ​ቢዩ በአ​ሳፍ ቃል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ ሌዋ​ው​ያ​ንን አዘዙ። በደ​ስ​ታም አመ​ሰ​ገኑ፤ አጐ​ነ​በ​ሱም፤ ሰገ​ዱም።


ነገር ግን ከአ​ሴ​ርና ከም​ናሴ፥ ከዛ​ብ​ሎ​ንም አያሌ ሰዎች ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን አዋ​ረዱ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም መጡ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ታላቅ ደስታ ሆነ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ከዳ​ዊት ልጅ ከን​ጉሥ ሰሎ​ሞን ዘመን ጀምሮ እን​ደ​ዚህ ያለ በዓል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አል​ተ​ደ​ረ​ገም ነበር።


የተ​ገ​ኙ​ትም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በዚያ ቀን ፋሲ​ካ​ውን፥ ሰባት ቀንም የቂ​ጣ​ውን በዓል አደ​ረጉ።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር በሃያ ሦስ​ተ​ኛው ቀን ሕዝ​ቡን ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው አሰ​ና​በተ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዳ​ዊ​ትና ለሰ​ሎ​ሞን፥ ለሕ​ዝ​ቡም ለእ​ስ​ራ​ኤል ስላ​ደ​ረ​ገው ቸር​ነት በል​ባ​ቸው ደስ ብሎ​አ​ቸው ሄዱ።


እር​ሱም፥ “ሂዱ፤ የሰ​ባ​ው​ንም ብሉ፤ ጣፋ​ጩ​ንም ጠጡ፤ ለእ​ነ​ዚ​ያም ምንም ለሌ​ላ​ቸው እድል ፈን​ታ​ቸ​ውን ላኩ፤ ዛሬ ለጌ​ታ​ችን የተ​ቀ​ደሰ ቀን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይ​ላ​ችን ነውና አት​ዘኑ” አላ​ቸው።


ከም​ር​ኮም የተ​መ​ለ​ሱት ማኅ​በር ሁሉ ዳስ ሠሩ፤ በዳ​ሱም ውስጥ ተቀ​መጡ። ከነ​ዌም ልጅ ከኢ​ያሱ ዘመን ጀምሮ እስ​ከ​ዚያ ቀን ድረስ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ያለ አላ​ደ​ረ​ጉም ነበር። እጅ​ግም ታላቅ ደስታ ሆነ።


“ሰባት ቀን ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያም ቀን እር​ሾ​ውን ከቤ​ታ​ችሁ ታወ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ቀን አን​ሥቶ እስከ ሰባ​ተ​ኛው ቀን እርሾ ያለ​በ​ትን እን​ጀራ የሚ​በላ ነፍስ ከእ​ስ​ራ​ኤል ተለ​ይቶ ይጥፋ።


ስድ​ስት ቀን ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ሰባ​ተ​ኛ​ውም ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ይሆ​ናል።


በዚ​ህም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቂጣ በዓል ነው፤ ሰባት ቀን ቂጣ ብሉ።


ሥራ​ቸ​ው​ንም ጨር​ሰው ተመ​ለሱ፤ ሕፃኑ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቀርቶ ነበር፤ ዮሴ​ፍና እና​ቱም አላ​ወ​ቁም ነበር።


ፋሲ​ካም የሚ​ባ​ለው የቂጣ በዓል ቀረበ።


የፋ​ሲ​ካን በግ የሚ​ያ​ር​ዱ​ባት የቂጣ በዓ​ልም ደረ​ሰች።


ሁል​ጊ​ዜም አንድ ልብ ሆነው በቤተ መቅ​ደስ ያገ​ለ​ግሉ ነበር፤ በቤ​ትም ኅብ​ስ​ትን ይቈ​ርሱ ነበር፤ በደ​ስ​ታና በልብ ቅን​ን​ነ​ትም ምግ​ባ​ቸ​ውን ይመ​ገቡ ነበር።


እና​ን​ተም፥ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ች​ሁም፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ክፍ​ልና ርስት ስለ​ሌ​ለው በደ​ጆ​ቻ​ችሁ ውስጥ የተ​ቀ​መ​ጠው ሌዋ​ዊም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


በዚ​ያም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ብሉ፤ እጃ​ች​ሁ​ንም በም​ት​ዘ​ረ​ጉ​በት፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በባ​ረ​ካ​ችሁ ነገር ሁሉ፥ እና​ን​ተና ቤተ​ሰ​ባ​ችሁ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


አን​ተም፥ ወንድ ልጅ​ህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪ​ያ​ህና ሴት ባሪ​ያህ፥ በሀ​ገ​ር​ህም ውስጥ ያለ ሌዋ​ዊና መጻ​ተኛ፥ ድሃ-አደ​ግና መበ​ለ​ትም በበ​ዓ​ልህ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


ዘወ​ትር በጌ​ታ​ችን ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ደግሜ እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


跟着我们:

广告


广告