2 ዜና መዋዕል 30:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 በጉባኤውም ያልነጹ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ስለዚህም ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ራሳቸውን ላላነጹት ሁሉ የፋሲካውን በግ ያርዱላቸው ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ከጉባኤው መካከል አብዛኛዎቹ ራሳቸውን ያልቀደሱ ስለ ነበሩ፣ ሌዋውያኑ በሥርዐቱ መሠረት ራሳቸውን ላላነጹትና ጠቦቶቻቸውን ለእግዚአብሔር መቀደስ ላልቻሉት ሁሉ የፋሲካውን በጎች ማረድ ነበረባቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 በጉባኤውም ያልተቀደሱ እጅግ ሰዎች ነበሩ፤ ስለዚህም ሌዋውያን ለጌታ የተቀደሱ ለማድረግ ንጹሐን ላልሆኑት ሁሉ የፋሲካውን ጠቦት ያርዱላቸው ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ከሕዝቡ መካከል ብዙዎቹ ራሳቸውን ያላነጹ ስለ ነበሩ ለፋሲካ የሚሆኑትን የበግ ጠቦቶች ለማረድ አልተፈቀደላቸውም ነበር፤ ስለዚህ ሌዋውያን በእነርሱ ምትክ የበግ ጠቦቶቹን በማረድ ለእግዚአብሔር አቀረቡላቸው፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 በጉባኤውም ያልተቀደሱ እጅግ ሰዎች ነበሩ፤ ስለዚህም ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ይቀድሱአቸው ዘንድ ንጹሐን ላልሆኑት ሁሉ ፋሲካውን ያርዱላቸው ነበር። 参见章节 |