Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 30:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ አረዱ፤ ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ተዘ​ጋጁ ነጹም። ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አመጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በሁለተኛው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን በግ ዐረዱ። ካህናቱና ሌዋውያኑ ዐፍረው ስለ ነበር ራሳቸውን ቀደሱ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትንም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አመጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በሁለተኛውም ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን ጠቦት አረዱ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አዋረዱ፥ ተቀደሱም፥ ወደ ጌታም ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የሁለተኛው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን የበግ ጠቦቶችን ለፋሲካ በዓል መሥዋዕት አድርገው ዐረዱ፤ በዚህ ጊዜ ራሳቸውን ያላነጹ ካህናትና ሌዋውያን በጣም አፈሩ፤ ከዚህም የተነሣ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለዩ፤ ከዚያም በኋላ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ማቅረብ ቻሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በሁለተኛውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ፋሲካውን አረዱ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም አፈሩ፤ ተቀደሱም፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 30:15
16 交叉引用  

ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰብ​ስ​በው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ንጉሡ ትእ​ዛዝ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ያነጹ ዘንድ ራሳ​ቸ​ውን አነጹ።


ጉባ​ኤ​ውም ያመ​ጡት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ቍጥር ሰባ ወይ​ፈን፥ መቶም አውራ በጎች፥ ሁለት መቶም የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ ይህ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነበረ።


ነገር ግን ካህ​ናቱ ጥቂ​ቶች ነበ​ሩና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለመ​ግ​ፈፍ አይ​ች​ሉም ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ሌዋ​ው​ያን በቅን ልብ ከካ​ህ​ናት ይልቅ ይቀ​ደሱ ነበ​ርና ሥራው እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ፥ ካህ​ና​ቱም እስ​ኪ​ቀ​ደሱ ድረስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሌዋ​ው​ያን ያግ​ዙ​አ​ቸው ነበር።


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር የቂ​ጣ​ውን በዓል ያደ​ርጉ ዘንድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ብዙ ሕዝብ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እጅ​ግም ታላቅ ጉባኤ ነበረ።


ንጉ​ሡና አለ​ቆቹ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ያለ የእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር ፋሲ​ካ​ውን ያደ​ርጉ ዘንድ ተማ​ከሩ።


ንጉሡ ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ስለ ቍር​ባን ሺህ ወይ​ፈ​ኖ​ች​ንና ሰባት ሺህ በጎ​ችን ለይ​ሁ​ዳና ለጉ​ባ​ኤው ሰጥቶ ነበር፤ አለ​ቆ​ቹም ሺህ ወይ​ፈ​ኖ​ች​ንና ዐሥር ሺህ በጎ​ችን ለጉ​ባ​ኤው ሰጥ​ተው ነበር፤ ከካ​ህ​ናቱ እጅግ ብዙ ተቀ​ድ​ሰው ነበ​ርና።


ካህ​ናቱ በሚ​በቃ ቍጥር ስላ​ል​ተ​ቀ​ደሱ፥ ሕዝ​ቡም ገና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስላ​ል​ተ​ሰ​በ​ሰቡ በጊ​ዜው ያደ​ር​ጉት ዘንድ አል​ቻ​ሉም ነበ​ርና።


በማ​ኅ​በ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው ለተ​ቈ​ጠሩ ለሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸው፥ ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ይሰጡ ነበር፤ በእ​ም​ነት ፈጽ​መው ተቀ​ድ​ሰ​ዋ​ልና።


የፋ​ሲ​ካ​ው​ንም በግ እረዱ፤ እና​ን​ተም ተቀ​ደሱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ እጅ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ታደ​ርጉ ዘንድ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ አዘ​ጋጁ።”


ከመ​ቅ​ደ​ስም ከወጡ በኋላ በዚያ የነ​በ​ሩት ካህ​ናት ሁሉ ተቀ​ድ​ሰው ነበር፤ በሰ​ሞ​ና​ቸ​ውም አል​ተ​ከ​ፈ​ሉም ነበር።


ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም አንድ ሆነው ነጽ​ተው ነበር፤ ሁሉም ንጹ​ሓን ነበሩ፤ ለም​ር​ኮ​ኞ​ቹም ልጆች ሁሉ፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ለካ​ህ​ናቱ፥ ለራ​ሳ​ቸ​ውም የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ዐረዱ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ውረድ፤ ዛሬና ነገ ራሳ​ቸ​ውን ያንጹ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ያጥቡ ዘንድ ሕዝ​ቡን እዘ​ዛ​ቸው።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ቀ​ር​ቡት ካህ​ናት ደግሞ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ራሳ​ቸ​ውን ይቀ​ድሱ” አለው።


በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ ያድ​ር​ጉት፤ ከቂጣ እን​ጀ​ራና ከመ​ራራ ቅጠል ጋር ይብ​ሉት።


跟着我们:

广告


广告