Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 30:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ነገር ግን ከአ​ሴ​ርና ከም​ናሴ፥ ከዛ​ብ​ሎ​ንም አያሌ ሰዎች ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን አዋ​ረዱ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም መጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሆኖም ከአሴር፣ ከምናሴና ከዛብሎን ጥቂት ሰዎች ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ነገር ግን ከአሴርና ከምናሴ ከዛብሎንም ጥቂት ሰዎች ብቻ ራሳቸውን አዋረዱ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ይሁን እንጂ ለእግዚአብሔር ትሕትናን በማሳየት ወደ ኢየሩሳሌም ፈቃደኞች ሆነው የመጡ ከአሴር፥ ከምናሴና ከዛብሎን ነገዶች አንዳንድ ሰዎች ነበሩ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ነገር ግን ከአሴርና ከምናሴ ከዛብሎንም አያሌ ሰዎች ሰውነታቸውን አዋረዱ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 30:11
19 交叉引用  

ከይ​ሁዳ ልጆ​ችና ከብ​ን​ያም ልጆች፥ ከኤ​ፍ​ሬ​ምና ከም​ናሴ ልጆች በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጡ።


ደግ​ሞም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠዉ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ፈ​ለግ ልባ​ቸ​ውን የሰጡ ሁሉ እነ​ር​ሱን ተከ​ት​ለው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጡ።


በተ​ፀ​ፀ​ተም ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ከእ​ርሱ ዘንድ ራቀ፤ ፈጽ​ሞም አላ​ጠ​ፋ​ውም፤ በይ​ሁዳ መል​ካም ነገር ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና።


እንደ ትእ​ዛ​ዙም ሳይ​ሆን ከኤ​ፍ​ሬ​ምና ከም​ናሴ፥ ከይ​ሳ​ኮ​ርና ከዛ​ብ​ሎ​ንም ወገን እጅግ ሰዎች ሳይ​ነጹ ፋሲ​ካ​ውን በሉ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተገ​ኝ​ተው የነ​በሩ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በየ​ቀኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገኑ የቂ​ጣ​ውን በዓል በታ​ላቅ ደስታ ሰባት ቀን አደ​ረጉ፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑና ካህ​ና​ቱም በዜማ ዕቃ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።


የይ​ሁ​ዳም ጉባኤ ሁሉ ፥ ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የመጡ ጉባኤ ሁሉ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገር የመ​ጡ​ትና በይ​ሁዳ የኖ​ሩት እን​ግ​ዶች ደስ አላ​ቸው።


በተ​ጨ​ነ​ቀም ጊዜ አም​ላ​ኩን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለገ፤ በአ​ባ​ቶ​ቹም አም​ላክ ፊት ሰው​ነ​ቱን እጅግ አዋ​ረደ።


አሁ​ንም አቤቱ፥ የጻ​ድ​ቃን አም​ላ​ካ​ቸው አንተ ነህ። ንስ​ሓን የፈ​ጠ​ርህ ለጻ​ድቅ ሰው አይ​ደ​ለ​ምና፥ አን​ተን ላል​በ​ደሉ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አይ​ደ​ለ​ምና፤ ነገር ግን የእ​ኔን የኃ​ጥ​ኡን ንስሓ ወደ ማየት ተመ​ለስ።


አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ፈጽሜ በደ​ልሁ፤ ኀጢ​አ​ቴ​ንም አም​ና​ለሁ።


በፊ​ቴም ራስ​ህን አዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ በዚ​ህም ስፍራ በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ ቃሌን በሰ​ማህ ጊዜ ራስ​ህን አዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ ልብ​ስ​ህ​ንም ቀድ​ደህ በፊቴ አል​ቅ​ሰ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሙሴና አሮ​ንም ወደ ፈር​ዖን ገቡ፤ አሉ​ትም፥ “የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔን ማፈ​ርን እስከ መቼ እንቢ ትላ​ለህ? ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።


እኔም ደግሞ አግ​ድሜ ከእ​ነ​ርሱ ጋር በቍጣ ሄድሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድር አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ። ነገር ግን በዚ​ያን ጊዜ ያል​ተ​ገ​ረ​ዘው ልባ​ቸው ያፍ​ራል፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይና​ዘ​ዛሉ፤


ራሱን ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም ያሚ​ያ​ዋ​ርድ ከፍ ይላ​ልና።”


እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም የሚ​ያ​ዋ​ርድ ይከ​ብ​ራ​ልና።”


አም​ነው የተ​ከ​ተ​ሉት ሰዎ​ችም ነበሩ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ ከአ​ር​ዮ​ስ​ፋ​ጎስ ባለ​ሥ​ል​ጣ​ኖች ወገን የሚ​ሆን ዲዮ​ና​ስ​ዮስ ነበር፤ ደማ​ሪስ የም​ት​ባል ሴትም ነበ​ረች፤ ሌሎ​ችም አብ​ረ​ዋ​ቸው ነበሩ።


በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ፤ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።


እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኀይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤


跟着我们:

广告


广告