Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 30:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹም ከከ​ተማ ወደ ከተማ በኤ​ፍ​ሬ​ምና በም​ናሴ ሀገር እስከ ዛብ​ሎን ሄዱ፤ እነ​ዚያ ግን በን​ቀት ሳቁ​ባ​ቸው፤ አፌ​ዙ​ባ​ቸ​ውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 መልእክተኞቹም በኤፍሬምና በምናሴ ምድር ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላው ከተማ በመዘዋወር እስከ ዛብሎን ድረስ ሄዱ፤ ሕዝቡ ግን አንቋሸሻቸው፤ ተሣለቀባቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 መልእክተኞቹም ከከተማ ወደ ከተማ በኤፍሬምና በምናሴ አገር እስከ ዛብሎን ድረስ ሄዱ፤ በእዚያ ያሉ ሰዎች ግን በንቀት ሳቁባቸው፤ አፌዙባቸውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 መልእክተኞቹ በኤፍሬምና በምናሴ ነገዶች ግዛት ወደሚገኙ ከተማዎች ሁሉ በመሄድ እስከ ዛብሎን ነገድ ሰሜናዊ ግዛት ድረስ ዘለቁ፤ እነዚያ ግን በንቀት እየሳቁ ተሳለቁባቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 መልእክተኞቹም ከከተማ ወደ ከተማ በኤፍሬምና በምናሴ አገር እስከ ዛብሎን ሄዱ፤ እነዚያ ግን በንቀት ሳቁባቸው፤ አፌዙባቸውም።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 30:10
18 交叉引用  

ሎጥም ወጣ፤ ልጆ​ቹን ለሚ​ያ​ገ​ቡት ለአ​ማ​ቾ​ቹም አላ​ቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን ከተማ ያጠ​ፋ​ታ​ልና።” ለአ​ማ​ቾቹ ግን የሚ​ያ​ፌ​ዝ​ባ​ቸው መሰ​ላ​ቸው።


እንደ ንጉ​ሡም ትእ​ዛዝ መል​እ​ክ​ተ​ኞቹ እን​ዲህ የሚ​ለ​ውን የን​ጉ​ሡ​ንና የአ​ለ​ቆ​ቹን ደብ​ዳቤ ይዘው ወደ እስ​ራ​ኤ​ልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ፈጥ​ነው ሄዱ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ ወዳ​መ​ለጠ ቅሬ​ታ​ችሁ እን​ዲ​መ​ለስ ወደ አብ​ር​ሃ​ምና ወደ ይስ​ሐቅ ወደ ያዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለሱ።


ወደ ታላ​ቁም ካህን ወደ ኬል​ቅ​ያስ መጡ፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም በረ​ኞች ከም​ና​ሴና ከኤ​ፍ​ሬም፥ ከአ​ለ​ቆ​ችም፥ ከቀ​ረ​ውም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያም ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ከሚ​ኖ​ሩት የሰ​በ​ሰ​ቡ​ትን፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የቀ​ረ​በ​ውን ገን​ዘብ ሰጡት።


እነ​ርሱ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በሕ​ዝቡ ላይ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ፥ ፈው​ስም እስ​ከ​ማ​ይ​ገ​ኝ​ላ​ቸው ድረስ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​እ​ክ​ተ​ኞች ይሳ​ለቁ፥ ቃሉ​ንም ያቃ​ልሉ፥ በነ​ቢ​ያ​ቱም ላይ ያፌዙ ነበር።


ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላጥ፥ አገ​ል​ጋ​ዩም አሞ​ና​ዊው ጦቢያ፥ ዓረ​ባ​ዊ​ውም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በን​ቀት ሳቁ​ብን፤ ቀላል አድ​ር​ገ​ው​ንም ወደ እኛ መጡና፥ “ይህ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር ምን​ድን ነው? በውኑ በን​ጉሡ ላይ ትሸ​ፍቱ ዘንድ ትወ​ድ​ዳ​ላ​ች​ሁን?” አሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጠ​ራሁ እር​ሱም የመ​ለ​ሰ​ልኝ እኔ፥ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው መሣ​ለ​ቂያ እን​ደ​ሚ​ሆን ሰው ሆኛ​ለሁ፤ ጻድ​ቁና ንጹሑ ሰው መሣ​ለ​ቂያ ሆኖ​አል።


ሕይ​ወቴ ከሚ​ሮጥ ሰው ይልቅ ይፈ​ጥ​ናል፤ ይሸ​ሻል፥ መል​ካ​ም​ንም አያ​ይም።


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ ኤር​ም​ያ​ስን፥ “ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን በኰ​በ​ለሉ በአ​ይ​ሁድ እጅ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ኛል፤ እነ​ር​ሱም ያፌ​ዙ​ብ​ኛል ብዬ እፈ​ራ​ለሁ” አለው።


ገን​ዘ​ብን የሚ​ወዱ ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ይህን ሁሉ ነገር ሰም​ተው ተጠ​ቃ​ቀ​ሱ​በት።


ሕዝ​ቡም ቆመው ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ አለ​ቆ​ችም፥ “ሌሎ​ችን አዳነ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ረጠ ክር​ስ​ቶስ ከሆነ ራሱን ያድን” እያሉ ያፌ​ዙ​በት ነበር።


እንደ ሞተ​ችም ዐው​ቀ​ዋ​ልና ሳቁ​በት።


የሙ​ታ​ን​ንም ትን​ሣኤ በሰሙ ጊዜ እኩ​ሌ​ቶቹ አፌ​ዙ​በት፤ ሌሎ​ችም፥ “ስለ​ዚህ ነገር በሌላ ቀን እና​ዳ​ም​ጥ​ሃ​ለን” አሉት።


የገ​ረ​ፉ​አ​ቸው፥ የዘ​በ​ቱ​ባ​ቸ​ውና ያሠ​ሩ​አ​ቸው ወደ ወህኒ ያገ​ቡ​አ​ቸ​ውም አሉ።


跟着我们:

广告


广告