Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 29:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ሌዋ​ው​ያን ሆይ፥ ስሙኝ፤ ራሳ​ች​ሁን አንጹ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ቀድሱ፤ ርኩ​ስን ነገር ሁሉ ከመ​ቅ​ደሱ አስ​ወ​ግዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ሌዋውያን፤ ስሙኝ! ራሳችሁን አሁኑኑ ቀድሱ፤ የአባቶቻችሁን አምላክ የእግዚአብሔርንም ቤተ መቅደስ ቀድሱ። ርኩስ ነገርንም ሁሉ ከመቅደሱ አስወግዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እንዲህም አላቸው፦ “ሌዋውያን ሆይ! ስሙኝ፤ ተቀደሱ፥ የአባቶቻችሁንም አምላክ የጌታን ቤት ቀድሱ፤ ርኩሱንም ነገር ሁሉ ከመቅደሱ አስወግዱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እንዲህም አላቸው፦ “እናንተ ሌዋውያን! ራሳችሁን መቀደስና የቀድሞ አባቶቻችሁን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤተ መቀደስ ማንጻት አለባችሁ፤ ቤተ መቅደሱን የሚያረክስ ነገር ሁሉ ከቤተ መቅደሱ ማስወገድ ይኖርባችኋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እንዲህም አላቸው፤ “ሌዋውያን ሆይ! ስሙኝ፤ ተቀደሱ፤ የአባቶቻችሁንም አምላክ የእግዚአብሔርን ቤት ቀድሱ፤ ርኩሱን ነገር ሁሉ ከመቅደሱ አስወግዱ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 29:5
21 交叉引用  

“እና​ንተ የሌ​ዋ​ው​ያን አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ናችሁ፤ ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላት ስፍራ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ታመጡ ዘንድ እና​ን​ተና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ተቀ​ደሱ።


ነገር ግን ካህ​ናቱ ጥቂ​ቶች ነበ​ሩና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለመ​ግ​ፈፍ አይ​ች​ሉም ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ሌዋ​ው​ያን በቅን ልብ ከካ​ህ​ናት ይልቅ ይቀ​ደሱ ነበ​ርና ሥራው እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ፥ ካህ​ና​ቱም እስ​ኪ​ቀ​ደሱ ድረስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሌዋ​ው​ያን ያግ​ዙ​አ​ቸው ነበር።


ካህ​ና​ቱ​ንና ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም አስ​መጣ፤ በም​ሥ​ራቅ በኩል ባለው አደ​ባ​ባ​ይም ሰበ​ሰ​ባ​ቸው፤


የፋ​ሲ​ካ​ው​ንም በግ እረዱ፤ እና​ን​ተም ተቀ​ደሱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ እጅ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ታደ​ርጉ ዘንድ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ አዘ​ጋጁ።”


ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ራሳ​ቸ​ውን አነጹ፤ ሕዝ​ቡ​ንም፥ በረ​ኞ​ች​ንም ቅጥ​ሩ​ንም አነጹ።


ዕቃ ቤቶ​ቹ​ንም እን​ዲ​ያ​ነጹ አዘ​ዝሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ዕቃ​ዎች፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን፥ ዕጣ​ኑ​ንም መልሼ በዚያ አገ​ባሁ።


አቤቱ፥ ሕዝ​ብ​ህን አዋ​ረዱ፥ ርስ​ት​ህ​ንም አሠ​ቃዩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ውረድ፤ ዛሬና ነገ ራሳ​ቸ​ውን ያንጹ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ያጥቡ ዘንድ ሕዝ​ቡን እዘ​ዛ​ቸው።


ሕዝ​ቡ​ንም፥ “ለሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተዘ​ጋጁ፤ ወደ ሴቶ​ቻ​ች​ሁም አት​ቅ​ረቡ” አለ።


ጥሩ ውኃ​ንም እረ​ጭ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ከር​ኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ አነ​ጻ​ች​ኋ​ለሁ።


እጅ መሳ​ይ​ንም ዘረጋ፤ በራስ ጠጕ​ሬም ያዘኝ፤ መን​ፈ​ስም በም​ድ​ርና በሰ​ማይ መካ​ከል አነ​ሣኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ራእይ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ሰሜን ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ በር መግ​ቢያ ቅን​አት የተ​ባ​ለው ምስል ወደ አለ​በት አመ​ጣኝ፤


እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ከመ​ቅ​ደሴ ያር​ቁኝ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት በዚህ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን፥ ታላ​ቁን ርኵ​ሰት ታያ​ለ​ህን? ደግ​ሞም ተመ​ል​ሰህ ከዚህ የበ​ለጠ ታላቅ ርኵ​ሰት ታያ​ለህ” አለኝ።


ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስቡ፤ ማኅ​በ​ሩ​ንም ቀድሱ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም ጥሩ፤ ጡት የሚ​ጠ​ቡ​ት​ንና ሕፃ​ና​ትን ሰብ​ስቡ፤ ሙሽ​ራው ከእ​ል​ፍኙ፥ ሙሽ​ራ​ዪ​ቱም ከጫ​ጕ​ላዋ ይውጡ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦ​ትስ በጣ​ዖት ቤት ውስጥ የሚ​ያ​ኖር ማን ነው? የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪ​ያ​ዎች እኛ አይ​ደ​ለ​ን​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፥ “እኔ በእ​ነ​ርሱ አድ​ራ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እኖ​ራ​ለሁ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል።”


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ ይህ ተስፋ ያለን ስለ​ሆን ራሳ​ች​ንን እና​ንጻ፤ ሥጋ​ች​ንን አና​ር​ክስ፤ ነፍ​ሳ​ች​ን​ንም አና​ሳ​ድፍ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ፍ​ራት የም​ን​ቀ​ደ​ስ​በ​ትን እን​ሥራ።


跟着我们:

广告


广告