Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 29:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ጉባ​ኤው ሁሉ ይሰ​ግዱ ነበር፤ መዘ​ም​ራ​ኑም ይዘ​ምሩ ነበር፤ መለ​ከ​ተ​ኞ​ችም ይነፉ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 መዘምራኑ በሚዘምሩበትና መለከተኞቹም በሚነፉበት ጊዜም መላው ጉባኤ አጐንብሰው ሰገዱ፤ የሚቃጠለው መሥዋዕት እስኪጠናቀቅ ድረስም ይህ ሁሉ ቀጠለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ጉባኤውም ሁሉ ሰገዱ፥ መዘምራኑም ዘመሩ፥ መለከተኞችም ነፉ፤ የሚቃጠለው መሥዋዕት እስኪፈጸም ድረስ ይህ ሁሉ ያለማቋረጥ ተከነናወነ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በዚያ የነበረ ሕዝብም ሁሉ በኅብረት ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ መሥዋዕቱም ሁሉ ፈጽሞ እስከሚቃጠል ድረስ እምቢልተኞቹ እምቢልታቸውን ይነፉ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ጉባኤውም ሁሉ ሰገዱ፤ መዘምራኑም ዘመሩ፤ መለከተኞችም ነፉ፤ የሚቃጠለው መሥዋዕት እስኪፈጸም ድረስ ይህ ሁሉ ሆነ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 29:28
9 交叉引用  

ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ አሳ​ርጉ” አለ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ማሳ​ረግ በተ​ጀ​መረ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዝ​ሙር ደግሞ ተጀ​መረ፤ መለ​ከ​ቱም ተነፋ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የዳ​ዊት ዜማ ዕቃ ተመታ።


ማቅ​ረ​ቡ​ንም በፈ​ጸሙ ጊዜ ንጉሡ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሁሉ አጐ​ነ​በሱ፤ ሰገ​ዱም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወ​ርድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ ድን​ጋይ በተ​ነ​ጠ​ፈ​በ​ትም ምድር በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደ​ፍ​ተው ሰገዱ፥ “እርሱ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና” እያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ።


መከ​ራን ባሳ​የ​ኸን ዘመን ፋንታ፥ ክፉ​ንም ባየ​ን​ባት ዘመን ፋንታ ደስ ይለ​ናል።


እም​ነ​ትና በጎ​ነት በፊቱ፥ ቅድ​ስ​ናና የክ​ብር ገና​ና​ነት በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ናቸው።


አንተ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በም​ድር ላይ ሁሉ ብቻ​ህን ልዑል ነህና፥ በአ​ማ​ል​ክ​ትም ሁሉ ላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለ​ሃ​ልና።


ሕዝቡ በሚ​ገ​ቡ​በት ጊዜ አለ​ቃው በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ይግባ፤ በሚ​ወ​ጡ​በ​ትም ጊዜ ይውጣ።


跟着我们:

广告


广告