Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 29:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ካህ​ና​ቱም አረ​ዱ​አ​ቸው፤ ንጉ​ሡም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ እን​ዲ​ደ​ረግ አዝዞ ነበ​ርና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ማስ​ተ​ስ​ረያ ያደ​ርጉ ዘንድ ደማ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ አቀ​ረቡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ንጉሡ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኀጢአት መሥዋዕት ስለ እስራኤል ሁሉ እንዲቀርብ አዝዞ ስለ ነበር፣ ካህናቱ ፍየሎቹን ዐርደው ስለ እስራኤል ሁሉ ማስተስረያ እንዲሆን የኀጢአት መሥዋዕት በማድረግ ደሙን በመሠዊያው ላይ አቀረቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ንጉሡም የሚቃጠል መሥዋዕትና የኃጢአት መሥዋዕት ለእስራኤል ሁሉ እንዲደረግ አዝዞ ነበርና ለእስራኤል ሁሉ ማስተሰረያ እንዲያደርጉ የኃጢአቱን መሥዋዕት ደም በመሠዊያው ላይ አቀረቡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ንጉሡ ስለ መላው የእስራኤል ሕዝብ የሚቃጠል መሥዋዕትና ለኃጢአት ስርየት የሚሆን መሥዋዕት እንዲቀርብ አዞ ስለ ነበር፥ ካህናቱ በትእዛዙ መሠረት ፍየሎቹን ዐርደው ደማቸውን መሥዋዕት በማድረግ በመሠዊያው ላይ አፈሰሱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ንጉሡም የሚቃጠል መሥዋዕትና የኃጢያት መሥዋዕት ለእስራኤል ሁሉ እንዲደረግ አዝዞ ነበርና ለእስራኤል ሁሉ ማስተሰረያ ያደርጉ ዘንድ የኃጢያቱን መሥዋዕት ደም በመሠዊያው ላይ አቀረቡ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 29:24
15 交叉引用  

ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲካ ያደ​ርጉ ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዲ​መጡ ሕዝ​ቅ​ያስ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ላከ፤ ደግ​ሞም ወደ ኤፍ​ሬ​ምና ወደ ምናሴ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን ጻፈ።


በዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ቅዳሴ መቶ ወይ​ፈ​ኖ​ችና ሁለት መቶ አውራ በጎች፥ አራት መቶም የበግ ጠቦ​ቶች አቀ​ረቡ፤ ስለ ኀጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት እንደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ቍጥር ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየ​ሎች አቀ​ረቡ።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ማሰ​ማ​ርያ ከመ​ን​ጋው ከሁ​ለት መቶው አን​ዱን የበግ ጠቦት ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ይህ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ችሁ ዘንድ ለእ​ህል ቍር​ባ​ንና ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ይሆ​ናል” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በየ​በ​ዓ​ላ​ቱም፥ በየ​መ​ባ​ቻ​ውም፥ በየ​ሰ​ን​በ​ታ​ቱም በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ዓመት በዓል ሁሉ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን መስ​ጠት በአ​ለ​ቃው ላይ ይሆ​ናል፤ እርሱ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል።”


ተቀ​ባ​ይ​ነት ይኖ​ረው ዘንድ ስለ እር​ሱም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለት ዘንድ እጁን በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ራስ ላይ ይጭ​ናል።


ካህ​ኑም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ እር​ሱም ንጹሕ ይሆ​ናል።


ነገር ግን በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ለማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ይሆን ዘንድ ከደሙ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን የሚ​ገ​ባው የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ አይ​በ​ላም፤ በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላል።


አረ​ዱ​ትም፤ ሙሴም ደሙን ወስዶ በጣቱ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀን​ዶች ዙሪያ ቀባ፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም አነ​ጻው፤ ደሙ​ንም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች አፈ​ሰ​ሰው፤ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ትም ዘንድ ቀደ​ሰው።


ከዚ​ህም በኋላ የሕ​ዝ​ቡን ቍር​ባን አቀ​ረበ፤ ስለ ሕዝቡ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሆ​ነ​ውን ፍየል ወስዶ አረ​ደው፤ አነ​ጻ​ውም፤ እንደ ፊተ​ኛ​ውም ለየው።


ስለ​ዚ​ህም የሕ​ዝ​ብን ኀጢ​አት ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሆ​ነው ነገር ሁሉ የሚ​ም​ርና የታ​መነ ሊቀ ካህ​ናት እን​ዲ​ሆን በነ​ገር ሁሉ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሊመ​ስል ተገ​ባው።


跟着我们:

广告


广告