2 ዜና መዋዕል 29:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ንጉሡም አካዝ ነግሦ ሳለ በመተላለፉ ያረከሰውን ዕቃ ሁሉ አዘጋጅተናል፤ ቀድሰናልም፤ እነሆም፥ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ሆነዋል” አሉት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ንጉሥ አካዝ ነግሦ ሳለ ባለመታመኑ ከቦታቸው ያነሣቸውን ዕቃዎች ሁሉ አዘጋጅተን ቀድሰናቸዋል፤ እነሆ፤ ዕቃዎቹ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠዊያ ፊት ለፊት ናቸው።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ንጉሡም አካዝ ነግሦ ሳለ በመተላለፍ ያረከሰውን ዕቃ ሁሉ አዘጋጅተናል ቀድሰናልም፤ እነሆም፥ በጌታ መሠዊያ ፊት ተቀምጠዋል።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 እንዲሁም ንጉሥ አካዝ ለእግዚአብሔር ታማኝ ባልነበረባቸው ዓመቶች ወስዶት የነበረውን ዕቃ ሁሉ መልሰን በማምጣት ለእግዚአብሔር የተለዩ እንዲሆኑ አድርገናል፤ እነዚህም ዕቃዎች በሙሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ፊት ለፊት ባለው ስፍራ ይገኛሉ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ንጉሡም አካዝ ነግሦ ሳለ በመተላለፍ ያረከሰውን ዕቃ ሁሉ አዘጋጅተናል ቀድሰናልም፤ እነሆም፥ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ሆነዋል” አሉት። 参见章节 |