Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 28:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 አካ​ዝም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ነገር ግን ወደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አላ​ገ​ቡ​ትም፤ ልጁም ሕዝ​ቅ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 አካዝ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በኢየሩሳሌምም ከተማ ተቀበረ፤ የተቀበረው ግን በእስራኤል ነገሥታት መካነ መቃብር አልነበረም። ልጁ ሕዝቅያስም በምትኩ ነገሠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በከተማይቱም በኢየሩሳሌም ቀበሩት፤ ነገር ግን ወደ እስራኤል ነገሥታት መቃብር አላገቡትም፤ ልጁም ሕዝቅያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ንጉሥ አካዝ ሞተ፤ በኢየሩሳሌምም ተቀበረ፤ ይሁን እንጂ በነገሥታት መካነ መቃብር አልተቀበረም፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ሕዝቅያስ ነገሠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በከተማይቱም በኢየሩሳሌም ቀበሩት፤ ነገር ግን ወደ እስራኤል ነገሥታት መቃብር አላገቡትም፤ ልጁም ሕዝቅያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 28:27
11 交叉引用  

አካ​ዝም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፥ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ተቀ​በረ፤ ልጁም ሕዝ​ቅ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የኤላ ልጅ ሆሴዕ በነ​ገሠ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የአ​ካዝ ልጅ ሕዝ​ቅ​ያስ ነገሠ።


ለእ​ር​ሱም የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጆች አዛ​ር​ያስ፥ ኢይ​ሔል፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ዔዛ​ር​ያስ፥ ሚካ​ኤል፥ ሰፋ​ጥ​ያስ የሚ​ባሉ ስድ​ስት ወን​ድ​ሞች ነበ​ሩት፤ እነ​ዚህ ሁሉ የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጆች ነበሩ።


መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ የሠ​ላሳ ሁለት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ስም​ንት ዓመት ነገሠ፤ ማንም ሳያ​ዝ​ን​ለት ሄደ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ እንጂ በነ​ገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አል​ቀ​በ​ሩ​ትም።


ከእ​ር​ሱም ዘንድ አል​ፈው ከሄዱ በኋላ እጅግ ታሞ ሳለ ተዉት፤ የገዛ ባሪ​ያ​ዎ​ቹም ስለ ካህኑ ስለ ኢዮ​አዳ ልጅ ደም ተበ​ቅ​ለው በአ​ል​ጋው ላይ ገደ​ሉት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ነገር ግን በነ​ገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አል​ቀ​በ​ሩ​ትም።


ዖዝ​ያ​ንም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ ለም​ጻም ነው ብለ​ዋ​ልና የነ​ገ​ሥ​ታቱ መቃ​ብር ባል​ሆነ እርሻ ውስጥ ቀበ​ሩት፤ ልጁም ኢዮ​አ​ታም በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ በነ​በረ ጊዜ መን​ገሥ ጀመረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የዘ​ካ​ር​ያስ ልጅ አብያ ትባል ነበር።


ቍጥሩ ከባ​ሕር አሸዋ የሚ​በ​ልጥ በደ​ልን በድ​ያ​ለ​ሁና፥ ኀጢ​አ​ቴም ብዙ ነውና፤ ከበ​ደ​ሌም ብዛት የተ​ነሣ ቀና ብዬ የሰ​ማ​ይን ርዝ​መት አይ ዘንድ አገ​ባቤ አይ​ደ​ለም። ሰው​ነ​ቴን ከኀ​ጢ​አቴ አሳ​ር​ፋት ዘንድ በብ​ረት ቀፎ ደከ​ምሁ፤ በዚ​ህም ደግሞ አላ​ረ​ፍ​ሁም፤ መዓ​ት​ህን አነ​ሣ​ሥ​ቻ​ለ​ሁና፥


የጻድቃን መታሰቢያ ከምስጋና ጋር ነው። የኃጥኣን ስም ግን ይጠፋል።


ንጉሡ አካዝ በሞ​ተ​በት ዓመት ይህ ነገር ሆነ።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ው​ነት ቤትህ፥ የአ​ባ​ት​ህም ቤት፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በፊቴ እን​ዲ​ኖር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አሁን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያከ​በ​ሩ​ኝን አከ​ብ​ራ​ለ​ሁና፥ የና​ቁ​ኝም ይና​ቃ​ሉና ይህ አይ​ሆ​ን​ል​ኝም።


跟着我们:

广告


广告