Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 28:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ንጉ​ሡም፥ “የመ​ቱ​ኝን የደ​ማ​ስ​ቆን አማ​ል​ክት እፈ​ል​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የሶ​ር​ያን ንጉሥ እር​ሱን ረድ​ተ​ው​ታ​ልና እኔ​ንም ይረ​ዱኝ ዘንድ እሠ​ዋ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለ። ነገር ግን ለእ​ር​ሱና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዕን​ቅ​ፋት ሆኑ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እርሱም “የሶርያ ነገሥታት አማልክት እነርሱን ስለ ረዷቸው፣ እኔንም ይረዱኝ ዘንድ እሠዋላቸዋለሁ” ሲል እርሱን ላሸነፉት የደማስቆ አማልክት መሥዋዕት አቀረበ። ነገር ግን ለርሱና ለመላው እስራኤል መሰናክል ሆኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ድል ለነሡትም ለደማስቆ አማልክት፦ “የሶሪያን ነገሥታት አማልክት ረድተዋቸዋልና እኔን እንዲረዱኝ እሠዋላቸዋለሁ” ብሎ ሠዋላቸው። ነገር ግን ለእርሱና ለእስራኤል ሁሉ እንቅፋት ሆኑ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አካዝ ድልን ላጐናጸፉአቸው ለሶርያውያን አማልክት መሥዋዕት አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት “የሶርያ አማልክት የሶርያን ነገሥታት ረድተዋል፤ መሥዋዕት ባቀርብላቸው እኔንም ይረዱኛል” ብሎ በማሰብ ነው፤ ይህም ድርጊት በራሱና በሀገሩ ላይ ጥፋትን አመጣ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ለመቱትም ለደማስቆ አማልክት “የሶሪያን ነገሥታት አማልክት ረድተዋቸዋልና እኔን ይረዱ ዘንድ እሠዋላቸዋለሁ” ብሎ ሠዋላቸው። ነገር ግን ለእርሱና ለእስራኤል ሁሉ እንቅፋት ሆኑ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 28:23
11 交叉引用  

አሜ​ስ​ያ​ስም የኤ​ዶ​ም​ያ​ስን ሰዎች ከገ​ደለ በኋላ የሴ​ይ​ርን ልጆች አማ​ል​ክት አመጣ፤ የእ​ር​ሱም አማ​ል​ክት ይሆኑ ዘንድ አቆ​ማ​ቸው፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ይሰ​ግ​ድ​ላ​ቸ​ውና ይሠ​ዋ​ላ​ቸው ነበር።


በደ​ለ​ኞ​ችና ኀጢ​አ​ተ​ኞች ግን በአ​ን​ድ​ነት ይቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ተ​ዉት ሁሉ ይጠ​ፋሉ።


እና​ንተ ከአ​ሕ​ዛብ ወገን ሆና​ችሁ ያመ​ለ​ጣ​ችሁ፥ ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ኑ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ተማ​ከሩ፤ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን የም​ስ​ላ​ቸ​ውን እን​ጨት የሚ​ሸ​ከ​ሙና ያድን ዘንድ ወደ​ማ​ይ​ችል አም​ላክ የሚ​ጸ​ልዩ ዕው​ቀት የላ​ቸ​ውም።


እንደ ተቀ​ረጸ ብር ናቸው፤ እነ​ር​ሱም አይ​ና​ገ​ሩም፤ መራ​መ​ድም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል። ክፉ መሥ​ራ​ትም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና፥ ደግ​ሞም መል​ካም ይሠሩ ዘንድ አይ​ች​ሉ​ምና አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው።”


እግ​ር​ሽን ከሰ​ን​ከ​ል​ካላ መን​ገድ፥ ጕሮ​ሮ​ሽ​ንም ከውኃ ጥም ከል​ክዪ፤ እር​ስዋ ግን፥ “እጨ​ክ​ና​ለሁ፤ እን​ግ​ዶ​ች​ንም ወድ​ጄ​አ​ለሁ” ብላ ተከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው።


እስ​ራ​ኤል ሆይ! በመ​ከ​ራህ ጊዜ ማን ይረ​ዳ​ሃል?


ወዳ​ጆ​ች​ዋ​ንም ትከ​ተ​ላ​ለች፤ ነገር ግን አት​ደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ውም፤ ትፈ​ል​ጋ​ቸ​ው​ማ​ለች፤ ነገር ግን አታ​ገ​ኛ​ቸ​ውም፤ እር​ስ​ዋም፥ “ከዛሬ ይልቅ የዚ​ያን ጊዜ ይሻ​ለኝ ነበ​ርና ተመ​ልሼ ወደ ቀደ​መው ባሌ እሄ​ዳ​ለሁ” ትላ​ለች።


የዚያን ጊዜም እንደ ነፋስ አልፎ ይሄዳል፥ ይበድልማል፣ ኃይሉንም አምላክ ያደርገዋል።


跟着我们:

广告


广告