Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 28:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ደግ​ሞም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በቆ​ላ​ውና በደ​ቡብ በኩል ባሉት በይ​ሁዳ ከተ​ሞች አደጋ ጥለው ነበር፤ ቤት​ሳ​ሚ​ስ​ንና ኤሎ​ንን፥ ጋቤ​ሮ​ት​ንም፥ ሠካ​ዕ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ ቴም​ና​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋ​ንም፥ ጋማ​ዚ​እ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወስ​ደው በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ፍልስጥኤማውያን ደግሞ በየኰረብታው ግርጌና በይሁዳ ደቡብ ያሉትን ከተሞች በመውረር ቤትሳሚስን፣ ኤሎንን፣ ግዴሮትን፣ ሦኮን፣ ተምናን፣ ጊምዞንና በአካባቢያቸው የሚገኙትን መንደሮች ሁሉ ያዙ፤ ተቀመጡባቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ደግሞም ፍልስጤማውያን በቈላውና በደቡብ በኩል ባሉት በይሁዳ ከተሞች አደጋ ጥለው ነበር፤ ቤትሳሚስንና ኤሎንን፥ ግዴሮትንም፥ ሦኮንና መንደሮችዋን፥ ተምናንና መንደሮችዋን፥ ጊምዞንና መንደሮችዋን ወስደው በዚያ ተቀምጠው ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በዚሁ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን በምዕራባዊ ኰረብቶች ግርጌና በደቡባዊ ይሁዳ የሚገኙትን ታናናሽ ከተሞች ወረሩ፤ ቤትሼሜሽ፥ አያሎን፥ ገዴሮት፥ ሶኮ፥ ቲምናና ጊምዞ ተብለው የሚጠሩትን ከተሞችና በዙሪያቸው የሚገኙትን መንደሮች በድል አድራጊነት ያዙ፤ በዚያም ኖሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ደግሞም ፍልስጤማውያን በቈላውና በደቡብ በኩል ባሉት በይሁዳ ከተሞች አደጋ ጥለው ነበር፤ ቤትሳሚስንና ኤሎንን፥ ግዴሮትንም፥ ሦኮንና መንደሮችዋን፥ ተምናንና መንደሮችዋን፥ ጊምዞንና መንደሮችዋን ወስደው በዚያ ተቀምጠው ነበር።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 28:18
13 交叉引用  

ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም እስከ ጋዛና እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ፥ ከዘ​በ​ኞች ግንብ ጀምሮ እስከ ምሽጉ ከተማ ድረስ አጠፋ።


ሶር​ዓን፥ ኤሎ​ንን፥ ኬብ​ሮ​ንን ሠራ።


ቤተ​ሱ​ራን፥ ሱላ​ኮን፥ ዓዶ​ላ​ምን፥


ጠላ​ቶ​ቹን ሶር​ያ​ው​ያ​ን​ንም ከም​ሥ​ራቅ፥ አረ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ከም​ዕ​ራብ ያን​ቀ​ሳ​ቅ​ስ​በ​ታል፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በተ​ከ​ፈተ አፍ ይበ​ሉ​ታል። በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


ስለ​ዚህ እነሆ እጄን በአ​ንቺ ላይ ዘር​ግ​ቻ​ለሁ፤ ድር​ሻ​ሽ​ንም አጕ​ድ​ያ​ለሁ፤ ለሚ​ጠ​ሉ​ሽም፥ ከመ​ን​ገ​ድሽ ለመ​ለ​ሱ​ሽና ለአ​ሳ​ቱሽ ለፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሴቶች ልጆች ፈቃድ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​ሻ​ለሁ።


ክፋ​ትሽ እንደ ዛሬው ሳይ​ገ​ለጥ ለሶ​ርያ ሴቶች ልጆ​ችና ለጐ​ረ​ቤ​ቶ​ችዋ ሁሉ በዙ​ሪ​ያ​ሽም ለሚ​ከ​ቡሽ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያት ሴቶች ልጆች መሰ​ደ​ቢያ ሆነ​ሻል።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በቀ​ልን አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፥ በቀ​ላ​ቸ​ው​ንም አጽ​ን​ተ​ዋ​ልና፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጠፉ ዘንድ ነፍ​ሳ​ቸው ደስ ይላ​ታ​ልና፤


ድን​በ​ሩም ከበ​ኣላ በባ​ሕር በኩል ያል​ፋል፤ ከዚ​ያም በኢ​ያ​ሪም ከተማ ደቡብ በኩ​ልና በኪ​ስ​ሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥ​ራ​ቱስ ድን​በር ያል​ፋል፤ በፀ​ሐይ ከተ​ማም ላይ ይወ​ር​ዳል፤ በሊ​ባም በኩል ያል​ፋል።


ጌዶር፥ በጋ​ድ​ያል፥ ኖማን፥ መቄ​ዶም፥ ዐሥራ ስድ​ስት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።


የሳ​ምር ተራ​ራ​ዎች ፥ ኢዩ​ቴር፥ ሦካ፤


ሶም​ሶ​ንም ወደ ቴም​ናታ ወረደ፤ በቴ​ም​ና​ታም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ልጆች አን​ዲት ሴት አየ፤ እር​ስ​ዋም በፊቱ ደስ አለ​ችው።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ለጦ​ር​ነት ሰበ​ሰቡ፤ ራሳ​ቸ​ውም በይ​ሁዳ በሰ​ኮት ተሰ​በ​ሰቡ፤ በሰ​ኮ​ትና በዓ​ዜቃ መካ​ከል በኤ​ፌ​ር​ሜም ሰፈሩ።


ወደ​ም​ት​ሄ​ድ​በ​ትም ተመ​ል​ከቱ፤ በድ​ን​በ​ሩም መን​ገድ ላይ ወደ ቤት​ሳ​ሚስ ብት​ወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደ​ረ​ገ​ብን እርሱ ነው፤ አለ​ዚ​ያም እን​ዲ​ያው መጥ​ቶ​ብ​ናል እንጂ የመ​ታን የእ​ርሱ እጅ እን​ዳ​ል​ሆነ እና​ው​ቃ​ለን።”


跟着我们:

广告


广告