Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 25:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ንጉሡ አሜ​ስ​ያ​ስም ከኤ​ፍ​ሬም ከተ​ሞች የመጡ ጭፍ​ሮች ወደ ስፍ​ራ​ቸው ይመ​ለሱ ዘንድ ለይቶ አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ ስለ​ዚ​ህም ቍጣ​ቸው በይ​ሁዳ ላይ ጸና፤ ወደ ስፍ​ራ​ቸ​ውም በጽኑ ቍጣ ተመ​ለሱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ስለዚህ አሜስያስ ከኤፍሬም ወደ እርሱ የመጡትን ወታደሮች ወደየመኖሪያ ስፍራቸው አሰናበታቸው። እነርሱም በይሁዳ ላይ ክፉኛ ተበሳጭተው ነበርና በታላቅ ቍጣ ወደ መኖሪያ ስፍራቸው ተመለሱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አሜስያስም ከኤፍሬም የመጡትን ሠራዊት ወደ ስፍራቸው እንዲመለሱ ለይቶ አሰናበታቸው፤ ስለዚህም ቁጣቸው በይሁዳ ላይ ጸና፥ ወደ አገራቸውም በጽኑ ቁጣ ተመለሱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ስለዚህ አሜስያስ ቅጥረኞቹን ወታደሮች ወደየመኖሪያ ስፍራቸው እንዲሄዱ አሰናበታቸው፤ እነርሱም በይሁዳ ሕዝብ ላይ እጅግ ተቈጥተው ወደ መኖሪያ ስፍራቸው ሄዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አሜስያስም ከኤፍሬም የመጡት ጭፍሮች ወደ ስፍራቸው ይመለሱ ዘንድ ለይቶ አሰናበታቸው፤ ስለዚህም ቍጣቸው በይሁዳ ላይ ጸና፤ ወደ አገራቸውም በጽኑ ቍጣ ተመለሱ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 25:10
5 交叉引用  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ለይ​ሁዳ ሰዎች መል​ሰው፥ “በን​ጉሡ ዘንድ ለእኛ ዐሥር ክፍል አለን፤ ከእ​ና​ን​ተም እኛ እን​ቀ​ድ​ማ​ለን፤ እኛም በኵር ነን፤ ለዳ​ዊ​ትም ከእ​ና​ንተ እኛ እን​ቀ​ር​ባ​ለን፤ ስለ​ምን ናቃ​ች​ሁን? ንጉ​ሡ​ንስ እን​መ​ል​ሰው ዘንድ ከእ​ና​ንተ የእኛ ቃል አይ​ቀ​ድ​ም​ምን?” አሏ​ቸው። የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ቃል ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ቃል ይልቅ ጠነ​ከረ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ነውና አት​ውጡ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አት​ውጉ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ቤቱ ይመ​ለስ።” እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰሙ፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ተመ​ል​ሰው ሄዱ።


አሜ​ስ​ያ​ስም በረታ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስቦ ወደ ጨው ሸለቆ ሄደ፤ ከሴ​ይ​ርም ልጆች ዐሥር ሺህ ገደለ።


አሜ​ስ​ያ​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ጭፍራ የሰ​ጠ​ሁት መቶ መክ​ሊት ምን ይሁን?” አለው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው፥ “ከዚህ አብ​ልጦ ይሰ​ጥህ ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ሳ​ነ​ውም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


跟着我们:

广告


广告