Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 24:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ከእ​ር​ሱም ዘንድ አል​ፈው ከሄዱ በኋላ እጅግ ታሞ ሳለ ተዉት፤ የገዛ ባሪ​ያ​ዎ​ቹም ስለ ካህኑ ስለ ኢዮ​አዳ ልጅ ደም ተበ​ቅ​ለው በአ​ል​ጋው ላይ ገደ​ሉት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ነገር ግን በነ​ገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አል​ቀ​በ​ሩ​ትም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ሶርያውያንም በወጡ ጊዜ ኢዮአስን ክፉኛ አቍስለው፣ ጥለውት ሄዱ፤ የካህኑን የዮዳሄን ልጅ ስለ ገደለም፣ ሹማምቱ አሢረውበት በዐልጋው ላይ እንዳለ ገደሉት። በዚህ ሁኔታም ሞቶ በዳዊት ከተማ ተቀበረ እንጂ በነገሥታቱ መቃብር አልተቀበረም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እርሱንም ትተውት በሄዱ ጊዜ በጽኑ አቊስለውት ነበር፤ የገዛ ባርያዎቹም የካህኑ የዮዳሄን ልጅ ደም ለመበቀል ሲሉ አሴሩበት፥ በአልጋውም ላይ ገደሉት፥ ሞተም፤ በዳዊት ከተማ እንጂ በነገሥታት መቃብር አልቀበሩትም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በብርቱም ቈስሎ ነበር፤ የጠላት ሠራዊት ከዚያ ተነሥቶ ከሄደ በኋላ ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች የካህኑን የዮዳሄን ልጅ ደም ለመበቀል በንጉሡ ላይ አሢረው በአልጋው ላይ እንዳለ ገደሉት፤ ንጉሡም በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ይሁን እንጂ በነገሥታት መካነ መቃብር አልተቀበረም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ከእርሱም ዘንድ አልፈው ከሄዱ በኋላ እጅግ ታምሞ ነበር፤ የገዛ ባሪያዎቹም ስለ ካህኑ ስለ ዮዳሄ ልጅ ተበቅለው ተማማሉበት፤ በአልጋውም ላይ ገደሉት፤ ሞተም፤ በዳዊት ከተማ እንጂ በነገሥታት መቃብር አልቀበሩትም።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 24:25
15 交叉引用  

ከበ​ለ​ዓን ቤት የሆነ የአ​ኪያ ልጅ ባኦስ ዐመ​ፀ​በት፤ ናባ​ጥና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ገባ​ቶ​ንን ከብ​በው ነበ​ርና ባኦስ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ልም ሀገር ባለው በገ​ባ​ቶን ገደ​ለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንና በኢ​ት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያን አጠ​ገብ የሚ​ኖ​ሩ​ትን የዓ​ረ​ብ​ያን ሰዎች በኢ​ዮ​ራም ላይ አስ​ነሣ።


ከሶ​ር​ያም ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ ሶር​ያ​ው​ያን በሬ​ማት ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል ይታ​ከም ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ተመ​ለሰ፤ ታም​ሞም ነበ​ርና የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ የአ​ክ​ዓ​ብን ልጅ ኢዮ​ራ​ምን ያይ ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወረደ።


አካ​ዝ​ያ​ስ​ንም ፈለ​ገው፤ በሰ​ማ​ር​ያም እየ​ታ​ከመ ሳለ አገ​ኙት፤ ወደ ኢዩም አመ​ጡት፤ እር​ሱም ገደ​ለው፦ እነ​ር​ሱም፥ “በፍ​ጹም ልብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የፈ​ለ​ገው የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ነው” ብለው ቀበ​ሩት። ከአ​ካ​ዝ​ያ​ስም ቤት ማንም መን​ግ​ሥ​ትን ይይዝ ዘንድ የሚ​ችል አል​ነ​በ​ረም።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ከቤ​ቱም ጋር መል​ካም ሠር​ቶ​አ​ልና በዳ​ዊት ከተማ ከነ​ገ​ሥ​ታቱ ጋር ቀበ​ሩት።


የገ​ደ​ሉ​ትም የአ​ሞ​ና​ዊቱ የሰ​ማት ልጅ ዘቡድ፥ የሞ​ዓ​ባ​ዊ​ቱም የሰ​ማ​ሪት ልጅ ኢዮ​ዛ​ብድ ነበሩ።


አሜ​ስ​ያ​ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል በራቀ ጊዜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የዐ​መፅ መሐላ አደ​ረ​ጉ​በት፤ ወደ ለኪ​ሶም ኮበ​ለለ፤ በስ​ተ​ኋ​ላ​ውም ወደ ለኪሶ ላኩ፤ በዚ​ያም ገደ​ሉት።


መን​ግ​ሥ​ትም በእጁ በጸ​ና​ለት ጊዜ ንጉ​ሡን አባ​ቱን የገ​ደ​ሉ​ትን ባሪ​ያ​ዎች ገደለ።


አካ​ዝም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ነገር ግን ወደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አላ​ገ​ቡ​ትም፤ ልጁም ሕዝ​ቅ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፤ የሚገባቸው ነውና፤” ብሎ ሲናገር ሰማሁ።


跟着我们:

广告


广告