Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 24:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ንጉ​ሡና ኢዮ​አ​ዳም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሥራ ላይ ለተ​ሾ​ሙት ሰጡ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የሚ​ጠ​ግ​ኑ​ትን ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንና አና​ጢ​ዎ​ችን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት የሚ​ያ​ድ​ሱ​ትን የብ​ረ​ትና የናስ ሠራ​ተ​ኞ​ችን ይቀ​ጥ​ሩ​በት ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ንጉሡና ዮዳሄም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ እንዲያሠሩ ለተመደቡት ሰዎች ገንዘቡን አስረከቧቸው፤ እነርሱም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለማደስ ድንጋይ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችና ዐናጺዎችን እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለመጠገን የብረትና የናስ ሠራተኞችን ቀጠሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ንጉሡና ዮዳሄም በጌታ ቤት ሥራ ላይ ለተሾሙት ሰጡአቸው፤ እነርሱም የጌታን ቤት የሚጠግኑትን ጠራቢዎችንና አናጢዎችን፥ የጌታንም ቤት የሚያድሱትን የብረትና የናስ ሠራተኞችን ይቀጥሩበት ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ንጉሡና ካህኑ ዮዳሄ ገንዘቡን የቤተ መቅደሱ እድሳት ኀላፊዎች ለሆኑት ሰዎች ይሰጡአቸው ነበር፤ እነዚህም ኀላፊዎች ገንዘቡን ቤተ መቅደሱን የሚጠግኑ ግንበኞችን፥ አናጢዎችንና ብረታ ብረት ሠራተኞችን ይቀጥሩበት ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ንጉሡና ዮዳሄም በእግዚአብሔር ቤት ሥራ ላይ ለተሾሙት ሰጡአቸው፤ እነርሱም የእግዚአብሔርን ቤት የሚጠግኑትን ጠራቢዎችንና አናጢዎችን፥ የእግዚአብሔርንም ቤት የሚያድሱትን የብረትና የናስ ሠራተኞችን ይገዙበት ነበር።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 24:12
7 交叉引用  

የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን፥ የዝ​ግባ እን​ጨ​ት​ንም፥ አና​ጢ​ዎ​ች​ንም፥ ድን​ጋይ ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንም ላከ፤ ለዳ​ዊ​ትም ቤት ሠሩ​ለት።


ለሰ​ሎ​ሞ​ንም ሰባ ሺህ ተሸ​ካ​ሚ​ዎች፥ ሰማ​ንያ ሺህም በተ​ራ​ራው ላይ ድን​ጋይ የሚ​ጠ​ርቡ ጠራ​ቢ​ዎች ነበ​ሩት።


ሣጥ​ኑም በሌ​ዋ​ው​ያን እጅ ወደ ንጉሡ ሹሞች በደ​ረሰ ጊዜ፥ ብዙ ገን​ዘ​ብም እን​ዳ​ለ​በት ባዩ ጊዜ፥ የን​ጉሡ ጸሓ​ፊና የሊቀ ካህ​ናቱ ሹም እየ​መጡ ብሩን ከሣ​ጥን ያወጡ ነበር፤ ሣጥ​ኑ​ንም ደግሞ ወደ ስፍ​ራው ይመ​ል​ሱት ነበር። እን​ዲ​ሁም በየ​ቀኑ ያደ​ርጉ ነበር፤ ብዙም ገን​ዘብ ሰበ​ሰቡ።


ሠራ​ተ​ኞ​ችም ሠሩ፤ ሥራ​ውም ሁሉ በእ​ጃ​ቸው ተፈ​ጸመ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት እንደ ቀድ​ሞው ሥራ መለሱ፤ አጽ​ን​ተ​ውም አቆ​ሙት።


የል​ጆ​ቹና በእ​ርሱ ላይ የተ​ደ​ረ​ገው ነገር፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ማደሱ፥ እነሆ በነ​ገ​ሥ​ታቱ የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል። ልጁም አሜ​ስ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


በነ​ገ​ሠም በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት ምድ​ሪ​ቱ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ካነጻ በኋላ፥ የሴ​ልያ ልጅ ሳፋን፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም አለቃ መዕ​ሴያ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ ኢዮ​አክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ኩን ቤት ይጠ​ግኑ ዘንድ ሰደ​ዳ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告