2 ዜና መዋዕል 23:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 የሀገሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው አፈረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹንም አደቀቁ፤ የበዓልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ሄደው የበኣልን ቤተ ጣዖት አፈራረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሰባበሩ፤ የበኣልን ካህን ማታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደሉት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ሕዝቡም ሁሉ ወደ ባዓል ቤት ሄደው አፈረሱት፥ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹንም አደቀቁ፥ የባዓልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ከዚህም በኋላ ሁሉም በአንድነት ባዓል ተብሎ ወደሚጠራው ቤተ ጣዖት ሄደው አፈረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሁሉ ሰባበሩ፤ ማታን ተብሎ የሚጠራውንም የባዓል ካህን በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደሉት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ሕዝቡም ሁሉ ወደ ባኣል ቤት ሄደው አፈረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹንም አደቀቁ፤ የባኣልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት። 参见章节 |