Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 22:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በም​ክ​ራ​ቸ​ውም ሄደ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ከአ​ክ​ዓብ ልጅ ከኢ​ዮ​ራም ጋር የሶ​ር​ያን ንጉሥ አዛ​ሄ​ልን በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ ሊዋጋ ሄደ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ኢዮ​ራ​ምን አቈ​ሰ​ሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እንዲሁም የእስራኤል ንጉሥ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም የሶርያን ንጉሥ አዛሄልን ለመውጋት ወደ ራሞት ገለዓድ በሄደ ጊዜ፣ የእነዚህኑ ሰዎች ምክር ተከትሎ ከኢዮራም ጋራ ዐብሮት ሄደ፣ ሶርያውያንም ኢዮራምን አቈሰሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በምክራቸውም ሄደ፥ ከእስራኤልም ንጉሥ ከአክዓብ ልጅ ከኢዮራም ጋር የሶርያን ንጉሥ አዛሄልን በሬማት ዘገለዓድ ሊዋጋ ሄደ፤ ሶርያውያንም ኢዮራምን አቈሰሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የእነርሱንም ምክር ተከትሎ በሶርያ ንጉሥ አዛሄል ላይ በተደረገው ጦርነት ከእስራኤል ንጉሥ ኢዮራም ጋር ተባበረ፤ ጦርነቱም በገለዓድ በምትገኘው በራሞት አጠገብ ተደርጎ በዚያ ውጊያ ላይ ኢዮራም ቈሰለ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በምክራቸውም ሄደ፤ ከእስራኤልም ንጉሥ ከአክዓብ ልጅ ከኢዮራም ጋር የሶርያን ንጉሥ አዛሄልን በሬማት ዘገለአድ ሊዋጋ ሄደ፤ ሶርያውያንም ኢዮራንም አቈሰሉት።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 22:5
13 交叉引用  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ የእኛ እንደ ሆነች፥ እኛም ከሶ​ርያ ንጉሥ እጅ ሳን​ወ​ስ​ዳት ዝም እን​ዳ​ልን ታው​ቃ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው።


በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ የጌ​ቤር ልጅ ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም በገ​ለ​ዓድ ያሉት የም​ናሴ ልጅ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ነበሩ፤ ለእ​ር​ሱም ደግሞ በባ​ሳን፥ በአ​ር​ጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥ​ርና የናስ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች የነ​በ​ረ​ባ​ቸው ስድሳ ታላ​ላቅ ከተ​ሞች ነበ​ሩ​በት፤


በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የአ​ክ​ዓብ ልጅ ኢዮ​ራም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ ዐሥራ ሁለ​ትም ዓመት ነገሠ።


አዛ​ሄ​ልም ሊገ​ና​ኘው ሄደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ከደ​ማ​ስቆ መል​ካ​ሙን ነገር ሁሉ የአ​ርባ ግመል ጭነት ገጸ በረ​ከት ወሰደ፤ መጥ​ቶም በፊቱ ቆመና፥ “ልጅህ የሶ​ርያ ንጉሥ ወልደ አዴር፦ ከዚህ በሽታ እድ​ና​ለ​ሁን? ሲል ወደ አንተ ልኮ​ኛል” አለው።


ነቢ​ዩም ኤል​ሳዕ ከነ​ቢ​ያት ልጆች አን​ዱን ጠርቶ እን​ዲህ አለው፥ “ወገ​ብ​ህን ታጥ​ቀህ ይህን የዘ​ይት ቀንድ በእ​ጅህ ያዝ፤ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓ​ድም ሂድ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አክ​ዓብ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ከእኔ ጋር ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ትሄ​ዳ​ለ​ህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝ​ቤም ለሰ​ልፍ እንደ ሕዝ​ብህ ናቸው፤” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም አለ​ቆች ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ባዩ ጊዜ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ነው” አሉ፤ ሊጋ​ጠ​ሙ​ትም ከበ​ቡት፤ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ግን ጮኸ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ነው፤ አም​ላ​ኩም ከእ​ርሱ መለ​ሳ​ቸው።


ነቢዩ የአ​ናኒ ልጅ ኢዩ ሊገ​ና​ኘው ወጣ፤ ንጉ​ሡ​ንም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ታግ​ዛ​ለ​ህን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጠ​ላ​ውን ትወ​ድ​ዳ​ለ​ህን? ስለ​ዚ​ህም ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ቍጣ መጥ​ቶ​ብ​ሃል።


ከሶ​ር​ያም ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ ሶር​ያ​ው​ያን በሬ​ማት ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል ይታ​ከም ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ተመ​ለሰ፤ ታም​ሞም ነበ​ርና የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ የአ​ክ​ዓ​ብን ልጅ ኢዮ​ራ​ምን ያይ ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወረደ።


ምስ​ጉን ነው፥ በዝ​ን​ጉ​ዎች ምክር ያል​ሄደ፥ በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም መን​ገድ ያል​ቆመ፥ በዋ​ዘ​ኞ​ችም ወን​በር ያል​ተ​ቀ​መጠ ሰው።


አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


跟着我们:

广告


广告