Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 21:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ነገር ግን ከዳ​ዊት ጋር ስላ​ደ​ረ​ገው ቃል ኪዳን፥ ለእ​ር​ሱና ለል​ጆ​ቹም በዘ​መ​ናት ሁሉ መብ​ራ​ትን ይሰ​ጠው ዘንድ ስለ ሰጠው ተስፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳ​ዊ​ትን ቤት ያጠፋ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከዳዊት ጋራ ካደረገው ኪዳን የተነሣ፣ የዳዊትን ቤት ማጥፋት አልፈለገም፤ ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም መብራት እንደሚሰጥ ተስፋ ሰጥቶ ነበርና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ነገር ግን ከዳዊት ጋር ስላደረገው ቃል ኪዳን፥ ለእርሱና ለልጆቹም በዘመናት ሁሉ መብራት ለመስጠት ስላደረገው ተስፋ፥ ጌታ የዳዊትን ቤት ለማጥፋት አልፈለገም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር የዳዊትን ሥርወ መንግሥት ሊያጠፋ አልፈለገም፤ ይህም የሆነው እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ከዳዊት ጋር ቃል ኪዳን ገብቶ ስለ ነበርና የዳዊት ዘሮችም ዘወትር ሳያቋርጡ የሚነግሡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተስፋ ቃል ሰጥቶት ስለ ነበር ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ነገር ግን ከዳዊት ጋር ስላደረገው ቃል ኪዳን፥ ለእርሱና ለልጆቹም በዘመናት ሁሉ መብራት ይሰጠው ዘንድ ስለ ሰጠው ተስፋ፥ እግዚአብሔር የዳዊትን ቤት ያጠፋ ዘንድ አልወደደም።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 21:7
19 交叉引用  

የሶ​ር​ህ​ያም ልጅ አቢሳ አዳ​ነው፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም ወግቶ ገደ​ለው። ያን​ጊ​ዜም የዳ​ዊት ሰዎች፥ “አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል መብ​ራት እን​ዳ​ት​ጠፋ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰ​ልፍ አት​ወ​ጣም” ብለው ማሉ​ለት።


በውኑ ቤቴ በኀ​ያሉ ዘንድ እን​ዲሁ አይ​ደ​ለ​ምን? ከእ​ኔም ጋር በዘ​መኑ ሁሉ የተ​ዘ​ጋ​ጀና የተ​ጠ​በቀ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን አድ​ር​ጎ​አል፤ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ፈቃ​ዴም ሁሉ ይህ ነውና። ዐመ​ፀ​ኛም አይ​በ​ቅ​ል​ምና።


ነገር ግን ስለ ባሪ​ያዬ ስለ ዳዊ​ትና ስለ መረ​ጥ​ኋት ሀገሬ ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለል​ጅህ አንድ ነገድ እሰ​ጣ​ለሁ እንጂ መን​ግ​ሥ​ቱን ሁሉ አል​ከ​ፍ​ልም።”


ስሜ​ንም ባኖ​ር​ሁ​ባት በዚ​ያች በመ​ረ​ጥ​ኋት ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለባ​ሪ​ያዬ ለዳ​ዊት በፊቴ ሁል​ጊዜ መብ​ራት ይሆ​ን​ለት ዘንድ ለልጁ ሁለት ነገ​ድን እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ።


ነገር ግን ልጁን ከእ​ርሱ በኋላ ያስ​ነሣ ዘንድ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ያጸና ዘንድ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ዳዊት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መብ​ራ​ትን አደ​ረ​ገ​ለት፤


ነገር ግን ለእ​ር​ሱና ለል​ጆቹ በዘ​መኑ ሁሉ መብ​ራት ይሰ​ጠው ዘንድ ተስፋ እንደ አደ​ረ​ገ​ለት፥ ስለ ባሪ​ያው ስለ ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁ​ዳን ያጠፋ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም።


ኢዮ​ራ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ በፋ​ን​ታ​ውም ልጁ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።


የን​ጉሡ ልጅ ዮሳ​ቤት ግን ከተ​ገ​ደ​ሉት ከን​ጉሡ ልጆች መካ​ከል የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ልጅ ኢዮ​አ​ስን ሰርቃ ወሰ​ደች፤ እር​ሱ​ንና ሞግ​ዚ​ቱን በእ​ል​ፍኝ ውስጥ አኖ​ረ​ቻ​ቸው፤ የን​ጉሡ የኢ​ዮ​ራም ልጅ የአ​ካ​ዝ​ያስ እኅት የካ​ህኑ የዮ​ዳሄ ሚስት ዮሳ​ቤት ከጎ​ቶ​ልያ ፊት ሸሸ​ገ​ችው፤ እር​ስ​ዋም አል​ገ​ደ​ለ​ች​ውም።


የይ​ሁ​ዳም ጉባኤ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ ከን​ጉሥ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ። የን​ጉ​ሥ​ንም ልጅ አሳ​ያ​ቸው፤ አላ​ቸ​ውም፥ “እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ዳዊት ቤት እንደ ተና​ገረ የን​ጉሡ ልጅ ይነ​ግ​ሣል።


አሁ​ንም አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ አንተ በፊቴ እንደ ሄድህ ልጆ​ችህ በሕጌ ይሄዱ ዘንድ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ቢጠ​ብቁ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን የሚ​ቀ​መጥ ሰው በፊቴ አይ​ታ​ጣም ብለህ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ለባ​ሪ​ያህ ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት ጠብቅ፤ አጽ​ናም።


ከባ​ር​ያው ከዳ​ዊት ቤት የም​ን​ድ​ን​በ​ትን ቀንድ አስ​ነ​ሣ​ልን፤


በጨ​ለ​ማና በሞት ጥላ ለነ​በ​ሩት ብር​ሃ​ኑን ያሳ​ያ​ቸው ዘንድ፥ እግ​ሮ​ቻ​ች​ን​ንም ወደ ሰላም ጎዳና ያቀና ዘንድ ወጣ።”


跟着我们:

广告


广告