Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 21:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ወደ ይሁ​ዳም ወጡ፤ በረ​ቱ​ባ​ቸ​ውም፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ወን​ዶች ልጆ​ቹ​ንም፥ ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም ወሰዱ፤ ከታ​ና​ሹም ልጅ ከአ​ካ​ዝ​ያስ በቀር ልጅ አል​ቀ​ረ​ለ​ትም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እነርሱም በይሁዳ ላይ ወጡ፤ ወረሯትም። በንጉሡ ቤተ መንግሥት የሚገኘውን ዕቃ ሁሉ፣ ከወንዶች ልጆቹና ከሚስቶቹ ጋራ ወሰዱ፤ ከመጨረሻ ልጁ ከአካዝያስ በቀር አንድም ልጅ አልቀረለትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ወደ ይሁዳም ወጡ፥ ወረርዋትም፥ የንጉሡንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ወንዶች ልጆቹንም ሴቶች ልጆቹንም ማረኩ፤ ከታናሹም ልጅ ከአካዝያስ በቀር ልጅ አላስቀሩለትም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለዚህም ይሁዳን በመውረር ቤተ መንግሥቱን ዘረፉ፤ ከኢዮራም መጨረሻ ልጅ ከአካዝያስ በቀር የንጉሡን ሚስቶችና ወንዶች ልጆች ሁሉ እስረኞች አድርገው ወሰዱአቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ወደ ይሁዳም ወጡ፤ አፈረሱአትም፤ የንጉሡንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ወንዶች ልጆቹንም ሴቶች ልጆቹንም ማረኩ፤ ከታናሹም ልጅ ከአካዝያስ በቀር ልጅ አልቀረለትም።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 21:17
8 交叉引用  

ኢዩ ከይ​ሁዳ ንጉሥ ከአ​ካ​ዝ​ያስ ወን​ድ​ሞች ጋር ተገ​ና​ኝቶ፥ “እና​ንተ እነ​ማን ናችሁ?” አለ፤ እነ​ር​ሱም፥ “እኛ የይ​ሁዳ ንጉሥ የአ​ካ​ዝ​ያስ ወን​ድ​ሞች ነን፤ የን​ጉ​ሡ​ንና የእ​ቴ​ጌ​ዪ​ቱን ልጆች ደኅ​ን​ነት እን​ነ​ግ​ረው ዘንድ ወረ​ድን” አሉት።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የነ​በ​ሩት ታና​ሹን ልጁን አካ​ዝ​ያ​ስን በእ​ርሱ ፋንታ አነ​ገ​ሡት። የመ​ጣ​ባ​ቸው የዓ​ረ​ብና የአ​ሊ​ማ​ዞን የሽ​ፍ​ቶች ጭፍራ የእ​ር​ሱን ታላ​ቆች ወን​ድ​ሞች ገድ​ለ​ዋ​ቸው ነበ​ርና የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።


ከሶ​ር​ያም ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ ሶር​ያ​ው​ያን በሬ​ማት ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል ይታ​ከም ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ተመ​ለሰ፤ ታም​ሞም ነበ​ርና የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ የአ​ክ​ዓ​ብን ልጅ ኢዮ​ራ​ምን ያይ ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወረደ።


ጎቶ​ልያ ከሐ​ዲት ነበ​ረ​ችና ልጆ​ች​ዋም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ተቀ​ድሶ የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ለበ​ኣ​ሊም ሰጥ​ተ​ዋ​ልና።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​አስ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ልጅ የኢ​ዮ​አ​ስን ልጅ አሜ​ስ​ያ​ስን በቤ​ት​ሳ​ሚስ ይዞ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጣው፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጥር ከኤ​ፍ​ሬም በር ጀምሮ እስከ ማዕ​ዘኑ በር ድረስ አራት መቶ ክንድ አፈ​ረሰ።


ብሬ​ንና ወር​ቄን ወስ​ዳ​ች​ኋ​ልና፥ የተ​ወ​ደ​ደ​ው​ንም መል​ካ​ሙን ዕቃ​ዬን ወደ ቤተ መቅ​ደ​ሳ​ችሁ አግ​ብ​ታ​ች​ኋ​ልና፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በኤ​ዶ​ም​ያስ ይዘ​ጉ​ባ​ቸው ዘንድ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ምርኮ ማር​ከ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጋዛ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


跟着我们:

广告


广告