Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 20:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እን​ዲ​ህም አሉ፦ ክፉ ነገር፥ የፍ​ርድ ሰይፍ ወይም ቸነ​ፈር ወይም ራብ፥ ቢመ​ጣ​ብን በዚህ ቤት ፊትና በፊ​ትህ እን​ቆ​ማ​ለን፤ ስምህ በዚህ ቤት ላይ ነውና፤ በመ​ከ​ራ​ች​ንም ወደ አንተ እን​ጮ​ኻ​ለን፥ አን​ተም ሰም​ተህ ታድ​ነ​ና​ለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ‘የፍርድ ሰይፍም ሆነ የቸነፈር ወይም የራብ መከራ ቢደርስብን፣ ስምህ በተጠራበት በዚህ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት፣ በፊትህ ቆመን በጭንቀታችን ወደ አንተ እንጮሃለን፤ አንተም ትሰማናለህ፤ ታድነናለህም።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ‘ክፉ ነገር፥ ሰይፍ ወይም ፍርድ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን ስምህ ባለበት በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ ቆመን በመከራችን ወደ አንተ እንጮሃለን፥ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ።’

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ‘እኛን ለመቅጣት ጦርነትን፥ ቸነፈርን ወይም ራብን የመሳሰለውን መቅሠፍት ብታደርስብን የአንተ ስም ወደሚጠራበት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት መጥተን በመቆም ከመከራችን እንድታድነን ወደ አንተ እንጸልያለን፤ አንተም ጸሎታችንን ሰምተህ በመታደግ ታድነናለህ’ ብሎ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ‘ክፉ ነገር፥ የፍርድ ሰይፍ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን ስምህ ባለበት በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ ቆመን በመከራችን ወደ አንተ እንጮሃለን፤ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ’ አሉ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 20:9
13 交叉引用  

ባሪ​ያ​ህና ሕዝ​ብህ እስ​ራ​ኤል ወደ​ዚህ ስፍራ የሚ​ጸ​ል​ዩ​ትን ልመና ስማ፤ በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤ ሰም​ተ​ህም ይቅር በል።


“ሕዝ​ብህ እስ​ራ​ኤል አን​ተን ስለ በደሉ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት ድል ቢሆኑ፥ ወደ አን​ተም ቢመ​ለሱ፥ ለስ​ም​ህም ቢና​ዘዙ፥


“በም​ድር ላይም ራብ፥ ወይም ቸነ​ፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረ​ማሞ ቢሆን፥ አን​በጣ፥ ወይም ኩብ​ኩባ ቢመጣ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህም ጠላት ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው በአ​ን​ዲቱ ከብቦ ቢያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥


እነ​ርሱ ተቀ​መ​ጡ​ባት፤ ለስ​ም​ህም መቅ​ደ​ስን ሠሩ​ባት።


ባሪ​ያህ በዚህ ቤት የሚ​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦ በዚያ ስሜ ይሆ​ናል ወዳ​ል​ኸው ስፍራ፥ ወደ​ዚህ ቤት ዐይ​ኖ​ችህ ቀንና ሌሊት የተ​ገ​ለጡ ይሁኑ።


እርሱ፦ ሕዝ​ቤን ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ሁ​በት ጊዜ ጀምሮ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ በዚያ ለስሜ ቤት ይሠ​ራ​በት ዘንድ ከተ​ማን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም። በሕ​ዝቤ እስ​ራ​ኤል ላይም ይነ​ግሥ ዘንድ ሰውን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም።


ዕዝ​ራም እያ​ለ​ቀ​ሰና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እየ​ወ​ደቀ በጸ​ለ​የና በተ​ና​ዘዘ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ የወ​ን​ድና የሴት፥ የሕ​ፃ​ና​ትም እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰበ፤ ሕዝ​ቡም እጅግ አለ​ቀሱ።


አቤቱ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን ክፈት፥ አፌም ምስ​ጋ​ና​ህን ያወ​ራል።


ዐሥር አው​ታር ባለው በበ​ገና፥ ከም​ስ​ጋና ጋርም በመ​ሰ​ንቆ።


ከአ​ፈ​ርም መሠ​ዊያ ሥራ​ልኝ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን፥ በጎ​ች​ህ​ንም፥ በሬ​ዎ​ች​ህ​ንም ሠዋ​በት፤ ስሜን ባስ​ጠ​ራ​ሁ​በት ስፍራ ሁሉ ወደ አንተ መጥቼ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ።


ራስ​ህን ጠብቅ፤ ስማው፤ እን​ቢም አት​በ​ለው፤ ስሜ በእ​ርሱ ስለ ሆነ ይቅር አይ​ል​ምና።


ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።”


跟着我们:

广告


广告