Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 20:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥና ሕዝ​ቡም ምርኮ ይወ​ስዱ ዘንድ መጡ፤ ብዙ ከብ​ትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብ​ስም፥ እጅ​ግም ያማረ ዕቃ አገኙ፤ ማረ​ኩ​ትም፤ ምር​ኮ​ውም ብዙ ነበ​ርና ምር​ኮ​ውን እየ​ሰ​በ​ሰቡ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቈዩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ኢዮሣፍጥና ሰዎቹም ምርኳቸውን ለማጋዝ ሄዱ፤ በዚያም መካከል እጅግ ብዙ መሣሪያና ልብስ፣ ሊሸከሙ ከሚችሉትም በላይ ውድ ዕቃዎችን አገኙ። ምርኮውም ከመብዛቱ የተነሣ ለመሰብሰብ ሦስት ቀን ፈጀ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ኢዮሣፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ለመውሰድ መጡ፤ ብዙ ከብትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብስም፥ እጅግም ያማረ ዕቃ አገኙ፥ በዘበዙትም፥ ሁሉንም ለመሸከም አልቻሉም፤ ከምርኮውም ብዛት የተነሣ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ይበዘብዙ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ከዚህ በኋላ ኢዮሣፍጥና ወታደሮቹ ምርኮ ለመውሰድ ወደዚያ ሄዱ፤ ብዙ የቀንድ ከብት፥ ስንቅና ትጥቅ፥ ልብስና ሌላም ውድ የሆኑ ዕቃዎች አገኙ፤ ምርኮውንም ለመሰብሰብ ሦስት ቀን ፈጀባቸው፤ ነገር ግን ምርኮው እጅግ ብዙ ስለ ነበር ሁሉንም መውሰድ አልቻሉም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ኢዮሣፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ይወስዱ ዘንድ መጡ፤ ብዙ ከብትና ልዩ ልዩ ዕቃ፥ ልብስ፥ እጅግም ያማረ ዕቃ አገኙ፤ በዘበዙትም፤ ሁሉንም ይሸከሙ ዘንድ አልቻሉም፤ ከምርኮውም ብዛት የተነሣ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ይበዘብዙ ነበር።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 20:25
15 交叉引用  

የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ወደ ምድረ በዳው መጠ​በ​ቂያ ግንብ በመጡ ጊዜ ሕዝ​ቡን አዩ፤ እነ​ሆም፥ በም​ድሩ ሁሉ ሬሳ ሞልቶ ነበር፤ ያመ​ለ​ጠም ሰው አል​ነ​በ​ረም።


በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ቀን በበ​ረ​ከት ሸለቆ ውስጥ ተሰ​በ​ሰቡ፤ በዚ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ፤ ስለ​ዚ​ህም ያ ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ የበ​ረ​ከት ሸለቆ ተባለ።


በደጅ የሚ​ቀ​መጡ በእኔ ይጫ​ወ​ታሉ፤ ወይን የሚ​ጠ​ጡም በእኔ ይዘ​ፍ​ናሉ።


ነገር ግን እያ​ን​ዳ​ን​ዲቱ ሴት ከጎ​ረ​ቤቷ፥ በቤ​ቷም ካለ​ችው ሴት የብር ዕቃ፥ የወ​ርቅ ዕቃ፥ ልብ​ስም ትዋ​ሳ​ለች፤ በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ችሁ ላይም ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም ትበ​ዘ​ብ​ዛ​ላ​ችሁ።”


ዋጋው ብዙ ከሆነ ዕንቍም የከበረች ናት። ክፉ ነገር አይቃወማትም፥ ለሚቀርቧትም መልካም ናት። ክብርም ሁሉ አይተካከላትም።


ይሁዳም ደግሞ በኢየሩሳሌም ውስጥ ሆኖ ይዋጋል፣ በዙሪያም ያሉት የአሕዛብ ሁሉ ሀብት እጅግ ብዙ ወርቅና ብር ልብስም ይሰበሰባል።


ሙሴም አላ​ቸው፥ “ሴቶ​ችን ሁሉ ለምን አዳ​ና​ች​ኋ​ቸው?


ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ሁሉ የማ​ረ​ኩ​ትን ለየ​ራ​ሳ​ቸው ወሰዱ።


ነገር ግን በወ​ደ​ደን በእ​ርሱ ሁሉን ድል እን​ነ​ሣ​ለን።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የእ​ነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች ምርኮ ሁሉ፥ ከብ​ቶ​ቹ​ንም ለራ​ሳ​ቸው ዘረፉ፤ ሰዎ​ቹን ሁሉ ግን እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በሰ​ይፍ ስለት መቱ​አ​ቸው፤ እስ​ት​ን​ፋስ ያለ​ው​ንም ሁሉ አን​ድም አላ​ስ​ቀ​ሩም።


跟着我们:

广告


广告