Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 20:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 የአ​ሞ​ንና የሞ​ዓብ ልጆ​ችም በሴ​ይር ተራራ በሚ​ኖ​ሩት ላይ ፈጽ​መው ይገ​ድ​ሉ​አ​ቸው ዘንድ፥ ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ ተነ​ሥ​ተ​ው​ባ​ቸው ነበር፤ በሴ​ይ​ርም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ካጠፉ በኋላ እርስ በር​ሳ​ቸው ሊጠ​ፋፉ ተነሡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 የአሞንና የሞዓብ ሰዎችም የሴይርን ተራራ ሰዎች ለማጥፋትና ለመደምሰስ ተነሡባቸው። ከሴይር የመጡትን ሰዎች ካጠፉ በኋላም፣ እርስ በርስ ተጠፋፉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 የአሞንና የሞዓብም ልጆችም በሴይርም ተራራ በሚኖሩት ላይ ፈጽመው ሊገድሉአቸውና ሊያጠፉአቸውም ተነሥተውባቸው ነበር፤ በሴይርም የሚኖሩትን ካጠፉ በኋላ አንዱ ሌላውን በማገዝ እርስ በርስ ተጠፋፉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ስለዚህ ዐሞናውያንና ሞአባውያን በኤዶማውያን ሠራዊት ላይ አደጋ ጥለው በሙሉ ደመሰሱአቸው፤ ከዚያም በመቀጠል በጭካኔ እርስ በርሳቸው ተፋጁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 የአሞንና የሞዓብም ልጆችም በሴይርም ተራራ በሚኖሩት ላይ ፈጽመው ይገድሉአቸው ዘንድ ያጠፉአቸውም ዘንድ ተነሥተውባቸው ነበር፤ በሴይርም የሚኖሩትን ካጠፉ በኋላ እያንዳንዱ ባልንጀራውን ለማጥፋት ተረዳዳ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 20:23
12 交叉引用  

በሴ​ይር ተራ​ራ​ዎች ያሉ የኬ​ሬ​ዎስ ሰዎ​ች​ንም በበ​ረሃ አጠ​ገብ እስከ አለ​ችው እስከ ፋራን ዛፍ ድረስ መቱ​አ​ቸው።


የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ወደ ምድረ በዳው መጠ​በ​ቂያ ግንብ በመጡ ጊዜ ሕዝ​ቡን አዩ፤ እነ​ሆም፥ በም​ድሩ ሁሉ ሬሳ ሞልቶ ነበር፤ ያመ​ለ​ጠም ሰው አል​ነ​በ​ረም።


በእ​ነ​ዚ​ያም ዘመ​ናት የኤ​ዶ​ም​ያስ ሰዎች በይ​ሁዳ ላይ ዐመፁ፤ ለራ​ሳ​ቸ​ውም ንጉሥ አነ​ገሡ።


“ግብ​ፃ​ው​ያን በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ይነ​ሣሉ፤ ወን​ድ​ምም ወን​ድ​ሙን፥ ሰውም ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ይገ​ድ​ላል፤ ከተ​ማም ከተ​ማን፥ መን​ግ​ሥ​ትም መን​ግ​ሥ​ትን ይወ​ጋል።


በተ​ራ​ሮ​ችም ሁሉ በእ​ርሱ ላይ ፍር​ሀ​ትን እጠ​ራ​ለሁ፤ የሰ​ውም ሁሉ ሰይፍ በወ​ን​ድሙ ላይ ይሆ​ናል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለሁ፥ የአሕዛብንም መንግሥታት ኃይል አጠፋለሁ፣ ሰረገሎችንና የሚቀመጡባቸውንም እገለብጣለሁ፣ ፈረሶችና ፈረሰኞቻቸውም እያንዳንዳቸው በወንድማቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።


የሴ​ይ​ርን ተራራ ለዔ​ሳው ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከም​ድ​ራ​ቸው የጫማ መር​ገጫ ታህል እን​ኳን አል​ሰ​ጣ​ች​ሁ​ምና አት​ጣ​ሉ​አ​ቸው።


ለይ​ስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብ​ንና ዔሳ​ውን ሰጠ​ሁት፤ ለዔ​ሳ​ውም የሴ​ይ​ርን ተራራ ርስት አድ​ርጌ ሰጠ​ሁት፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚ​ያም ታላቅ ሕዝብ ሆኑ፤ በዙም፤ በረ​ቱም፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም መከራ አጸ​ኑ​ባ​ቸው።


ሦስ​ቱ​ንም መቶ ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ችን ነፉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ውን ሁሉ ሰይፍ በባ​ል​ን​ጀ​ራ​ዉና በሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ ላይ አደ​ረገ፤ ሠራ​ዊ​ቱም በጽ​ሬራ በኩል እስከ ቤት​ሲጣ ጋራ​ጋታ ድረስ በጣ​ባት አጠ​ገብ እስ​ካ​ለው እስከ አቤ​ል​ሜ​ሁላ ዳርቻ ድረስ ሸሸ።


ሳኦ​ልና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ ውጊ​ያው መጡ፤ እነ​ሆም፥ የእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ሰይፍ በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ነበረ፤ እጅ​ግም ታላቅ ሽብር ሆነ።


跟着我们:

广告


广告