Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 20:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሰዎ​ችም መጥ​ተው፥ “ከባ​ሕሩ ማዶ ከሶ​ርያ ታላቅ ሠራ​ዊት መጥ​ቶ​ብ​ሃል፤ እነ​ሆም፥ ዓይ​ን​ጋዲ በተ​ባ​ለች በሐ​ሴ​ሶን ታማር ናቸው” ብለው ለኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ነገ​ሩት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ሰዎችም መጥተው ኢዮሣፍጥን፣ “ግዙፍ ሰራዊት ሊወጋህ ከሙት ባሕር ወዲያ ካለው ከኤዶም መጥቶብሃል፤ እነሆም፣ ሐሴሶን ታማር በተባለው በዓይንጋዲ ናቸው” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሰዎችም መጥተው እንዲህ በማለት ለኢዮሣፍጥ አወሩለት፦ “ከባሕሩ ማዶ ከሶሪያ ታላቅ ሠራዊት መጥቶብሃል፤ እነሆም፥ ዐይን-ጋዲ በተባለች በሐሴሶን ታማር ይገኛሉ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ሰዎች መጥተው ለንጉሥ ኢዮሣፍጥ “በአንተ ላይ አደጋ ለመጣል እጅግ ብዙ የሆነ ሠራዊት ከሙት ባሕር ባሻገር ካለው ከኤዶም ምድር መጥቶብሃል፤ እነሆ ሐጸጾንታማርን ቀደም ሲል በድል አድራጊነት ይዘዋል” ሲሉ ነገሩት፤ (ሐጸጾንታማር የዔንገዲ ሌላ መጠሪያ ስሙ ነው፤)

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ወሬኞችም መጥተው “ከባሕሩ ማዶ ከሶሪያ ታላቅ ሠራዊት መጥቶብሃል፤ እነሆም፥ ዓይንጋዲ በተባለች በሐሴሶን ታማር ናቸው” ብለው ለኢዮሳፍጥ ነገሩት።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 20:2
10 交叉引用  

እነ​ዚህ ሁሉ በኤ​ሌ​ቄን ሸለቆ ተሰ​ብ​ስ​በው ተባ​በሩ፤ ይኸ​ውም የጨው ባሕር ነው።


ተመ​ል​ሰ​ውም ቃዴስ ወደ ተባ​ለች ወደ ፍርድ ምንጭ መጡ፤ የአ​ማ​ሌ​ቅን አለ​ቆች ሁሉና በአ​ሳ​ሶን ታማር የሚ​ኖሩ አሞ​ራ​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ሉ​አ​ቸው።


ልጅ ወን​ድሜ ለእኔ በዐ​ይ​ን​ጋዲ ወይን ቦታ እን​ዳለ እንደ አበባ ዕቅፍ ነው።


ዓሣ አጥ​ማ​ጆ​ችም ከዓ​ይ​ን​ጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይ​ን​ኤ​ግ​ላ​ይም ድረስ በዚያ ይቆ​ማሉ። ያም መረብ መዘ​ር​ጊያ ይሆ​ናል፤ ዓሣ​ዎ​ችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣ​ዎች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው እጅግ ይበ​ዛሉ።


የደ​ቡ​ቡም ድን​በር ከታ​ማር ጀምሮ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብፅ ወንዝ እስከ ታላቁ ባሕር ይሆ​ናል። የደ​ቡ​ቡም ድን​በር ይህ ነው።


ከጋ​ድም ድን​በር ቀጥሎ በደ​ቡብ በኩል ድን​በሩ ከታ​ማር ጀምሮ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውኃ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ይሆ​ናል።


ዳር​ቻ​ውም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ይወ​ር​ዳል፤ መው​ጫ​ውም በጨው ባሕር ይሆ​ናል። ምድ​ራ​ችሁ እንደ ዳር​ቻዋ በዙ​ሪ​ያዋ ይህች ናት።”


ናፍ​ላ​ዛ​ንና ከተ​ሞ​ቻ​ቸው፥ ሳዶን፥ አቃ​ዴስ፥ ሰባት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።


ከላይ የሚ​ወ​ር​ደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀር​ያ​ት​ያ​ርም አው​ራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድ​ግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚ​ወ​ር​ደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝ​ቡም በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ።


跟着我们:

广告


广告