Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 20:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይሁዳ ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የም​ት​ኖሩ፥ አን​ተም ንጉሡ ኢዮ​ሣ​ፍጥ! ስሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ች​ኋል፦ ሰልፉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ የእ​ና​ንተ አይ​ደ​ለ​ምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተ​ነሣ አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጡም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እርሱም እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ ኢዮሣፍጥ፣ እናንተም በይሁዳና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ! እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል፤ ‘ውጊያው የእግዚአብሔር እንጂ የእናንተ አይደለምና፣ ከዚህ ታላቅ ሰራዊት የተነሣ አትፍሩ፤ አትደንግጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እንዲህም አለ፦ “ይሁዳ ሁሉ፥ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ፥ አንተም ንጉሡ ኢዮሣፍጥ፥ ስሙ፤ ጌታ እንዲህ ይላችኋል፦ ‘ውግያው የጌታ ነው እንጂ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሣ አትፍሩ፥ አትደንግጡም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ያሐዚኤልም እንዲህ አለ፦ “ንጉሥ ሆይ! እናንተም የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በሙሉ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ተስፋ አትቊረጡ፤ ይህንንም ታላቅ ሠራዊት ለመቋቋም አትፍሩ፤ ጦርነቱ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እንዲህም አለ “ይሁዳ ሁሉ፥ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ፥ አንተም ንጉሡ ኢዮሣፍጥ፥ ስሙ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል ‘ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሣ አትፍሩ፤ አትደንግጡም።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 20:15
18 交叉引用  

ሁለ​ቱም የዐ​መፅ ልጆች የሆኑ ሰዎች ገብ​ተው በፊቱ ቆሙ፤ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ንጉ​ሡን ሰድ​በ​ሃል” ብለው መሰ​ከ​ሩ​በት። የዚያ ጊዜም ከከ​ተማ አው​ጥ​ተው በድ​ን​ጋይ ደብ​ድ​በው ገደ​ሉት።


ነገ በእ​ነ​ርሱ ላይ ውረዱ፤ እነሆ፥ በአ​ሲስ ዐቀ​በት ይወ​ጣሉ፤ በሸ​ለ​ቆ​ውም መጨ​ረሻ በኢ​ያ​ር​ሔል ምድረ በዳ ፊት ለፊት ታገ​ኙ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።


አይ​ችም ተነ​ሣሁ፤ ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹ​ንም፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ሕዝብ፥ “አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው፤ ታላ​ቁ​ንና የተ​ፈ​ራ​ውን አም​ላ​ካ​ች​ንን አስቡ፤ ስለ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም፥ ስለ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ ስለ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁም፥ ስለ ቤቶ​ቻ​ች​ሁም ተዋጉ” አል​ኋ​ቸው።


እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም ሩጫ ለፈ​ጣ​ኖች፥ ጦር​ነ​ትም ለኀ​ያ​ላን፥ እን​ጀ​ራም ለጠ​ቢ​ባን፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትም ለአ​ስ​ተ​ዋ​ዮች፥ ሞገ​ስም ለዐ​ዋ​ቂ​ዎች እን​ዳ​ል​ሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገ​ና​ኛ​ቸ​ዋል።


ኢሳ​ይ​ያስ፥ “ለጌ​ታ​ችሁ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ሦር ንጉሥ ባሪ​ያ​ዎች ስለ ሰደ​ቡኝ፥ ስለ ሰማ​ኸው ቃል አት​ፍራ።


“ጠላ​ቶ​ች​ህን ለመ​ው​ጋት በወ​ጣህ ጊዜ፥ ፈረ​ሶ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ሕዝ​ቡ​ንም ከአ​ንተ ይልቅ በዝ​ተው ባየህ ጊዜ፥ ከግ​ብፅ ሀገር ያወ​ጣህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና አት​ፍ​ራ​ቸው።


ከእ​ና​ንተ ጋር የሚ​ሄድ፥ ያድ​ና​ች​ሁም ዘንድ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ስለ እና​ንተ የሚ​ወጋ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና።


ጽና፤ በርታ፤ አት​ፍራ፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አት​ደ​ን​ግጥ፤ አት​ድ​ከም፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ከአ​ንተ ጋር ይሄ​ዳል፤ አይ​ጥ​ል​ህም፤ አይ​ተ​ው​ህ​ምም።


በፊ​ት​ህም የሚ​ሄድ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ከአ​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ አይ​ጥ​ል​ህም፤ አይ​ተ​ው​ህም፤ አት​ፍራ፤ አት​ደ​ን​ግጥ’ ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ይሞቱ ዘንድ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና አት​ፍ​ራ​ቸው፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን ቋንጃ ትቈ​ር​ጣ​ለህ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ” አለው።


ሁሉም በየ​ቦ​ታው፥ በሰ​ፈሩ ዙሪያ ቆመ፤ ሠራ​ዊ​ቱም ሁሉ ደን​ግ​ጠው ሸሹ።


ይህም ጉባኤ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ይ​ፍና በጦር የሚ​ያ​ድን እን​ዳ​ይ​ደለ ያው​ቃል። ሰልፉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እና​ን​ተን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።”


跟着我们:

广告


广告