Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አሁ​ንም በወ​ር​ቅና በብር፥ በና​ስና በብ​ረት፥ በሐ​ም​ራ​ዊና በቀይ፥ በሰ​ማ​ያ​ዊም ግምጃ መለ​በጥ የሚ​ች​ልና፥ አባቴ ዳዊት ካዘ​ጋ​ጃ​ቸው በእኔ ዘንድ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ካሉት ብል​ሃ​ተ​ኞች ጋር ቅርጽ ማው​ጣት የሚ​ያ​ውቅ ብል​ሃ​ተኛ ሰውን ላክ​ልኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ስለዚህ አንተ በወርቅና በብር፣ በናስና በብረት፣ በሐምራዊና በደማቅ ቀይ፣ በሰማያዊም ግምጃ ሥራ ዕውቀት ያለውን እንዲሁም አባቴ ዳዊት ካዘጋጃቸው ከእኔ የእጅ ባለሙያዎች ጋራ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የቅርጻ ቅርጽ ጥበብ ሥራ የሚሠራ ሰው ላክልኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አሁንም አባቴ ዳዊት ካዘጋጃቸው በእኔ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ካሉት ብልሃተኞች ጋር አብሮ የሚሆን፥ ወርቁንና ብሩን፥ ናሱንና ብረቱን፥ ሐምራዊውንና ቀዩን ሰማያዊውንም ግምጃ የሚሠራ፥ ቅርጽንም የሚያውቅ ብልሃተኛ ሰው ላክልኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እንግዲህ ቅርጽን የማውጣት፥ ወርቅን፥ ብርን፥ ነሐስንና ብረትን የማቅለጥ፥ ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ልብስ የመሥራት ችሎታ ያለውን ብልኀተኛ ሰው ላክልኝ፤ እርሱም አባቴ ዳዊት ከመረጣቸው በይሁዳና በኢየሩሳሌም ካሉት ብልኀተኞች ሰዎች ጋር ይሠራል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አሁንም አባቴ ዳዊት ካዘጋጃቸው በእኔ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ካሉት ብልሃተኞች ጋር የሚሆን፥ ወርቁንና ብሩን፥ ናሱንና ብረቱን፥ ሐምራዊውንና ቀዩን ሰማያዊውንም ግምጃ የሚሠራ፥ ቅርጽንም የሚያውቅ ብልሃተኛ ሰው ላክልኝ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 2:7
9 交叉引用  

ከኦ​ፌ​ርም ወርቅ ያመ​ጣች የኪ​ራም መር​ከብ እጅግ ብዙ የተ​ጠ​ረበ እን​ጨ​ትና የከ​በረ ዕንቍ አመ​ጣች።


እር​ሱም ከን​ፍ​ታ​ሌም ወገን የነ​በ​ረች የባል አልባ ሴት ልጅ ነበረ፤ አባ​ቱም የጢ​ሮስ ሰው ናስ ሠራ​ተኛ ነበረ፤ የና​ስ​ንም ሥራ ሁሉ ይሠራ ዘንድ በጥ​በ​ብና በማ​ስ​ተ​ዋል፥ በብ​ል​ሃ​ትም ተሞ​ልቶ ነበር። ወደ ንጉ​ሡም ወደ ሰሎ​ሞን መጥቶ ሥራ​ውን ሁሉ ሠራ።


ምድ​ርም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍርድ ተምራ ደስ ይላ​ታል።


ይህም ደግሞ ድንቅ ምክ​ርን ከሚ​መ​ክር በግ​ብ​ሩም ገናና ከሆ​ነው ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወጥ​ቶ​አል። እና​ንተ ግን ከንቱ መጽ​ና​ና​ትን ታበዙ ዘንድ ትሻ​ላ​ችሁ።


በቍ​ጣዬ ቀሥፌ በይ​ቅ​ር​ታዬ አቅ​ር​ቤ​ሻ​ለ​ሁና መጻ​ተ​ኞች ቅጥ​ር​ሽን ይሠ​ራሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም በፊ​ትሽ ይቆ​ማሉ።


ሳን​ቃ​ዎ​ች​ሽን ሁሉ ከሳ​ኔር ጥድ ሠር​ተ​ዋል፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ሽ​ንም ይሠ​ሩ​ልሽ ዘንድ ከሊ​ባ​ኖስ ዝግ​ባን ወስ​ደ​ዋል።


跟着我们:

广告


广告