Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እኛም ከሊ​ባ​ኖስ የም​ት​ሻ​ውን ያህል እን​ጨት እን​ቈ​ር​ጣ​ለን፤ በታ​ን​ኳም አድ​ር​ገን በባ​ሕር ላይ ወደ አንተ ወደ ኢዮጴ እን​ል​ካ​ለን፤ አን​ተም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ታስ​ወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እኛም የሚያስፈልግህን ግንድ ሁሉ ከሊባኖስ ቈርጠንና አስረን እስከ ኢዮጴ ድረስ ቍልቍል በማንሳፈፍ እንሰድድልሃለን፤ አንተም ወደ ኢየሩሳሌም ታስወስደዋለህ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እኛም ከሊባኖስ የምትሻውን ያህል እንጨት እንቈርጣለን፥ በታንኳም አድርገን በባሕር ላይ ወደ አንተ ወደ ኢዮጴ እናመጣለን፤ አንተም ወደ ኢየሩሳሌም ታስወስደዋለህ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እኛም የምትፈልገውን ግንድ ሁሉ ከሊባኖስ ተራራዎች ቈርጠን አንድ ላይ በማሰር በባሕር ላይ ተንሳፍፎ እስከ ኢዮጴ እንዲደርስ እናደርጋለን፤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ልትወስደው ትችላለህ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እኛም ከሊባኖስ የምትሻውን ያህል እንጨት እንቈርጣለን፤ በታንኳም አድርገን በባሕር ላይ ወደ አንተ ወደ ኢዮጴ እንሰድዳለን፤ አንተም ወደ ኢየሩሳሌም ታስወስደዋለህ።”

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 2:16
15 交叉引用  

ዳዊ​ትም በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር የነ​በ​ሩ​ትን መጻ​ተ​ኞች ይሰ​በ​ስቡ ዘንድ አዘዘ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ለመ​ሥ​ራት የሚ​ወ​ቀ​ሩ​ትን ድን​ጋ​ዮች ይወ​ቅሩ ዘንድ ጠራ​ቢ​ዎ​ችን አኖረ።


የይ​ሁ​ዳም ጉባኤ ሁሉ ፥ ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የመጡ ጉባኤ ሁሉ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገር የመ​ጡ​ትና በይ​ሁዳ የኖ​ሩት እን​ግ​ዶች ደስ አላ​ቸው።


ከኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ከአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ከፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ከኤ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ከኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም የቀ​ሩ​ትን፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ያል​ሆ​ኑ​ትን ሕዝብ ሁሉ፥


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ያላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውን፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም በም​ድር ላይ የቀ​ሩ​ትን ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ሰሎ​ሞን እስከ ዛሬ ድረስ ገባ​ሮች አደ​ረ​ጋ​ቸው።


ለጠ​ራ​ቢ​ዎ​ችና ለአ​ና​ጢ​ዎ​ችም ብር ሰጡ፤ የፋ​ር​ስም ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀ​ደ​ላ​ቸው የዝ​ግባ ዛፍ ከሊ​ባ​ኖስ በባ​ሕር ወደ ኢዮጴ ያመጡ ዘንድ ለሲ​ዶ​ናና ለጢ​ሮስ ሰዎች መብ​ልና መጠጥ፥ ዘይ​ትም ሰጡ።


ዮናስ ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ተር​ሴስ ይሸሽ ዘንድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮ​ጴም ወረደ፤ ወደ ተር​ሴ​ስም የም​ታ​ልፍ መር​ከብ አገኘ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ኰብ​ልሎ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወደ ተር​ሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እር​ስዋ ገባ።


ሁሉም በእ​ርሱ ሆነ፤ ከሆ​ነ​ውም ሁሉ ያለ እርሱ ምንም የሆነ የለም።


አሁ​ንም ወደ ኢዮጴ ከተማ ላክና በባ​ሕር አቅ​ራ​ቢያ ባለ​ችው በቍ​ር​በት ፋቂው በስ​ም​ዖን ቤት የሚ​ኖ​ረ​ውን ጴጥ​ሮስ የተ​ባ​ለ​ውን ስም​ዖ​ንን ይጥ​ሩ​ልህ፤ እርሱ መጥቶ የም​ት​ድ​ን​በ​ትን ይነ​ግ​ር​ሃል።


በኢ​ዮጴ ሀገ​ርም ጣቢታ የም​ት​ባል አን​ዲት ደቀ መዝ​ሙር ነበ​ረች፤ በት​ር​ጓ​ሜ​ውም ዶር​ቃስ ይሉ​አ​ታል፤ ፌቆ ማለት ነው፤ እር​ስ​ዋም ብዙ ደጋግ ሥራ ትሠራ ነበር፤ ምጽ​ዋ​ትም ትሰጥ ነበር።


ልዳም ለኢ​ዮጴ ቅርብ ነበ​ርና ደቀ መዛ​ሙ​ርት ጴጥ​ሮስ በዚያ እን​ዳለ ሰም​ተው ወደ እነ​ርሱ መም​ጣት እን​ዳ​ይ​ዘ​ገይ ይማ​ል​ዱት ዘንድ ሁለት ሰዎ​ችን ወደ እርሱ ላኩ።


በኢ​ዮ​ጴም ያሉ ሁሉ ይህን ሰሙ፤ ብዙ​ዎ​ችም በጌ​ታ​ችን አመኑ።


ጴጥ​ሮ​ስም በኢ​ዮጴ በቍ​ር​በት ፋቂው በስ​ም​ዖን ቤት ብዙ ቀን ተቀ​መጠ።


በባ​ሕር በኩል በኢ​ዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ኢያ​ራ​ቆን።


በዚ​ያም ቀን ኢያሱ እነ​ር​ሱን ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ እን​ጨት ቈራ​ጮ​ችና ውኃ ቀጂ​ዎች አደ​ረ​ጋ​ቸው። ስለ​ዚ​ህም የገ​ባ​ዖን ሰዎች ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ረ​ጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ጨት ቈራ​ጮች፥ ውኃም ቀጂ​ዎች ሆኑ።


跟着我们:

广告


广告