Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 18:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አክ​ዓብ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ከእኔ ጋር ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ትሄ​ዳ​ለ​ህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝ​ቤም ለሰ​ልፍ እንደ ሕዝ​ብህ ናቸው፤” ብሎ መለ​ሰ​ለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የእስራኤል ንጉሥ አክዓብም የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፣ “ራሞት ገለዓድን ለመውጋት ዐብረኸኝ ትሄዳለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮሣፍጥም፣ “እኔ እንደ አንተው ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ ነው፤ በጦርነቱ ዐብረናችሁ እንሰለፋለን” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የእስራኤልም ንጉሥ አክዓብ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፦ “ከእኔ ጋር ወደ ሬማት ዘገለዓድ ትሄዳለህን?” አለው። እርሱም፦ “እኔ እንደ አንተ ነኝ፥ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ ናቸው፤ በጦርነቱም ላይ ከአንተ ጋር እንሆናለን” ብሎ መለሰለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “በራሞት ላይ አደጋ ለመጣል ከእኔ ጋር ትዘምታለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮሣፍጥም “እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ ነው፤ በጦርነቱም እንተባበርሃለን አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የእስራኤልም ንጉሥ አክዓብ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን “ከእኔ ጋር ወደ ሬማት ዘገለዓድ ትሄዳለህን?” አለው። እርሱም“እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ ናቸው፤ በሰልፍም ከአንተ ጋር እንሆናለን” ብሎ መለሰለት።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 18:3
9 交叉引用  

የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ እን​ዋጋ ዘንድ ከእኔ ጋር ትዘ​ም​ታ​ለ​ህን?” አለው። ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ለእ​ስ​ራ​እል ንጉሥ፥ “እኔ እንደ አንተ፥ ሕዝ​ቤም እንደ ሕዝ​ብህ፥ ፈረ​ሶቼም እንደ ፈረ​ሶ​ችህ ናቸው” አለው።


በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ የጌ​ቤር ልጅ ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም በገ​ለ​ዓድ ያሉት የም​ናሴ ልጅ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ነበሩ፤ ለእ​ር​ሱም ደግሞ በባ​ሳን፥ በአ​ር​ጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥ​ርና የናስ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች የነ​በ​ረ​ባ​ቸው ስድሳ ታላ​ላቅ ከተ​ሞች ነበ​ሩ​በት፤


ወደ ይሁ​ዳም ንጉሥ ወደ ኢዮ​ሣ​ፍጥ፥ “የሞ​ዓብ ንጉሥ ከዳኝ፤ ከእኔ ጋር በሞ​ዓብ ላይ ለሰ​ልፍ ትሄ​ዳ​ለ​ህን?” ብሎ፤ ላከ። እር​ሱም፥ “እወ​ጣ​ለሁ፤ እኔ እንደ አንተ፥ አን​ተም እንደ እኔ፥ ሕዝ​ቤም እንደ ሕዝ​ብህ፥ ፈረ​ሶ​ቼም እንደ ፈረ​ሶ​ችህ ናቸው” አለ።


ከጥ​ቂት ዓመ​ታት በኋ​ላም ወደ አክ​ዓብ ወደ ሰማ​ርያ ወረደ። አክ​ዓ​ብም ለእ​ር​ሱና ከእ​ርሱ ጋር ለነ​በ​ሩት ሕዝብ ብዙ በጎ​ች​ንና በሬ​ዎ​ችን አረደ፤ ወደ​ደ​ውም፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ይሄድ ዘንድ አባ​በ​ለው።


ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ፥ “ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይቅ” አለው።


ነቢዩ የአ​ናኒ ልጅ ኢዩ ሊገ​ና​ኘው ወጣ፤ ንጉ​ሡ​ንም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ታግ​ዛ​ለ​ህን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጠ​ላ​ውን ትወ​ድ​ዳ​ለ​ህን? ስለ​ዚ​ህም ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ቍጣ መጥ​ቶ​ብ​ሃል።


የሥራ ፍሬ ከሌ​ላ​ቸው፥ ሁለ​ን​ተ​ና​ቸ​ውም ጨለማ ከሆነ ሰዎች ጋር አት​ተ​ባ​በሩ፤ ገሥ​ጹ​አ​ቸው እንጂ።


跟着我们:

广告


广告