Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 18:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ከጥ​ቂት ዓመ​ታት በኋ​ላም ወደ አክ​ዓብ ወደ ሰማ​ርያ ወረደ። አክ​ዓ​ብም ለእ​ር​ሱና ከእ​ርሱ ጋር ለነ​በ​ሩት ሕዝብ ብዙ በጎ​ች​ንና በሬ​ዎ​ችን አረደ፤ ወደ​ደ​ውም፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ይሄድ ዘንድ አባ​በ​ለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከጥቂት ዓመታት በኋላም አክዓብን ሊጐበኝ ወደ ሰማርያ ወረደ። አክዓብም ለርሱና ዐብሮት ለነበረው ሕዝብ ብዙ በግና በሬ ዐረደ፤ ከዚያም በራሞት ገለዓድ ላይ አደጋ እንዲጥል አግባባው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከጥቂት ዓመት በኋላም ወደ አክዓብ ወደ ሰማርያ ወረደ። አክዓብም ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሕዝብ ብዙ በጎችና በሬዎችን አረደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ሬማት ዘገለዓድ እንዲሄድ አባበለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከጥቂት ዓመቶች በኋላም ኢዮሣፍጥ አክዓብን ለመጐብኘት ወደ ሰማርያ ከተማ ሄደ፤ አክዓብም ለኢዮሣፍጥና ለአጃቢዎቹ ክብር ብዙ በጎችንና የቀንድ ከብቶችን ዐርዶ ታላቅ ግብዣ አደረገ፤ አክዓብ በገለዓድ በሚገኘው በራሞት ከተማ ላይ አደጋ ለመጣል ይተባበረው ዘንድ ኢዮሣፍጥን አግባባው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ከጥቂት ዓመት በኋላም ወደ አክዓብ ወደ ሰማርያ ወረደ። አክዓብም ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሕዝብ ብዙ በጎችና በሬዎችን አረደ፤ ከእርሱም ጋር ወደ ሬማት ዘገለዓድ ይሄድ ዘንድ አባበለው።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 18:2
12 交叉引用  

አዶ​ን​ያ​ስም በጎ​ች​ንና በሬ​ዎ​ችን፥ ጠቦ​ቶ​ች​ንም በሮ​ጌል ምንጭ አጠ​ገብ ባለ​ችው በዞ​ሔ​ሌት ድን​ጋይ ዘንድ ሠዋ፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ፥ የን​ጉ​ሡ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ኀያ​ላን ሁሉ ጠራ።


ከብዙ ቀንም በኋላ በም​ድር ላይ ዝናብ አል​ነ​በ​ረ​ምና ፈፋው ደረቀ።


በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ የጌ​ቤር ልጅ ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም በገ​ለ​ዓድ ያሉት የም​ናሴ ልጅ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ነበሩ፤ ለእ​ር​ሱም ደግሞ በባ​ሳን፥ በአ​ር​ጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥ​ርና የናስ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች የነ​በ​ረ​ባ​ቸው ስድሳ ታላ​ላቅ ከተ​ሞች ነበ​ሩ​በት፤


ነቢ​ዩም ኤል​ሳዕ ከነ​ቢ​ያት ልጆች አን​ዱን ጠርቶ እን​ዲህ አለው፥ “ወገ​ብ​ህን ታጥ​ቀህ ይህን የዘ​ይት ቀንድ በእ​ጅህ ያዝ፤ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓ​ድም ሂድ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አክ​ዓብ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ከእኔ ጋር ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ትሄ​ዳ​ለ​ህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝ​ቤም ለሰ​ልፍ እንደ ሕዝ​ብህ ናቸው፤” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ነቢዩ የአ​ናኒ ልጅ ኢዩ ሊገ​ና​ኘው ወጣ፤ ንጉ​ሡ​ንም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ታግ​ዛ​ለ​ህን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጠ​ላ​ውን ትወ​ድ​ዳ​ለ​ህን? ስለ​ዚ​ህም ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ቍጣ መጥ​ቶ​ብ​ሃል።


እኔ ግን በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሠ​ላሳ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት ወደ ንጉሡ ሄጄ ነበ​ርና በዚህ ጊዜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አል​ነ​በ​ር​ሁም። ከጥ​ቂት ዘመ​ንም በኋላ የን​ጉ​ሡን ፈቃድ ለመ​ንሁ፤


ለሮ​ቤል ነገድ በም​ድረ በዳ በደ​ል​ዳላ ስፍራ ያለ ባሶር፥ ለጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ያለ ራሞት፥ ለም​ና​ሴም ነገድ በባ​ሳን ያለ ጎላን ነበሩ።


በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ከኢ​ያ​ሪኮ ወደ ምሥ​ራቅ ከሮ​ቤል ነገድ በም​ድረ በዳው በደ​ል​ዳ​ላው ስፍራ ቦሶ​ርን፥ ከጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ኤር​ሞ​ትን፥ ከም​ና​ሴም ነገድ በባ​ሳን ጎላ​ንን ለዩ።


跟着我们:

广告


广告