Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 18:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሚክ​ያ​ስ​ንም ሊጠራ የሄደ መል​እ​ክ​ተኛ፥ “እነሆ፥ ነቢ​ያት በአ​ንድ አፍ ሆነው ለን​ጉሡ መል​ካም ይና​ገ​ራሉ፤ ቃል​ህም እንደ ቃላ​ቸው እን​ዲ​ሆን መል​ካም እን​ድ​ት​ና​ገር እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሚክያስን ሊጠራ ሄዶ የነበረውም መልእክተኛ፣ “እነሆ፣ ሌሎቹ ነቢያት በአንድ አፍ ሆነው፣ ለንጉሡ መልካምን ነገር እየተነበዩ ነው፤ እባክህ የአንተም ቃል እንደ ቃላቸው ይሁን፤ ንጉሡን ደስ የሚያሠኘውን ተናገር” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሚክያስንም ሊጠራ የሄደ መልክተኛ ሚክያስን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ነቢያት በአንድ ድምፅ ሆነው ለንጉሡ መልካም ነገር ይናገራሉ፤ ቃልህም እንደ ቃላቸው እንዲሆን መልካም እንድትናገር እለምንሃለሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሚክያስን ለመጥራት ሄዶ የነበረው መልእክተኛ በዚሁ ጊዜ ሚክያስ “ሌሎች ነቢያት በሙሉ ንጉሥ አክዓብ ድል የሚያደርግ መሆኑን የሚያረጋግጥ የትንቢት ቃል ተናግረዋል፤ ስለዚህ አንተም እንደ እነርሱ ብታደርግ ይሻልሃል” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሚክያስንም ሊጠራ የሄደ መልክተኛ “እነሆ፥ ነቢያት በአንድ አፍ ሆነው ለንጉሡ መልካም ይናገራሉ፤ ቃልህም እንደ ቃላቸው እንዲሆን መልካም እንድትናገር እለምንሃለሁ” አለው።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 18:12
11 交叉引用  

ነቢ​ያ​ትም ሁሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በን​ጉሡ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ታ​ልና ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ውጣና ተከ​ና​ወን” እያሉ እን​ዲሁ ትን​ቢት ይና​ገሩ ነበር።


ሚክ​ያ​ስም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! አም​ላኬ የሚ​ለ​ውን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለ።


አን​ተም እን​ዲህ ብለ​ሃል፦ ኀያል እርሱ ምን ያው​ቃል? በድ​ቅ​ድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ሊፈ​ርድ ይች​ላ​ልን?


ነቢ​ያ​ትን፥ “አት​ን​ገ​ሩን፤ ባለ ራእ​ዮ​ች​ንም አታ​ው​ሩን፤ ነገር ግን ሌላ​ውን ስሕ​ተት አስ​ረ​ዱን፤ ንገ​ሩ​ንም” ይላሉ፤


ነገ​ሥ​ታቱ በክ​ፋ​ታ​ቸው፥ አለ​ቆ​ቹም በሐ​ሰ​ታ​ቸው ደስ ተሰኙ።


ነገር ግን ቤቴል የን​ጉሥ መቅ​ደ​ስና የመ​ን​ግ​ሥት ቤት ናትና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በዚህ ደግሞ ትን​ቢት አት​ና​ገር” አለው።


ነፋስንም ተከትሎ፦ ስለ ወይን ጠጅና ስለ ስካር ትንቢት እናገርልሃለሁ ብሎ ሐሰትን የሚናገር ሰው ቢኖር እርሱ ለዚህ ሕዝብ ነቢይ ይሆናል።


ትንቢት አትናገሩ ብለው ይናገራሉ፥ በእነዚህ ላይ ትንቢት አይናገሩም፥ ስድብም አይርቅም።


ኢያ​ሱ​ንና እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ።


跟着我们:

广告


广告