Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 18:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ነቢ​ያ​ትም ሁሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በን​ጉሡ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ታ​ልና ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ውጣና ተከ​ና​ወን” እያሉ እን​ዲሁ ትን​ቢት ይና​ገሩ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የቀሩትም ነቢያት ሁሉ፣ “እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና፣ በገለዓድ በምትገኘው ራሞት ላይ ዝመትባት” በማለት ተመሳሳይ ትንቢት ይናገሩ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ነቢያትም ሁሉ፦ “ጌታ በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ወደ ሬማት ዘገለዓድ ሂድ፥ ለአንተም ይከናወንልሃል” እያሉ ተመሳሳይ የሆነን ትንቢት ይናገሩ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሌሎቹም ነቢያት ይህንኑ ቃል በመደገፍ “በራሞት ላይ ዝመት፤ ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔር ድልን ይሰጥሃል” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ነቢያትም ሁሉ “እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ወደ ሬማት ዘገለዓድ ሂድና ተከናወን” እያሉ እንዲሁ ትንቢት ይናገሩ ነበር።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 18:11
11 交叉引用  

በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ የጌ​ቤር ልጅ ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም በገ​ለ​ዓድ ያሉት የም​ናሴ ልጅ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ነበሩ፤ ለእ​ር​ሱም ደግሞ በባ​ሳን፥ በአ​ር​ጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥ​ርና የናስ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች የነ​በ​ረ​ባ​ቸው ስድሳ ታላ​ላቅ ከተ​ሞች ነበ​ሩ​በት፤


የካ​ህ​ናን ልጅ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም የብ​ረት ቀን​ዶች ሠርቶ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሶር​ያ​ው​ያ​ንን እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ በእ​ነ​ዚህ ትወ​ጋ​ለህ” አለ።


ሚክ​ያ​ስ​ንም ሊጠራ የሄደ መል​እ​ክ​ተኛ፥ “እነሆ፥ ነቢ​ያት በአ​ንድ አፍ ሆነው ለን​ጉሡ መል​ካም ይና​ገ​ራሉ፤ ቃል​ህም እንደ ቃላ​ቸው እን​ዲ​ሆን መል​ካም እን​ድ​ት​ና​ገር እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ከነ​ቢ​ያቱ አራት መቶ ሰዎ​ችን ሰብ​ስቦ፥ “ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ለሰ​ልፍ ልሂ​ድን? ወይስ ልቅር?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በን​ጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ታ​ልና ውጣ” አሉት።


እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ በጥርሳቸው ሲነክሱ በሰላም ይሰብካሉ፥ በአፋቸው ግን አንዳች በማይሰጥ ሰው ላይ ሰልፍን ያስቡበታል።


እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፤ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል።


አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።


跟着我们:

广告


广告