Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 18:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የካ​ህ​ናን ልጅ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም የብ​ረት ቀን​ዶች ሠርቶ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሶር​ያ​ው​ያ​ንን እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ በእ​ነ​ዚህ ትወ​ጋ​ለህ” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በዚህ ጊዜ፣ የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስ የብረት ቀንዶች ሠርቶ፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሶርያውያን እስኪጠፉ ድረስ በእነዚህ ትወጋቸዋለህ’ ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የክንዓና ልጅ ሰዴቅያስም የብረት ቀንዶች ሠርቶ፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ሶሪያውያንን እስኪጠፉ ድረስ በእነዚህ ትወጋቸዋለህ’ ” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከእነርሱም አንዱ የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ከብረት ቀንዶችን ሠርቶ አክዓብን “እግዚአብሔር ‘በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ’ ይልሃል” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የክንዓና ልጅ ሰዴቅያስም የብረት ቀንዶች ሠርቶ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ሶሪያውያንን እስኪጠፉ ድረስ በእነዚህ ትወጋለህ’” አለ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 18:10
15 交叉引用  

የከ​ሓና ልጅ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም የብ​ረት ቀን​ዶች ሠርቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በእ​ነ​ዚህ ቀን​ዶች ሶር​ያ​ው​ያ​ንን ትወ​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ” አለ።


ነቢ​ያ​ትም ሁሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በን​ጉሡ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ታ​ልና ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ውጣና ተከ​ና​ወን” እያሉ እን​ዲሁ ትን​ቢት ይና​ገሩ ነበር።


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥና የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ልብሰ መን​ግ​ሥት ለብ​ሰው በሰ​ማ​ርያ በር መግ​ቢያ አጠ​ገብ በአ​ደ​ባ​ባይ በዙ​ፋ​ኖ​ቻ​ቸው ላይ ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ ነቢ​ያ​ትም ሁሉ በፊ​ታ​ቸው ትን​ቢት ይና​ገሩ ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ለሚ​ያ​ቃ​ልሉ ሰላም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፥ በፍ​ላ​ጎ​ታ​ቸ​ውና በል​ቡ​ና​ቸው ክፋት ለሚ​ሄ​ዱም ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያ​ገ​ኛ​ች​ሁም” ይላሉ።


“እኔ ሳል​ል​ካ​ቸው እነ​ዚህ ነቢ​ያት ሮጡ፤ እኔም ሳል​ነ​ግ​ራ​ቸው ትን​ቢ​ትን ተና​ገሩ።


ሕል​ምን አለ​ምን እያሉ በስሜ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን የነ​ቢ​ያ​ትን ነገር ሰም​ቻ​ለሁ።


እነሆ ከም​ላ​ሳ​ቸው ትን​ቢ​ትን አው​ጥ​ተው፦ እርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም ነው በሚሉ ነቢ​ያት ላይ ነኝ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰን​ሰ​ለ​ትና ቀን​በር ሥራ፤ በአ​ን​ገ​ት​ህም ላይ አድ​ርግ፤


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በስሜ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢ​ትን ስለ​ሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ ስለ ቆልያ ልጅ፥ ስለ አክ​ዓ​ብና ሰለ ማሴው ልጅ ስለ ሴዴ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም ፊት ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል።


እኔም ሳል​ና​ገር፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ​አል ስትሉ፥ ከንቱ ምዋ​ር​ትን የተ​ና​ገ​ራ​ችሁ፥ የሐ​ሰት ራእ​ይ​ንም ያያ​ችሁ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን?”


ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ይቀ​ቡ​አ​ቸ​ዋል፤ ከንቱ ነገ​ር​ንም ያዩ​ላ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አለ እያ​ሉም በሐ​ሰት ያም​ዋ​ር​ቱ​ላ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን አል​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውም።


ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም የተጣሉ ሰዎች ሆነው እውነትን ይቃወማሉ።


跟着我们:

广告


广告