Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 17:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም እየ​በ​ረ​ታና እጅ​ግም እየ​ከ​በረ ሄደ፤ በይ​ሁ​ዳም ግን​ቦ​ች​ንና የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ችን ሠራ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ኢዮሣፍጥም እያየለ ሄደ፤ በይሁዳም ምሽጎችና የዕቃ ማከማቻ ከተሞች ሠራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ኢዮሣፍጥም እየበረታና እጅግም እየከበረ ሄደ፤ በይሁዳም ግንቦችንና ለግምጃ ቤት የሚያገለግሉትን ከተሞች ሠራ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12-13 ስለዚህ ኢዮሣፍጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ ገናና እየሆነ ሄደ፤ በመላው ይሁዳ ምሽጎችንና፥ እጅግ የበዛ ስንቅና ትጥቅ የተከማቹባቸውን ከተማዎች ሠራ። በኢየሩሳሌምም የተለየ ችሎታ ያላቸውን ተዋጊዎች አኖረ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ኢዮሳፍጥም እየበረታና እጅግም እየከበረ ሄደ፤ በይሁዳም ግንቦችንና የጎተራ ከተሞችን ሠራ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 17:12
13 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት እጅግ አገ​ነ​ነው፤ ከእ​ርሱ በፊ​ትም ለነ​በ​ሩት ነገ​ሥ​ታት ያል​ሆ​ነ​ውን የመ​ን​ግ​ሥት ክብር ሰጠው።


ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ለኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ እጅ መን​ሻና የብር ግብር ያመጡ ነበር፤ ዐረ​ባ​ው​ያ​ንም ደግሞ ከመ​ን​ጎ​ቻ​ቸው ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በጎ​ች​ንና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየ​ሎ​ችን ያመ​ጡ​ለት ነበር።


በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ብዙ ሥራ ሠራ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰል​ፈ​ኞች ነበ​ሩት።


ለኢ​ዮ​ሣ​ፍ​ጥም ብዙ ብል​ጥ​ግ​ናና ክብር ነበ​ረው፤ ከአ​ክ​ዓ​ብም ወገን ሚስት አገባ።


በም​ድረ በዳ​ውም ግን​ቦ​ችን ሠራ፤ ብዙ ጕድ​ጓ​ድም ማሰ፤ በቆ​ላ​ውና በደ​ጋው ብዙ እን​ስ​ሶች ነበ​ሩ​ትና፤ ደግ​ሞም እርሻ ይወ​ድድ ነበ​ርና በተ​ራ​ራ​ማ​ውና በፍ​ሬ​ያ​ማው ስፍራ አራ​ሾ​ችና የወ​ይን አት​ክ​ል​ተ​ኞች ነበ​ሩት።


በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በይ​ሁዳ ሀገር ላይ ከተ​ሞ​ችን ሠራ፤ በዱር ስፍ​ራ​ዎ​ችም አም​ባ​ዎ​ች​ንና ግን​ቦ​ችን ሠራ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ሰው​ነ​ቱን አጽ​ናና፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ በላ​ዩም ግንብ ሠራ​በት፤ ከእ​ር​ሱም በስ​ተ​ውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ ወደ ዳዊ​ትም ከተማ የሚ​ያ​ወ​ጣ​ውን በር አጠ​ነ​ከረ፤ ብዙም መሣ​ሪ​ያና ጋሻ አዘ​ጋጀ።


በብ​ርቱ ሥራም ያስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው ዘንድ የሠ​ራ​ተ​ኞች አለ​ቆ​ችን ሾመ​ባ​ቸው፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም ፌቶ​ምን፥ ራም​ሴ​ንና የፀ​ሐይ ከተማ የም​ት​ባል ዖንን ጽኑ ከተ​ሞች አድ​ር​ገው ሠሩ።


跟着我们:

广告


广告