Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 14:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የእ​ን​ግ​ዶ​ቹ​ንም አማ​ል​ክት መሠ​ዊያ፥ የኮ​ረ​ብ​ታ​ው​ንም መስ​ገ​ጃ​ዎች አፈ​ረሰ፤ ሐው​ል​ቶ​ቹ​ንም ሰበረ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ አፀ​ዶ​ቹ​ንም ቈረጠ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ባዕዳን መሠዊያዎችንና ማምለኪያ ኰረብቶችን አስወገደ፤ ማምለኪያ ዐምዶችን አፈረሰ፤ አሼራ ለተባለች ጣዖት አምላክ የቆሙ የዕንጨት ቅርጽ ምስሎችንም ቈራረጠ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የእንግዶቹንም አማልክት መሠዊያ የኮረብታውንም መስገጃዎች አፈረሰ፥ ሐውልቶቹንም ሰባበረ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቈረጠ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ባዕዳን መሠዊያዎችንና በኰረብቶች ላይ የነበሩትን የአሕዛብ የማምለኪያ ስፍራዎችን አስወገደ፤ ለማምለኪያ የተሠሩ የድንጋይ ዐምዶችን ሰባበረ፤ አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ ምስሎችን አንከታክቶ ጣለ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የእንግዶቹንም አማልክት መሠዊያ የኮረብታውንም መስገጃዎች አፈረሰ፤ ሐውልቶቹንም ሰበረ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቈረጠ፤

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 14:3
17 交叉引用  

ጽድ​ቅ​ንና ፍር​ድን በማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ ልጆ​ቹ​ንና ቤቱን ያዝ​ዛ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ለው አው​ቃ​ለ​ሁና፤ ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ያደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ ነው።”


በኮ​ረ​ብ​ታም ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች አስ​ወ​ገደ፤ ሐው​ል​ቶ​ች​ንም ሰባ​በረ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ች​ንም ነቃ​ቀለ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እስ​ከ​ዚህ ዘመን ድረስ ያጥ​ኑ​ለት ነበ​ርና ሙሴ የሠ​ራ​ውን የና​ሱን እባብ አጠፋ፤ ስሙ​ንም “ነሑ​ስ​ታን” ብሎ ጠራው።


ሐው​ል​ቶ​ቹ​ንም ሁሉ አደ​ቀቀ፥ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቹ​ንም ሁሉ ቈረጠ፤ በስ​ፍ​ራ​ቸ​ውም የሙ​ታ​ንን አጥ​ንት ሞላ​በት።


የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ድ​ንም ጣዖት ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ውጭ ወደ ቄድ​ሮን ፈፋ አወ​ጣው፤ በቄ​ድ​ሮ​ንም ፈፋ አጠ​ገብ አቃ​ጠ​ለው፤ አድ​ቅ​ቆም ትቢያ አደ​ረ​ገው፥ ትቢ​ያ​ው​ንም በሕ​ዝብ መቃ​ብር ላይ ጨመ​ረው።


አሳም በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ቅን ነገር አደ​ረገ፤


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይሹ ዘንድ፥ ሕጉ​ንና ትእ​ዛ​ዙ​ንም ያደ​ርጉ ዘንድ የይ​ሁ​ዳን ሕዝብ አዘዘ።


በኮ​ረ​ብታ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች ግን ከእ​ስ​ራ​ኤል አላ​ራ​ቀም። ገና በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ እስከ አሁን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ የአሳ ልብ በዘ​መኑ ሁሉ ፍጹም ነበረ።


ይኸ​ውም በተ​መ​ሰ​ገ​ነው ስምህ ነው፤ ኀይ​ልህ ከመ​ገ​ለጡ የተ​ነሣ ሁሉ የሚ​ር​ድና የሚ​ን​ቀ​ጠ​ቀጥ፤


የበ​ዓ​ሊ​ም​ንም መሠ​ዊ​ያ​ዎች በፊቱ አፈ​ረሰ፤ በላ​ዩም የነ​በ​ሩ​ትን ኮረ​ብ​ታ​ዎ​ችን ዐፀ​ዶ​ቹ​ንም ቈረጠ፤ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ት​ንና ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም ምስ​ሎች ሰባ​በረ፤ አደ​ቀ​ቃ​ቸ​ውም፤ ይሠ​ዉ​ላ​ቸው በነ​በ​ሩት ሰዎች መቃ​ብ​ርም ላይ በተ​ና​ቸው።


ነገር ግን መሠ​ው​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን ታፈ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትሰ​ብ​ራ​ላ​ችሁ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቻ​ቸ​ውን ትቈ​ር​ጣ​ላ​ችሁ፤ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ላ​ችሁ፤


የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቻ​ች​ሁን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ በእጅ የተ​ሠሩ የዕ​ን​ጨት ምስ​ሎ​ቻ​ች​ሁ​ንም አጠ​ፋ​ለሁ፤ ሬሳ​ች​ሁ​ንም በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ችሁ ሬሳ​ዎች ላይ እጥ​ላ​ለሁ፤ ነፍ​ሴም ትጸ​የ​ፋ​ች​ኋ​ለች።


የአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ምስል በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ሠ​ራ​ባ​ቸ​ውን ብር​ንና ወር​ቅን፥ አት​መኝ፤ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እን​ዳ​ት​በ​ድ​ል​በት ከእ​ርሱ ምንም አት​ው​ሰድ።


ነገር ግን እን​ዲህ አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ውን አፍ​ርሱ፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰባ​ብሩ፥ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቍረጡ፥ የአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ምስል በእ​ሳት አቃ​ጥሉ።


跟着我们:

广告


广告