Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 13:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሦስት ዓመ​ትም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነገሠ፤ የእ​ና​ቱም ስም መዓካ ነበረ፤ የገ​ባ​ዖን ሰው የኡ​ር​ኤል ልጅ ነበ​ረች። በአ​ብ​ያና በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መካ​ከ​ልም ሰልፍ ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሦስት ዓመት ገዛ። እናቱ ሚካያ ትባላለች፤ እርሷም የጊብዓ ተወላጅ የኡርኤል ልጅ ነበረች። በአብያና በኢዮርብዓምም መካከል ጦርነት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሦስት ዓመት በኢየሩሳሌም ነገሠ፤ የእናቱም ስም ሚካያ ነበረ፥ የገብዓ ሰው የኡርኤል ልጅ ነበረች። በአብያና በኢዮርብዓም መካከል ጦርነት ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱ ሚካያ ተብላ የምትጠራ የጊብዓ ከተማ ተወላጅ የሆነ የኡሪኤል ልጅ ነበረች። በአቢያና በኢዮርብዓም መካከል ጦርነት ተነሥቶ ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሦስት ዓመት በኢየሩሳሌም ነገሠ፤ የእናቱም ስም ሚካያ ነበረ፤ የገብዓ ሰው የኡርኤል ልጅ ነበረች።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 13:2
11 交叉引用  

የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ነገር፥ እን​ዴት እንደ ተዋጋ፥ እን​ዴ​ትም እንደ ነገሠ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም የነ​ገ​ሠ​በት ዘመን ሃያ አራት ዓመት ነበረ፥ ከአ​ባ​ቶ​ቹም ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ ልጁም ናባጥ በፋ​ን​ታው ነገሠ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሦስት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም መዓካ የተ​ባ​ለች የአ​ቤ​ሴ​ሎም ልጅ ነበ​ረች።


ከእ​ር​ስ​ዋም በኋላ የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምን ልጅ መዓ​ካን አገባ፤ እር​ስ​ዋም አብ​ያን፥ ኢያ​ቲን፥ ዚዛን፥ ሰሎ​ሚ​ትን ወለ​ደ​ች​ለት።


የሮ​ብ​ዓ​ምም የፊ​ተ​ኛ​ውና የኋ​ለ​ኛው ነገር እነሆ፥ በነ​ቢዩ ሰማ​ያና በባለ ራእዩ በአዶ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? ሮብ​ዓ​ምም ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ጋር በዘ​መኑ ሁሉ ይዋጋ ነበር።


አብ​ያም የተ​መ​ረ​ጡ​ትን አራት መቶ ሺህ ኀያ​ላን ሰል​ፈ​ኞች ይዞ ወደ ሰልፍ ወጣ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም የተ​መ​ረ​ጡ​ትን ስም​ንት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ይዞ በእ​ርሱ ላይ ተሰ​ለፈ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ባል የኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎን ከተ​ማና የኢ​ያ​ሪ​ሞን ከተማ ገባ​ዖን፤ ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው። የብ​ን​ያም ልጆች ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።


አል​ፈ​ውም ሄዱ፤ የብ​ን​ያ​ምም ነገድ በም​ት​ሆ​ነው በገ​ባ​ዖን አጠ​ገብ ሳሉ ፀሐይ ገባ​ች​ባ​ቸው።


እነ​ሆም አንድ ሽማ​ግሌ ከእ​ር​ሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፤ ይህም ሰው ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር ነበረ፤ በገ​ባ​ዖ​ንም በእ​ን​ግ​ድ​ነት ተቀ​ምጦ ነበር፤ የዚያ ሀገር ሰዎች ግን የብ​ን​ያም ልጆች ነበሩ።


ሳኦ​ልም ወደ ቤቱ ወደ ገባ​ዖን ሄደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልባ​ቸ​ውን የነ​ካው ኀያ​ላ​ንም ከሳ​ኦል ጋር ሄዱ።


跟着我们:

广告


广告