Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 11:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እርሱ ግን ለኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች፥ ከንቱ ለሆኑ ጣዖ​ታ​ቱም፥ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ለሠ​ራ​ቸው እን​ቦ​ሶ​ችም ካህ​ና​ትን አቆመ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እርሱም ለየኰረብታው መስገጃ እንዲሁም ለሠራቸው የፍየልና የጥጃ ምስሎች የራሱን ካህናት ሾመ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እርሱ ግን ለኮረብታው መስገጃዎች ለአጋንንቱም ለሠራቸውም እምቦሶች ካህናትን ሾመ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ኢዮርብዓም በኰረብቶች ላይ በሚገኙ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎች የሚያገለግሉ፥ ለአጋንንትና እርሱ ራሱ በጥጆች አምሳል ለሠራቸው ጣዖቶች የሚሰግዱ የራሱን ካህናት ሾሞ ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እርሱ ግን ለኮረብታው መስገጃዎች፥ ለአጋንንቱ፥ ለሠራቸውም እምቦሶች ካህናትን አቆመ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 11:15
16 交叉引用  

ንጉ​ሡም ተማ​ከረ፤ ሁለ​ትም የወ​ርቅ ጥጆች ሠርቶ፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መው​ጣት ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጡ​አ​ችሁ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ችሁ እነሆ” አላ​ቸው።


በኮ​ረ​ብ​ቶ​ቹም ላይ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠራ፤ ከሌዊ ልጆች ካይ​ደሉ ከማ​ን​ኛ​ውም ሕዝብ ሁሉ የጣ​ዖት ካህ​ና​ትን ሾመ።


ከዚ​ህም በኋላ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከክ​ፋቱ አል​ተ​መ​ለ​ሰም፤ ነገር ግን ለኮ​ረ​ብ​ታ​ዎቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች አብ​ልጦ ከሕ​ዝብ ሁሉ የጣ​ዖት ካህ​ና​ትን ሾመ፤ የሚ​ወ​ድ​ደ​ው​ንም ሁሉ ይቀ​ድስ ነበር፤ እር​ሱም ለኮ​ረ​ብ​ቶቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች ካህን ይሆን ነበር።


ከአ​ን​ተም አስ​ቀ​ድ​መው ከነ​በ​ሩት ሁሉ ይልቅ ክፉ ሠራህ፤ ታስ​ቈ​ጣ​ኝም ዘንድ ሄደህ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትና ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ትን ምስ​ሎች አደ​ረ​ግህ፤ ወደ ኋላ​ህም ተው​ኸኝ።


አሁ​ንም በዳ​ዊት ልጆች እጅ የሚ​ሆ​ነ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ልት​ቋ​ቋሙ እን​ዲህ ትላ​ላ​ችሁ። እና​ን​ተም እጅግ ታላቅ ሕዝብ ናችሁ፥ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም አማ​ል​ክት አድ​ርጎ የሠ​ራ​ላ​ችሁ የወ​ርቅ እን​ቦ​ሶች ከእ​ና​ንተ ጋር ናቸው።


የአ​ሮ​ንን ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን አላ​ሳ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ምን? ከም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ ለራ​ሳ​ችሁ ካህ​ና​ትን አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምን? አንድ ወይ​ፈ​ንና ሰባት አውራ በጎ​ችን ይዞ ራሱን ይቀ​ድስ ዘንድ የሚ​መጣ ሁሉ አማ​ል​ክት ላል​ሆ​ኑት ለእ​ነ​ዚያ ካህን ይሆ​ናል።


ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ልሶ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ እኒህ ሕዝብ ታላቅ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ዋል፤ ለራ​ሳ​ቸ​ውም የወ​ርቅ አማ​ል​ክት አድ​ር​ገ​ዋል፤


ዳግ​መ​ኛም በደሉ፤ ጠራቢ በሚ​ሠ​ራው አም​ሳል ከወ​ር​ቃ​ቸ​ውና ከብ​ራ​ቸው ጣዖ​ትን ሠሩ፤ እን​ዲ​ህም አሉ “ሰውን ሠዉ፤ ላሙ ግን አል​ቋል።”


መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ው​ንም ደግሞ ተከ​ት​ለው ላመ​ነ​ዘ​ሩ​ባ​ቸው ለሰ​ይ​ጣ​ናት አይ​ሠዉ። ይህ ለእ​ነ​ርሱ ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።”


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያይ​ደለ ለአ​ጋ​ን​ንት፥ ለማ​ያ​ው​ቋ​ቸ​ውም አማ​ል​ክት፥ ድን​ገት ለተ​ገኙ ለማ​ይ​ሠ​ሩና ለማ​ይ​ጠ​ቅሙ አማ​ል​ክት፥ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ለማ​ያ​ው​ቋ​ቸው አማ​ል​ክት ሠዉ።


መንፈስ ግን በግልጥ “በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ፤” ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥


ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።


跟着我们:

广告


广告