Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ወደ ተራ​ራ​ማ​ውም ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ሄዱ፤ በሲ​ልካ ምድ​ርም አለፉ፤ አላ​ገ​ኙ​አ​ቸ​ው​ምም፤ በፋ​ስ​ቂም ምድር አለፉ፤ በዚ​ያም አል​ነ​በ​ሩም፤ በኢ​ያ​ሚ​ንም ምድር አለፉ፤ አላ​ገ​ኙ​አ​ቸ​ው​ምም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ስለዚህ በኰረብታማው በኤፍሬም አገርና በሻሊሻ አካባቢ ባለው ስፍራ ሁሉ ተዘዋወረ፤ ሆኖም አህዮቹን አላገኙም። ወደ ሻዕሊምም ግዛት ዘልቀው ገቡ፤ አህዮቹ ግን በዚያም አልነበሩም። እንዲሁም በብንያም ግዛት በኩል ዐለፈ፤ ሆኖም አላገኟቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ስለዚህ በተራራማው በኤፍሬም አገርና በሻሊሻ አካባቢ ባለው ስፍራ ሁሉ ተዘዋወረ፤ ሆኖም አህዮቹን አላገኘም። ወደ ሻዕሊምም ግዛት ዘልቀው ገቡ፤ አህዮቹ ግን በዚያም አልነበሩም። ከዚያም በብንያም ምድር በኩል አለፉ፤ ሆኖም አላገኟቸውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሳኦልና አገልጋዩም ተነሥተው በተራራማው የኤፍሬም አገርና በሻሊሻ ምድር በኩል አልፈው አህዮቹን መፈለግ ጀመሩ፤ ነገር ግን አህዮቹን ማግኘት አልቻሉም፤ ከዚያም በሻዕሊም ምድር በኩል አልፈው ሳያገኙአቸው ቀሩ፤ እንደገናም በብንያም ግዛት በኩል አለፉ፤ ይሁን እንጂ አሁንም አህዮቹን ማግኘት አልቻሉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በተራራማው በኤፍሬም አገርና በሻሊሻ አለፉ፥ አላገኙአቸውምም፥ በሻዕሊም ምድርም አለፉ፥ በዚያም አልነበሩም፥ በብንያም ምድርም አለፉ፥ አላገኙአቸውምም።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 9:4
9 交叉引用  

ያዕ​ቆ​ብም ከሁ​ለቱ ወን​ዞች መካ​ከል በተ​መ​ለሰ ጊዜ በከ​ነ​ዓን ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ ሰቂ​ሞን ከተማ ወደ ሴሎም መጣ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ፊት ለፊት ሰፈረ።


አንድ ሰውም ከቤ​ት​ሣ​ሪሳ ከእ​ህሉ ቀዳ​ም​ያት፥ ሃያ የገ​ብስ እን​ጀራ፥ የእ​ህ​ልም እሸት በአ​ቁ​ማዳ ይዞ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው መጣ፤ ኤል​ሳ​ዕም አገ​ል​ጋ​ዩን፥ “ይበሉ ዘንድ ለሕ​ዝቡ ስጣ​ቸው” አለ።


ዮሐ​ን​ስም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሳ​ሌም አቅ​ራ​ቢያ በሄ​ኖን ያጠ​ምቅ ነበር፤ በዚያ ብዙ ውኃ ነበ​ርና፤ ብዙ ሰዎ​ችም ወደ እርሱ እየ​መጡ ያጠ​ም​ቃ​ቸው ነበር።


ሰሊ​ባን፥ አሞን፥ ሴላታ፥


የአ​ሮ​ንም ልጅ ሊቀ ካህ​ናቱ አል​ዓ​ዛር ሞተ፤ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ለልጁ ለፊ​ን​ሐስ በተ​ሰ​ጠ​ችው በጊ​ብ​ዓት መሬት ቀበ​ሩት።


በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ሚካ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ።


በዚ​ያም ዘመን ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም። በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ማዶ የተ​ቀ​መጠ አንድ ሌዋዊ ሰው ነበረ፤ ከይ​ሁዳ ቤተ ልሔ​ምም ዕቅ​ብት አገባ።


በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ከአ​ር​ማ​ቴም መሴፋ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። ስሙም፥ የና​ሲብ ልጅ የቴቆ ልጅ፥ የኤ​ልዩ ልጅ ፥ የኢ​ያ​ር​ም​ያል ልጅ፥ ኤፍ​ራ​ታ​ዊው ሕል​ቃና ነበረ።


የሳ​ኦ​ልም አባት የቂስ አህ​ዮች ጠፍ​ተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦ​ልን፥ “ከብ​ላ​ቴ​ኖቹ አን​ዱን ወስ​ደህ ተነ​ሡና ሄዳ​ችሁ አህ​ዮ​ችን ፈልጉ” አለው።


跟着我们:

广告


广告